ር. ሊ. ጳ ፍራንቸስኮስ “እናንተ የመጪው ሳይሆን በዛሬው ዘመን የምትገኙ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ”።

ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም እነሆኝ   የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተገኙበት በፓናማ ሲካሄድ የቆየው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን በትልንትናው እለት ማለትም በጥር 19/2011 ዓ.ም በሰላም መጠናቀቁ ይታወቃል።

በዚህ በ34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ከአምስት አህጉራት የተውጣጡ ከ167,000 በላይ ወጣቶች ተሳታፊ እንደ ነበሩም ቀደም ሲል መግለጻችን ይታውሳል። በዚህ በ34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ማብቂያ ላይ በዚያው በፓናማ ሜትሮ ፓርክ በመባል በሚጠራው ስፍራ ላይ በተደርገው የዚህ የ34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መገባደዱን በማስመልከት በተዘጋጀውና በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት በተካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ መጠናቀቁ ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት በወቅቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከሉቃስ (1፡1-4, 4፡14-21) ላይ ተወስዶ በተነበበው እና “ኢየሱስም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።  ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ።  የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል፣ ይህ በጆሮዋችሁ የሰማችሁት ቃል ዛሬ ተፈጸመ” በሚለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “እናንተ የመጪው ጊዜ ሳይሆን በዛሬው ዘመን የምትገኙ የእግዚኣብሔር ልጆች ናችሁ” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ አሳርገውት በነበረው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ እንድተከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም ይህ ዛሬ በጆሮዎቻችሁ የሰማችሁት የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ አላቸው” (ሉቃ 4፡20-21)።

እነዚህ ቃላት በመጠቀም የዛሬው ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ ምዳራዊ አገልግሎቱን በይፋ እንደ ጀመረ ይገልጻል። የጀመረውም እርሱ እያየው ባደገው በምኵራብ ውስጥ፣ በጎረቤቶቹና በሚያውቁት ሰዎች መካከል ሲሆን አልፎ ተርፎም አንዳንዶቹ እርሱ ሕጻን በነበረበት ወቅት እርሱን የሕግ ትምህርት አስተምረውት በነበሩ ሰዎች መካከል በመሆን ነበር። በመምህሩ (በኢየሱስ) ሕይወት ውስጥ ይህ ወሳኝ የሆነ ወቅት ነበር: በእዚያ ማኅበረሰብ ውስጥ የተማረና ያደገው ልጅ፣ በመካከላቸው ቆሞ ስያስተምር/ሲያውጅ እና የእግዚኣብሔርን ሕልም እውን ሲያደርግ እናያለን። ቀደም ሲል የተነበበው ቃል የወደፊቱን ነገር የሚያመላክት የተስፋ ቃል ይመስል ነበር፣ አሁን ግን በኢየሱስ ከንፈሮች ላይ ብቻ “ይህ ዛሬ ተፈጽሟል" በማለት አሁን በተፈጸመው ሁኔታ ውስጥ በእውነት ሲገለጽ እናያለን።

ኢየሱስ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል” (ሉቃ 4፡18-19) በማለት ሊገናኘንና በአሁኑ ወቅት/ጊዜ በእርሱ ውስጥ እንድንሳተፍ የሚጠራንን አሁን ያለውን/ወቅታዊ የሆነውን እግዚአብሔር ይገልጽልናል። ይህ አሁን ያለው እግዚአብሔር ነው። ከኢየሱስ ጋር ይኖራል፣ የፊት ገጽታ አለው፣ ሥጋም ለብሱዋል። ራሱን ለመግለጽ ምቹ ወይም እንከን የለሽ ሁኔታዎች የማይጠብቀውን እና እንዲሁም ስለ ውጫዊ ገጽታው ብዙ የማይጨነቅ እግዚኣብሔር። ሁሉንም ሁኔታ በትክክለኛ እና በተገቢ ቦታ እንዲሆን የሚያደርገው ይህ የእግዚአብሔር ጊዜ ነው። በኢየሱስ አማካኝነት የወደፊቱ ተስፋ አሁን ተጀመረ እናም ይህ ህይወት ይሆናል።

መቼ? አሁን! ይህንን ነገር ስያዳምጡ የነበሩ ሰዎች ሁሉ የተጠሩ ወይም የተጋበዙ መስሎ አልተሰማቸውም ነበር። እርሱን በሚገባ የሚያውቁት እና የእርሱን እድገት በሚገባ የተመለከቱ፣ በጣም ለብዙ ጊዜ ሲጠባበቁት የነበረው ሕልማቸው ዛሬ እንደ ተፈጸመ የተነገራቸው ሁሉም የናዝሬት ነዋሪዎች በእርሱ ለማመን ዝግጁ አልነበሩም። በዚህም ብቻ አላበቁም በተጨማሪም “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” (ሉቃ 4፡22) በማለት ይመጻደቁ ነበር።

