ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከልዑካን ጋር ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከልዑካን ጋር 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ቤተክርስቲያን ሰብዓዊ ችግሮችን ለመፍታት ውይይት ለማድረግ ቁርጠኛ ናት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 04/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የክለሜንቲና የስብሰባ አዳራሽ በቫቲካን የተለያዩ ሀገራት መንግሥታት ልዑካን ጋር ባደርጉት ስብሰባ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ “ከቤተክርስቲያን ጋር በመወያየት መፍትሄዎችን ማቅረብ ያስፈልጋል” ማለታቸውን ለቫቲካን ዜና ከደረሰው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሰብዓዊ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ገንቢ የሆነ አወንታዊ ውይይት ለማድረግ ቁርጠኛ እንደ ሆነች ቅዱስነታቸው ጨምረው መናገራቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ይህንን የተናግሩት በቫቲካን የተለያዩ ሀገራትን መንግሥታትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ ልዑካን የሹመት ደብዳቤ በተቀበሉበት ወቅት እንደ ነበረ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እነዚህም በቫቲካን የተለያዩ ሀገራትን መንግሥታትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ ልዑካን የተውጣጡት ከሲውዘርላንድ፣ ከማልታ፣ ከባሃማስ፣ ከካፖ ቨርዴ፣ ከአይስላንድ፣ ከጋንቢያ፣ ከኳታር፣ ከእስቶኒያ፣ ከቱርክመንስታን እና ከግሬናዳ መሆናቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የቱርክመንስታን እና የግሬናዳ መግሥታት ልዑካን ቀደም ሲል ከቫቲካን ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያልነበራቸው ሀገራት እንደ ነበሩም ለመረዳት ተችሉዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ በቫቲካን የተለያዩ ሀገራትን መንግሥታትን በመወከል የሹመት ደብዳቤዎቻቸውን ላቀረቡት ልዑካን ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት እ.አ.አ በ2018 ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀበትን 100ኛ አመት ተዘክሮ ማለፉን አስታውሰው “የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ታሪካዊ ገጽታ ሁሉም የሰው ልጆች የጦርነትን ባህል እንዲያስወግዱ  እና በአሁኑ ወቅት በብዙ የዓለማችን ክፍሎች እየተከሰቱ የሚገኙ ግጭቶችን ለማስቆም ህጋዊ የሆኑ መፍትሄዎችን እንዲፈጉ የሚያስጠነቅቅ  እና የሚያስታውስ ክስተት ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው “እኛ ግን ከእዚያ አስቃቂ ክስተት የተማርነው ነገር ያለ አይመስለኝም” ብለዋል። ከእርሳቸው በፊት የነበሩት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት በነዴክቶስ 16ኛ ይህንን የመጀመርያውን የዓለም ጦርነት አስመልክቶ “ትርጉም የሌሽ ጭፍጨፋ” በማለት ጦርነቱን ገልጸው እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ዓለማችን ካሳለፈችው አሰቃቂ ከሆኑ ሁለት የዓለም ጦርነቶች ጥለውት ያለፉትን መጥፎ ጠባሳ በማስታወስ በዚህ ባለንበት 20ኛው ክፍለዘመን የሚገኙ መንግሥታ የጦር መሳርያን ለመታጠቅ የሚያደጉትን እሽቅድድም በመተው፣ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት በዓለም ዙርያ ሰላም እንዲረጋገጥ መስራት እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በተለይም ደግም ሰብዓዊ መብቶችን በተመለከተ በዓለማቀፍ ደረጃ የተረቀቁ የሰብዕእዊ መብቶችን የተመለክቱ ሕጎች ከተረቀቁ እነሆ 70 አመታት ማለፋቸውን ያስትወሱት ቅዱስነታቸው በአሁኑም ወቅት ቢሆን ከ70አመታት በኋላ በዓለም ዙርያ የሚኖሩ ሕዝቦች ሰብዕእዊ መብታቸው ሙሉ በሙሉ እንዳልተከበረ አስታውሰው የሰው ልጆችን ሰብዕእዊ መብት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ለአዳዲስ ተሹዋሚ ልዑካን መልእክት አስተላፈዋል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማንኛውም አይነት ግጭቶች በሰላማዊ መልኩ ይፈቱ ዘንድ እና የሰው ልጆች ሰብዓዊ መብት ይረጋገጥ ዘንድ የበኩላን አስተዋጾ ማድረጓን አጠናክራ ትቀጥላለች በማለት በቫቲካን የተለያዩ ሀገራትን መንግሥታትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ ልዑካን የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለም ደግም ገንቢ የሆኑ ውይይቶችን በማድረግ ችግሮችን የመፍታት ባሕል በመላው ዓለም ይጎለበት ዘንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበኩሉዋን አስተዋጾ ማድረጓን አጠናክራ እንደ ምትቀጥል ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

13 December 2018, 15:54