ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለታኅሳስ ወር የሚሆን የጸሎት ሐሳብ ያፋ ማድረጋቸው ተገለጸ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልእክት ይፋ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር መሰረት ለታኅሳስ ወር ቅዱስነታቸው ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ “እምነትን ለማስፋፋት በማሰብ የሚደርገውን አገልግሎት በጸሎት እንደግፍ” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ጸሎት እንዲደረግ ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

“እምነትህን በቃል ማስተላለፍ ከፈለክ በቅድሚያ በደንብ እና በጥንቃቄ ብዙ ማዳመጥ ይጠበቅብሃል” በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የኢየሱስን አብነት በመከተል እርሱ እንዳደረገው የሕዝቡን የአኗኗር ሁኔታ በመላበስ ከእነርሱ ጋር በመሆን የእግዚኣብሔርን ፍቅር እንዲቋደሱ እንዳደረገ ሁሉ እኛም በዚህ በተመሳሳይ መንገድ ላይ መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል።

“እመንት እንዲስፋፋ በመሥራት ላይ ላሉ ሰዎች ሁሉ መጸልይ ይገባል”፣ በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎች እመንትን በማስፋፋት ላይ የሚገኙባቸውን አከባቢዎች ባሕል በጠበቀ መልኩ፣ ትክክለኛውን እና ተገቢ የሆነ ቋንቋዎችን እንዲጠቀሙ፣ ባሕልን ማዕከል ያደርገ አስተምህሮ እንዲያደርጉ፣ ለሰዎች ጆሮ ሳይሆን ለሰዎች ልብ መናገር እንዲችሉ ከሁሉም በላይ ደግም የማዳመጥ ጸጋን በተላበሰ መልኩ ስብከተ ወንገልን ማስፋፋት ይችሉ ዘንድ በዚህ በታኅሳስ ወር ልንጸልይላቸው የገባል ካሉ በኋላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

06 December 2018, 15:18