በእኛም ውስጥ ተመሳሳይ ነገር ሊኖር ይችላል። እግዚአብሔር እውን የሆነ እና ከእኛ ጋር ቅርበት ያለው፣ እውነተኛ እና ቅርብ የሆነ፣ ጎረቤት፣ ወዳጅ፣ ዘመድ በሆነ ሰው በኩል፣ በጣም አናሳ በሚባል ሰው በኩል ሳይቀር ይሠራል ብለን ሁልጊዜ አናምንም። ጌታ ቀለል ባለ መልኩ እና በተጣጣመ መልኩ በመንግሥቱ ውስጥ ከእርሱ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንሠራ እና በእጆቻችን ውስጥ የእርሱን እጅ በማስገባት እንድንሰራ ሊያደርገን ይችላል ብለን ሁልጊዜ አናምንም። “የእግዚአብሔር ፍቅር ተጨባጭ በሆነ መልኩ በታሪክ ውስጥ በሚከሰቱ ታላላቅ በሆኑ እና እንዲሁም አሰቃቂ በሚባሉ የከበሩ ሽንፈቶች ውስጥ ሳይቀር የእግዚኣብሔርን ፍቅር መለማመድ ይቻላል” (በነዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ በመስከረም 28/2005 ዓ.ም ላይ ካደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የተወሰደ) የሚለውን ማመን በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል።

እኛም አንዳንድ ጊዜ የናዝሬት ሕዝቦች የነበራቸው ዓይነት ባህሪ እንላበሳለን፡ እኛ ሩቅ መስሎ የሚታየውን አምላክ እንመርጣለን: ጥሩና፣ ለጋስ የሆነ አምላክ፣ ነገር ግን ከእኛ ሩቅ የሆነ እኛን የማያሰናክል አምላክ እንመርጣለን። ምክንያቱም ለእኛ በጣም ቅርብ የሆነ እና በእየለቱ የምንገናኛው የቅርብ ወዳቻችን፣ ወንድማችን የሆነው እግዚኣብሔር በአካባቢያችን በሚከሰቱ እለታዊ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት እንድንሳተፍ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የወንድማማችነት መንፈስን አጥበቀን እንድንጠብቅ ስለሚጠይቀን ነው። እግዚአብሔር ራሱን እንደ መላእክ ወይም በሌላ ለየት ባለ መንገድ ራሱን ለመግለጽ አለፈለገም፣ ነገር ግን የወንድማማችነት መንፈስ በሚገለጽበት እና ወዳጅነትን በሚያጠናክር መልኩ የታመነና የታወቀ ፊት ይዞ መገለጽን ፈለገ። እግዚአብሔር እውነት ነው፣ ምክንያቱም ፍቅር እውነት ስለሆነ፣ እግዚኣብሔር ተጨባጭ ነው፣ ምክንያቱም ፍቅር ተጨባጭ ስለሆነ። በእርግጥም ይህ "የፍቅር መገለጫ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች አንዱ ነው” (ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ በሚያዝያ 1/2006 ዓ.ም ካደረጉት ስብከት የተወሰደ)።

እኛም አንዳንድ ጊዜ ልክ እንደ የናዝሬት ሕዝቦች ተመሳሳይ በሆኑ አደጋዎች ውስጥ ላለመግባት በማሰብ በዚህም የተነሳ በማኅበረሰባችን ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን ተጨባጭ በሆነ ሁኔት ለመኖር እንፈራለን። እኛም ልክ እንደ ናዝሬት ሰዎች “እነዚህ ወጣቶች የማርያም እና የዮሴፍ ልጆች አይደሉም ወይ?፣ እነዚህ ወጣቶች የእከሌ እና የእከሊት ልጆች አይደሉም ወይ? እነዚህ ወጣቶች ሲያድጉ በዓይናችን አላየናቸውም ወይ? ያ እዚያ ጋር ያለው ደግሞ በኳስ የስፈሩን መስታወት በሙሉ ሲሰባብር የነበረ ልጅ አልነበረም ወይ? ማለት ይቀለናል ወይም ይቀናናል። በትንቢት አማካይነት የተወለደው እና የታወጀውን የእግዚኣብሔር መንግሥት በእኛ እለታዊ ኑሩ መመዘኛ ውስጥ በማስገባት እና ተመጣጣኝ ያልሆነ ትርጉም በመስጠት ለመረዳት የመሞከር ፈተና አለ። የእግዚኣብሔርን ቃል በእኛ መመዘኛ ውስጥ በማስገባት ለመተርጎም የሚደረጉ ሙከራዎች በእየለቱ ይካሄዳሉ።

