ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 25/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው አስተንትኖ ካደርጉ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን የብስራተ ገብሬል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት በቅርቡ በግብጽ በሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ በአሸባሪዎች በተፈጸመው ጥቃት እጅግ ማዘናቸውን ገልጸው ክርስቲያን በመሆቸው ብቻ ለዚህ አሰቃቂ ጥቃት ተዳርገው ሕይወታቸውን ያጡ ክርስቲያኖችን በጸሎቴ አስታውሳቸዋለው፣ በአደጋው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ያጡ ሰዎችን  እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታጽናናቸው ዘንድ እማጸናታለሁ ብለዋል።

“እዚህ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰባችሁ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና በአጠቃላይ በዚህ ስፍራ ለተገናችሁ ሰዎች ሁሉ ሰላምታዬን አቀርባለሁ” ያሉት ቅዱስነታቸው እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ” ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ ሳምንታዊ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

04 November 2018, 16:04