በኒውዝላን ክራይስትቼርች በሁለት መስጊዶች ላይ በተሰነዘረው አሰቃቂ ጥቃት በኒውዝላን ክራይስትቼርች በሁለት መስጊዶች ላይ በተሰነዘረው አሰቃቂ ጥቃት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 09/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበስቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ካደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በመቀጠል  ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እና በዕለተ ሰንበት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን የመልኣኩ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሁሉንም የሰው ዘር ለማጥፋት በማሰብ የሚያደርጉት ጦርነቶች እና ግጭቶች አሁንም ተጠናክረው መቀጠላቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው በቅርቡ በኒውዝላን ክራይስትቼርች ተብሎ በሚታወቅበት ሥፋር በሁለት መስጊዶች ላይ በተሰነዘረው አሰቃቂ ጥቃት የብዙ ሰዎች ነፍስ ማለፉ እና ብዙዎችን ለስቃይ የዳረገ ክስተት መሆኑን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በዚህ ጥቃት ነፍሳችውን ላጡ ሰዎች፣ ለቆሰሉ እና እንዲሁም በአጠቃላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሁሉ ጸሎቴን አቀርባለሁ ብለዋል። በዚህ አገጣሚ ወንድሞቻችን ከሆኑት ከመላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች ጎን መሆኔን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል። ጥላቻና ዓመፅን ለመዋጋት ይችል ዘንድ በጸሎት መንፈስ ሰላም ወዳድ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በአንድነት እንዲቆሙ ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በሳምንታዊ መልእክታቸው ማብቂያ ላይ በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ የተሰበሰቡትን ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች ሰላምታን አቅርበው እንደ ተለመደው “እብካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መሰናበታቸውን ከስፍራው ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

17 March 2019, 15:55