ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የሞት ቅጣት ኢሰባዊ የሆነ ተግባር ነው” ማለታቸው ተገለጸ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የሞት ቅጣት ኢሰባዊ የሆነ ተግባር ነው” ማለታቸው ተገለጸ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የሞት ቅጣት ኢሰባዊ የሆነ ተግባር ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ይሁን እንጂ ዛሬ አንድ ሰው በጣም ከባድ የሆኑ ወንጀሎች ከፈፀመ በኋላም እንኳን ቢሆን ሰብዓዊ የሆነ ክብሩ እንዳለ እንደ ሚቀጥል ለመገንዘብ ተችሉዋል። በተጨማሪም ሀገራት ባስቀመጡዋቸው ከፍተኛ ቅጣቶች ትርጉም ላይ አዲስ ግንዛቤ ተገኝቷል። በመጨረሻም የዜጎች ደኅንነት መጠበቁን የሚያረጋግጥ የበለጠ ውጤታማ የእስር ማቆያ ስርዓት የተዘጋጀ ቢሆንም፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ታራሚው ወይም በዳዩ የጎድለውን ሰነ-ምግባር በፍጹም መልሶ መጎንጸፍ አይችልም የሚለውን ሐሳብ ግን የማረጋገጥ እድል የለውም”። በዚህም ምክንያት ቤተክርስትያን በወንጌል ብርሃን በመመራት "የሞት ቅጣት በፍጹም ተቀባይነት የለውም ምክንያቱም የሞት ቅጣት የሰውን ልጅ ተጋላጭ የሚያደርግ እና በሰው ልጅ ክብር ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው በማለት ታስተምራለች፣ ይህ ቅጣት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፋጻሚ እንዳይሆን በጽናት ትሠራለች”።

