የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ የርዕሠ ሊቃነ ጵጵስናቸው 80ኛ ዓመት ታስቦ ዋለ።።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና አመጽ ላጎሳቆለው ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስን የሰላም ብርሃን ለማምጣት ከፍተኛ ጥረቶችን ያደረጉት፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ የርዕሠ ሊቃነ ጵጵስና 80ኛ ዓመት መታሰቢያ ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ. ም. ተከብሮ መዋሉ ይታወሳል።

ካርዲናል ኤውጄኒዮ ፓቼሊ በሚል ስም የሚታወቁት፣ መላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንን ለማገልገል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ፒዮስ 12ኛ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትነት የአገልግሎት ስልጣን ያገኙበት 80ኛ ዓመት ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ. ም. መሆኑ ሲታወስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ በኣክቶሊካዊት ቤተክርስቲያን 260ኛ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ መላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንን ለ19 ዓመታት ያገለገሉ መሆናቸው ይታወቃል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ የጵጵስናን ማዕረግ የተቀበሉት፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፖርቱጋል ፋጢማ በሚባል መንደር ለመጀመሪያ ጊዜ በተገለጸችበት በግንቦት 5 ቀን 1909 ዓ. ም. መሆኑ ይታወሳል። የጵጵስና ማዕረግን ከተቀበሉ በኋላ እመቤታችን ማርያም የተገለጸችላትን እህት ሉቺያን ለብዙ ጊዜ ያገኟት መሆኑ ሲታወስ በ1932 ዓ. ም. የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ግልጸት እርግጠኛነት ማጽደቃቸው ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ በ1942 ዓ. ም. የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነፍስ እና በስጋዋ ወደ ሰማይ እናዳረገች ከመጀመሪያው ዘመን አንስቶ የነበረውን የቤተክርስቲያን የእምነት ዶግማን አጽድቀዋል። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትነት ሐዋርያዊ የአገልግሎት ስልጣን ከተረከቡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሁለቱ ቅዱሳት፣ ማለትም በኢጣሊያ የአሲሲ ተወላጅ የሆነው ቅዱስ ፍራንችስኮስ እና አሁንም በኢጣሊያ የሴና ከተማ ተወላጅ የሆነች ቅድስት ካታሪና የአገሩ ባልደረባ እንዲሆኑ መወሰናቸው ይታወሳል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ በቴሌቪዥን መስኮቶች ለመታየት የመጀመሪያው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው ታውቋል። በቅድስት መንበር ሥር የሚገኙትን ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤቶችን በአዲስ መልክ በማዋቀር እና በ1942 ዓ. ም. የተከበረውን ጠቅላላ የኢዮቤልዩ ክብረ በዓልን ማስተባበራቸው ይታውወሳል። የቤተሰብ ሕይወት እንዲያድግ በማድረግ ለነፍሳትም እንክብካቤን በመስጠት ረገድ ትልቅ አስተዋጽዖን ማድረጋቸው ይታወሳል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ የክርስትና እምነት አስተምህሮችን ወደ ጎን በማድረግ፣ ፈጣሪንም በመካድ የኮሚኒስት ስርዓትን የሚከተሉ ምዕመናንን ከቤተክርስቲያን እስከማግለል የደረሱ መሆናቸው ይታወቃል።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት፣

ችግሮች በበዙበት የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት ለሐዋርያዊ አገልግሎት የበቁት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ ነሐሴ 18 ቀን 2031 ዓ. ም. ባስተላለፉት የሬዲዮ መልዕክታቸው፣ የሰው ልጅ እጅግ አስከፊ አደጋ ላይ እንደሚገኝ በማወቅ፣ ለመንግሥታት መሪዎች እና ለመላው ሕዝብ ባሳለፉት መልዕክታቸው ነፍሳትን ወደ ፍትህ እና ወደ ሰላም እንድንመልስ ዘወትር የሚጠይቀን የእግዚአብሔር ድምጽ ወይም ጥያቄ ችላ ማለት የለብንም ማለታቸው ይታወሳል። በማከልም በጦር መሣሪያ በመታገዝ ሳይሆን ምክንያታዊ የሆነ ትክክለኛ መንገድን በመከተል ፍትህን እናንግስ ብለዋል። ጦርነት ከሚያመጣው የሕይወት እና የንብረት ጥፋት በማምለጥ ወደ ሰላም የሚደረስበት ተስፋ እንዳለ ገልጸው ሰላምን በማንገስ የምናጣው ነገር የለም። ጦርነትን በማካሄድ ሁሉን እናጣለን ብለዋል። እነዚህን ሐዋርያዊ መልዕክቶችን በማስስተላለፍ፣ በጦርነት ለሚሰቃዩት እርዳታን በማዳረስ እና ከለላን በመስጠት ስቃያቸውንም መካፈላቸው ይታወሳል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ ይህን አቋማቸውን በመያዝ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን የሰላም እና የተስፋ ብርሃን በይፋ ለመመስከር ወደ አደባባይ በመውጣታቸው ይታወሳል። በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ የሮም ከተማ ነዋሪዎች ለጦርነት አደጋ መተው ያልፈለጉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ በሚያዚያ ወር 1937 ዓ. ም. ባስተላለፉት የሬዲዮ መልእክታቸው ለዓለም ሰላም በተለይም ለሩቅ ምሥራቅ አገሮች ጸሎታቸውን ካቀረቡ በኋላ ጦርነቱ በእነዚህ አገራት ከፍተኛ የሕይወት እና የንብረት ጥፋትን እንዳስከተለ ገልጸው የሕይወት እና የንብረት ጉዳት ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ሞራላዊ አስተሳሰቡን እንዲያጣ ማድረጉን ገልጸው ከዚህ አስከፊ መንገድ ወጥተን ሰላም የነገሰባትን ዓለም መገንባት እንደሚያስፈልግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በሰኔ 2 ቀን 1937 ዓ. ም. ለብጹዓን ካርዲናሎች ባሰሙት ንግግርም ሰላም አደጋ ላይ መውደቁን ገልጸው መላዋ ቤተክርስቲያን በዓለም ዙሪያ ሰላምን ለማምጣት፣ በተለይም የቤተክርስቲያን አባቶች ጥንቃቄ በተመላበት ሂደት እና በታማኝነት አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ በማድረግ ሐላፊነትን መወጣት እንዳለባቸው ማሳሰባቸው ይታወሳል።

02 March 2019, 16:29