ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊ ዜና እረፍት በተመለከተ የሐዘን መግለጫ መልእክት አስተላለፉ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊ ዜና እረፍት በተመለከተ የሐዘን መግለጫ መልእክት አስተላለፉ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊ ዜና እረፍት በተመለከተ የሐዘን መግለጫ መልእክት አስተላለፉ

ወንጌልን ዘወትር ስበኩ አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ ቃላትን ተጠቀሙ”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የቀድሞ የአሜርካ ፕሬዚደንት የነበሩት የጆርጅ ቡሽ አባት እና 41ኛ የአሜርካ ፕሬዚደንት የነበሩት ቡሽ ቀዳማዊ ዜና እረፍ በተመለከተ የሐዘን መግለጫ መልእክት ለአሜርካ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት እና ለጆርጅ ቡሽ ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ መልእክት በቴለግራም ማስተላለፋቸው ተገለጸ። ቡሽ ቀዳማዊ በኅዳር 26/2011 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ብሔራዊ ካቴድራል የፍትሃት ጸሎት እንደ ተደረገላቸው የሚታወቅ ሲሆን በዚህ የፍትሃት ጸሎት ላይ ባራክ ኦባማን እና ቢል ክሊንተንን ጨምሮ ለየት ባለ ሁኔታ 4 የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች መገኘታቸው ታውቁዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቡሽ ቀዳማዊ ዜና እረፍት የተሰማቸውን ሐዘን የሚገልጽ የቴለግራም መልእክት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ በሆኑት በካርዲናል ፕትሮ ፓሮሊን በኩል ማስተላላፈቻውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው በሁኔታው ማዘናቸውን እና በአሜሪካ ከሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጋር በጋራ በመሆን የቡሽ ቀዳማዊ ነፍስ ሁሉን በሚችል በእግዚኣብሔር ምሕረት ከላላ ውስጥ ይቀመጥ ዘንድ  ጸሎት እንደ ሚያደርሱም መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የአሜሪካ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚደንት የሆኑት ካርዲናል ዳኒኤል ዲ ናርዶ በበኩላቸው በጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን በአሜርካ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባሄ ስም የተሰማቸውን ሐዘን ማስተላለፋቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ካርዲናል ዳኒኤል ዲ ናርዶ በመልእክታቸው ጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊን “ታላቁ ሰው” በማለት እንዳሞካሹዋቸው ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ለሰላም ግንባታ የሚሆኑ የመሸጋገሪያ ድልድዮችን በመገንባት እና ሀገራችን አሜሪካ ነጻነቷ የተረጋገጥ እንዲሆን ባላማቋረጥ በቁርጠኝነት ማገልገላቸውን ገለጸው በዚህም ተግባራቸው በአሜሪካ የሚገኙ የብዙሃኑን ባልትዳሮች፣ የቤተሰብ መሪዎች እና የሀገር አፍቃሪዎችን ቀልብ ስበው ያለፉ ፕሬዚደንት እንደ ሆኑም በሐዘን መግለጫ መልዕክታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊ አሜሪካን እ.አ.አ ከ1989 እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ ያስተዳድሩ የአሜሪካ 41ኛ ፕሬዚደንት እንደ ነበሩ ከደረሰን መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በ94 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊ 264ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከነበሩት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ወቅት የነበሩ 41ኛ የአሜርካ ፕሬዚዳንት እንደ ነበሩ የሚታወስ ሲሆን ሁለቱም በሕይወት ዘመናቸው ለበርካታ ጊዜያት ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው የሚታወስ ሲሆን ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊ ቫቲካንን ሁለት ጊዜ መጎብኘታቸውም ይታወሳል። ፕሬዚዳንት ጆርጂ ዳብሊዩ ቡሽ ስለ አባታቸው ጆርጅ ቡሽ ቀዳማዊ ስያስታውሱ “"ወንጌልን ዘወትር ስበኩ አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ ቃላትን ተጠቀሙ” በማለት አባታቸው አዘውትረው ይናገሩ እንደ ነበረ መግለጻቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

06 December 2018, 15:32