ይህንን ለውጥ እና ማሻሻያ በተመለከተ አስተያየታቸውን ኦዜርቫቶሬ ሮማኖ ለተሰኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እለታዊ ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚኬላ እንደ ገለጹት “የሞት ቅጣት የሰው ልጅን ሰብዓዊ መብት ይቃረናል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
አዲስ የስብከተ ወንጌል ዜዴዎችን የሚያስተዋውቀው ጳጳሳዊ ምክርበት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚቄላ “በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካቶሊክ ቤተክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ውስጥ የሞት ፍርድን በተመለከተ ያደርጉት አዲሱ ማሻሻያ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስትያን ቀጣይነት ባለው መልኩ አስተምህሮዎቹዋን እያሻሻለች እንደ ምትሄድ ያሳየ ጠቃሚ አጋጣሚ መሆኑን” ጨምረው ገለጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ ቀደም ሲል የሞት ቅጣትን በተመለከተ የነበረውን አስተምህሮ በሐምሌ 25/2010 ዓ.ም የሞት ቅጣትን በሚያወግዝ አዲስ አስተምህር እንዲተካ በደረጉበት ወቅት እንደ ገለጹት “የሞት ፍራድ ሊገረሰስ የማይችለውን የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብር የሚቃረን በመሆኑ ቤተክርስትያን የሞት ፍራድን በጽናት ትቃወማለች!” ማለታቸውን ይታወሳል።
የእምነትን ይዘት የበለጠ ግልጽ እንዲሆን ያደርጋል
ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚቄላ ይህንን በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አማካይነት የተድረገውን ማሻሻያ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ጨምረው እንደ ገለጹት “እውነቱን ለመገር የአንቀጸ እመንት ማሻሻያዎች የእምነትን ይዘት የበለጠ ግልጽ እንዲሆን የሚያደርጉ ሂደቶች ናቸው” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ እምነትን በተመለከተ “አንድ ሰው የሞት ፍርድ በዘመናችን መፈጸም እንደ ሌለበት እንዲገነዘብ ያደርገ መልካም አጋጣሚ ነው” ብለዋል።
ይህ አሁን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ የተደርገው ለውጥ ሦስት ዋና ዋና እንድምታዎች እንዳሉት የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚቄላ “ከሁሉም በላይ አስፈላጊው እና ጠቃሚ ጉዳይ ለሁሉም የሰው ልጆች ሰብዓዊ ክብር እውቅና መሰጠቱ፣ የሰው ልጅ ነብስ ምንም እንኳን በጣም ከባድ የሚባል ወንጄል ቢሰራም እንኳን የሰው ልጅ ነብስ በፍጹም መጥፋት እንደ ሌለበት በግልጽ ያስቀመጠ ለውጥ” መሆኑን ገለጸዋል።
በተጨማሪም የክርስትያን ማኅበረሰብ የሰው ልጆችን ነብስ በተመለከተ ያላውን ግንዛቤ "አዎንታዊ" በሆነ መልኩ ለውጥ እንዲያደርጉ ያስቻለ አጋጣሚ መሆኑን የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፍዚቄላ አሁን ያለው የወንጀለኛ አያያዝ ሁኔታ ውጤታማ የሆኑ ስርዓቶችን እየተከተለ የሚገኝ በመሆኑ ይህም "በበደለኛ ሰዎች ላይ ይደረግ የነበረውን አሰቃቂ አደጋ እና ሰቆቃ በማስቀረት በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ስነ-ምግባራዊ የሆነ ለውጥ እንዲያመጡ እና ከጥፋታቸው ተመልሰው መልካም ሰዎች በመሆን ማኅበርሰቡን ተመልሰው እንዲቀላቀሉ እድል የሚሰጣቸው አጋጣሚ ነው” ብለዋል።
እምነት ማለት ለእያንዳንዱ ትውልድ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ መፍቀድ ማለት ነው
ይህ አሁን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ የተደርገው ለውጥ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስትያን አስተምህሮዎቹዋን የምታሻሽለበት መንገድ አንዱ አካል መሆኑን የጠቀሱ ሊቀ ጳጳስት ሪኖ ፍዚቄላ “የተቀደሰውን የእምነት አስተምህሮ ጠብቆ መሄድ ማለት እምነትን እንደ አንድ ጥናትዊ የሆነ አጽም አድርገን ጠብቀን መያዝ ማለት ግን አይደለም” ካሉ በኋላ “ነገር ግን በተቃራኒው እመነት ከእራሱ ባህሪ ጋር ያለውን ተፈጥሮኣዊ ውህደት ወይም ትስስር የበለጠ ለመጥራት እና እውነተኛ እምነት ማለት ለእያንዳንዱ ትውልድ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ መፍቀድ ማለት ነው” ብለዋል።
ይህ አሁን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ የተደርገው ለውጥ “ቅዱስ ወንጌልን በይበልጥ በመረዳት” የተደረገ በጣም ወሳኝ የነበረ ለውጥ እንደ ሆነ የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚቄላ “በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን በተመለከተ “ለረዥም ጊዜ የቆየውን የቤተክርስትያኗን አንቀጸ እመንት ትርጓሜ ለመቀየር በጣም ወሳኝ እርምጃ መወሰዳቸውን” አድንቀዋል።

የሞት ፍርድን ለመበየን የሚያስችል ውሳኔ ለመስጠት የሚያበቁትን “በጣም አደገኛ እና ኢሰባዊ የሆኑ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ቤተ ክርስትያን የተደበላለቀ ስሜት እንደሚፈጠር ትገነዘባለች” ካሉ በኋላ ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል. . .
የሞት ቅጣትን ለማስወገድ መጣር ማለት የተጎጂዎችን ስቃይ እና የፈጸሙባቸውን ኢፍትሀዊ የሆኑ ወንጀሎችን መርሳት ማለት ግን አይደለም። ይልቁንም የፍትህ ስርዓቱ የራሱን ወሳኝ እርምጃ እንዲወስድ ይረዳል፣ በቁጣትና በበቀል ሳይሆን ነገር ግን አሁን ካለው ጊዜያዊ ችግር ባሻገር በመሄድ ኋላፊነት መውሰድ ያስፈልጋል”።

ሊቀ ጳጳሳ ሪኖ ፍዚቄላ በቅርቡ በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ የሞት ፍርድን በተመለከተ የተደረገውን ለውጥ በተመለከተ ኦዜርቫቶሬ ሮማኖ ከተባለ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እለታዊ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት መደምደሚያ ላይ እንደ ተናገሩት "ሰብዓዊ ሕይወትን በፍቃደኝነት መጨቆን" ከክርስቲያን ገልጸት ጋር የሚቃረን ተገባር ነው” ማለታቸውንም መዘገባችን ይታወሳል።
 

28 February 2019, 13:06