ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያለ አንድነት ልማት ሊኖር እንደማይችል ገለጹ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ውድ ወዳጆቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን፣

ሰላምታዬን እልክላክሁላችሁ ጉባኤ ያችሁም ውጤታማ እንዲሆን እመኛለሁ። በቅርቡ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያደረግሁትን እና የተደረገልኝን ደማቅ አቀባበል አስታውሳለሁ። ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባደረግሁት ሐዋርያዊ ጉብኝቴ ወቅት ያች አገር ያለፈ ዘመናዊነትን ለማምጣጣት በምታደርገው ጥረቶቿ መካአክል ያለፈ ታሪኳንም ያልዘነጋች አገር መሆኗል ተረግቼአለሁ።  ልማትን ለማምጣት በምታደርገው ጥረት መካከል መቻቻልን፣ ወንድማማችነትን፣ እርስ በእርስ መከባበርን እና ነጻነትን በተግባር የምታሳይ አገር መሆኗንም ተመልክቼአለሁ። በተጨማሪም ምንም በሌለበት በረሃማው ሥፍራ አበቦች ለምልመው ሲያድጉ ተመልክቼአለሁ። ከሐዋርያዊ ጉብኝቴ መለስ በሌሎችም በርካታ የዓለማችን ክፍሎች የሚገኙ በርሃማ አካባቢዎች ሊለሙ እና በአበቦች ሊሸፈኑ እንደሚችሉ ተስፋ አድርጌ አለሁ። ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው የምንተጋገዝ ከሆነ፣ ግልጽነት እና መከባበር ያለ ከሆነ፣ በዓለማችን ውስጥ የሚገኘውን የእያንዳንዱን ሰው ችግር እንደ ራስ ችግር በመቁጠር ለማቃለል የምንነሳ ከሆነ በእርግጥም በጋራ ማደግ እንደሚቻል አምናለሁ።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ ትኩረትን በመስጠት እየተወያያችሁ ባላችሁባቸው መሠረታዊ የሆኑ ርዕሠ ጉዳዮች እነዚህም በፖለቲካ ዙሪያ፣ በምጣኔ ሃብት እድገት፣ በአካባቢ ጥበቃ እና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ እንደሆነ እገነዘባለሁ። እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የምታደርጉት ውይይቶች፣ ከእነዚህ ርዕሠ ጉዳዮች የበለጠ ተጠቃሚዎች ልንሆን የምንችለው እንዴት ነው የሚል ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ምን የመሰለ ዓለምን በጋራ ሆነን መገንባት እንፈልጋለን የሚል እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ አስተሳሰብ ወይም ጥያቄ ደግሞ የምጣኔ ሃብትን ለማሳደግ ወይም ኤኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን ስለማሟላት ሳይሆን ስለ ሕዝቦች እና ስለ ሰው ልጅ ቅድሚያ መስጠትን ይጠይቃል። ይህ ጥያቄ ለነገ ተብሎ ማደር ያለበት ሳይሆን ከዛሬ ጀምሮ ወደፊት የሚጠብቀንን የሰው ልጆች ሕይወትን በሃላፊነት በመሸከም፣ ዛሬ የምንኖርባትን ዓለም በከንቱ ሳናወድም ተንከባክበን በማቆየት ወደ ፊት ለሚመጣው ትውልድ ማስረከብን፣ የምንኖርባትን ዓለም ብቻ ሳይሆን ስነ ሞራላዊ ግዴታችንንም ጠብቀን ማቆየትን ይመለከታል።

አንድነታችንን ሳናጠናክር ስለ ዘላቂ ልማት መናገር አንችልም። ስለ ሰው ልጆች ሁለ ገብ እድገት ስንናገር፣ እያንዳንዱን የማሕበረሰብ ክፍል ያሳተፈ የጋራ ጥረት ካልሆነ እድገት ብለን መናገር አንችልም። ዛሬ ከምን ጊዜም በበለጠ ሃሳብን በተግባር መተርጎም በሕዝቦች መካከል እውነተኛ ውይይት እንዲኖር ማድረግን ይጠይቃል። ምክንያቱም ሌሎች ያልተሳተፉበት ሃሳብ እና ተግባር ለወደ ፊት ማሕበራዊ ኑሮ አችን ዋስትና ሊሰጠን እንደማይችል አስባለሁ። በመሆኑም በውይይቶቻችሁ መካከል ለሰው ልጅ ቅድሚያን በመስጠት፣ ተጨንቀው የሚያሰሙት የሰው ልጆች ጩሄት በማዳመጥ፣ በድህነት ሕይወት የወደቁትንም በማሰብ፣ የሕጻናትንም ጥያቄዎች ግንዛቤ ውስጥ እንደምታስገቡ ተስፋ አደርጋለሁ። 

ሁለ ገብ ማሕበራዊ እድገትን ለማምጣትን የምታደርጉት ጥረት ፍሬያማ እንደሚሆን ተስፋ አደረጋለሁ። ጥረታችሁንም ለያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት ምቹ ዓለምን ለመገንባት የሚያስችል እንዲሆን እግዚአብሔር እንዲባርከው በጸሎቴ እጠይቀዋለሁ።

11 February 2019, 15:49