የተወደዳችሁ ወጣቶች! የእናንተ ተልዕኮዎ፣ የእናንተ ጥሪ፣ ሌላው ቀርቶ ሕይወታችሁ እንኳን ሳይቀር የአሁኑን ጊዜ የሚያመልክት ሳይሆን የወደፊቱን መጻይ ጊዜ የሚያመልክት ነው፣ ብላችሁ በምታስቡበት ወቅቶች ሁሉ ይህ ሊያጋጥማችሁ ይችላል። ወጣትነት ማለት ልክ በአንድ የእንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ሆኖ እስከ ምትጠሩ ድረስ መጠበቅ ማለት መስሎዋችሁ ሊሰማችሁ አይገባም። እናም "በጊዜ" ውስጥ እኛ አዋቂዎች ወይም እናንተ ራሳችሁ ሁሉም ነገር አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና "በጥሩ ሁኔታ የተሞላ” በሚሆንበት ጊዜ ሁሉም ነገር ምንም ዓይነት መጥፎ ውጤት ሳያስከትል በተረጋጋ መልኩ የሚሄድ አድርገን እንቆጥራለን። በዚህም ተግባራችን ደስታ የሚመስል ነገር እንፈጥራለን። በዚህም ተግባራችን “እናንተ ተዘናግታችሁ እንድትኖሩ እናደርጋችኋለን” ማለት ነው፣ ዝም እንድትሉ ጥያቄዎችን እንዳታነሱ እናደርጋችኋለን። በዚህም ምክንያት ሕልሞቻችሁ እውን ሳይሆኑ እዚያው ባሉበት ቦታ ይቀራሉ፣ ሕልሞቻችሁ በዚያው ደርቀው የቀራሉ። ይህም የሚከሰተው የእናንተ ጊዜ ገና አልመጣም፣ ገና ሩቅት ነው ብለን ስለምናስብ እና እናንተ እንዲሁ እንድታስቡ፣ እናንተ አሁን ልጆች በመሆናችሁ የተነሳ ለወደፊቱ እንጂ ለአሁኑ ጊዜ ማሰብ አትችሉም የሚለውን አስተሳሰብ በውስጣችሁ እንዲሰርጽ ስላደረግን ነው።

ውድ ወጣቶች! እናንተ የወደፊቱ ሳይሆን የአሁኑ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። እርሱም እናንተን በማኅበረሰቦቻችሁ እና በየከተማዎቻችሁ ውስጥ የሚኖሩትን አያቶቻችሁን፣ የእድሜ ባለጸጋ የሆኑትን ሰዎች ሄዳችሁ እንድትጎበኙ፣ ከእነሩስ ጋር በጋራ በመቆም ያላችሁን ሕልም ያለፍርሃት በመናገር እና ጌታ ለእናተ ያለውን ሕልም እውን እንድታደርጉ ይጋብዛችኋል፣ ይጠራችኋልም።

ይህንን የምታደርጉት ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፣ ምክንያቱም ሐብታችሁ ባለበት ቦታ ሁሉ በእዚያው ልባችሁ ይኖራልና ነው (ማቴ 6፡21)። እናንተ በፍቅር የወደቃችሁለት ነገር በእናተ አዕምሮ ውስጥ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ነገር ሳይሆን ሁሉንም ነገር በእጅ አዙር ይነካል። በጠዋት እድትነሱ የሚያደርጋችሁ፣ ድካም ሲሰማችሁ ወደ ፊት በብርታት እንድትጓዙ የሚያደርጋችሁ፣ ልባችሁ ሲሰበር ደግሞ ያንን የተሰበረ ልብ በአድናቆት፣ በደስታ እና በምስጋና እንዴት መሙላት እንደ ምትችሉ የሚያስተምራችሁ ነው። እናንተ ተልዕኮ እንዳልችሁ ማወቅ እና ከተልዕኮዋችሁ ጋር ፍቅር እንድይዛችሁ ያስፈልጋል። ሁሉም ነገር ሊኖረን ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን የፍቅር ስሜት ከሌለን፣ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው፣ ምንም ነገር ሊኖረን አይችልም። ከእርሱ ጋር በፍቅር እንወድቅ ዘንድ እንዲረዳን ጌታን እንማጸነው።

በነዚህ ቀናት ውስጥ የማርያም ድምጽ በሎህሳስ መልኩ በዚህ ስፍራ እያስተጋባ ይገኛል። እርሷ በእግዚኣብሔር እና በእርሱ ቃል ኪዳን ቢቻ አላመነችም ነበር፣ ይህንንም ማድረግ ይቻል ነር፣ ነገር ግን እርሷ ያመነችሁ እግዚኣብሔርን ራሱ እና ለእርሱ ቃል “እነሆኝ” የሚል ምላሽ በመስጠት ለመጪው ጊዜ ሳይሆን አሁን ላለው እግዚኣብሔር ምላሽ ሰጥታ ነበር። እርሷ ተልዕኮ እንደ ተሰጣት ተሰምቱዋት ነበር፣ እንደ ተወደደች ሆኖ ተስምቱዋት ነበር፣ በዚህም የተነሳ ሁሉንም ነገር ለመቀበል ወሰነች።

በናዝሬት በምኩራብ ውስጥ እንዳደርገው ሁሉ ዛሬ ጌታ በመካከላችን ቆሞ “ዛሬ ይህ በጆሮዋችሁ የሰማችሁት ቃል ተፈጸመ” (ሉቃ 4፡21) ይለናል።

 

28 January 2019, 13:48