2018-01-12 Haiti scuole di strada 2018-01-12 Haiti scuole di strada 

ሰው የማወቅና የመማር መብቱ ከተነፈገ በምንም መልኩ ሙላት ያለው ነፃነት እንደማይኖረው ተገለፀ።

ሰው ትምህርት የማግኘት መብቱ ወይም ነፃነቱ ከተነፈገ የራሱን ዓላማና ዕጣ ፈንታ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሙሉ ነፃነት ኣይኖረውም።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ፣ ቫቲካን

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ዛሬ በትዊተር ወይም ማኅበራዊ መገናኛ ድህረ ገፃቸው በየዓመቱ መስከረም 8 ቀን የሚከበረውን የዓለም ኣቀፍ የማንበብና የመፃፍ ቀን ምክንያት በማድረግ የሰው ልጅ የማወቅ ወይም የመማር መብቱኝ ሊነፈግ የማይገባውና መሠረታዊ መብቱ መሆኑን ኣስታወሱ። በዚሁ በማኅበራዊ መገናኛ ድህረ ገፃቸው በሄይቲ መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋሞች በቀን ከ 800 በላይ ሕፃናትን የመማር ወይንም ትምህርት የማግኘት መብታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ያለውን እንቅስቃሴ ሲሞኔ ሳርቺያ ከሚባል የኣንድ የሄይቲ ዜጋ የምስክርነት ቃል ከሰሙ በኋላ መሆኑን የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ ጋብሪኤላ ቼራሶን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

ሰው ትምህርት የማግኘት መብቱ ወይም ነፃነቱ ከተነፈገ የራሱን ዓላማና ዕጣ ፈንታ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሙሉ ነፃነት ኣይኖረውም ብለው የተናገሩት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 8 ቀን 1966 በዩኔስኮ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የማንበብ ቀንን ምክንያት በማድረግ ሲሆን በዚሁ ረገድ የተሰማሩትን ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች መንሥታዊ የሆኑና ያልሆኑ ድርጅቶችን ማጠናከርና ማነቃቃትን እንደሚያስፈለግ “ኣት ፖንትፊክስ” (@Pontifex) በተሰኘው በዚሁ ማኅበራዊ መገናኛ ድህረ ገፃቸው አማካኝነት በትናንትናው ዕለት ኣስተላልፈዋል።

ማንበብና መጻፍ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብት መሆኑ፤

በፖርት ኣው ፕሪንስ በዋና ከተማው በኣንድ በዓለማችን ካሉ ትልቅ የብረታብረት ማምረቻ የኣንድ ክፍል ኃላፊ ሆኖ የሚሰራው ሲሞኔ ሳርቺአ ቼስቪ ላቫቲካን ሬዲዮ እንዳስረዳው እና በሄይቲ ያለዉን የመማር እና ማስተማር ልምዱን እንዳጋራው በብዙ ኣገሮች በተለይም ከ800 ሚልዮን በላይ የሚሆኑት ሕዝቦች በተለይም ሴቶችና ሕፃናት ዛሬም መሠረታዊ የሆነው የትምህርት የኣካባቢ የሠላምና የመሠረታዊ ዕድገት መብቶቻቸው ጥያቄ ውስጥ የወደቁ መሆናቸው ተገልጿል።

አለኣግባብ ሕግን መተላለፍና ባርነትን በተመለከተ፤

ሲሞኔ ሳርቺአ ላቫቲካን ሬዲኦ ባልደረባ እንደገለፀው በሄይቲ የሚገኙ ሕፃናት ወደ ትምህርት ቤት መሄዳቸው ኣእምሮቸው በትምህርትና በማኅበረሰባዊ ባሕሎችና እሴቶች መዳበሩ ብቻ ሳይሆን ከኣንዳንድ ኣላስፈላጊ የጉልበት ብዝበዛዎች ሕገ ወጠ ጥሰቶች ባርነቶችና የመሳሰሉት ኣደጋዎች ሁሉ እንዳያገኛቸው ፍቱንና የተመቻቸ ቦታ ነው ሲል ያሳቡን ገልጿል። እንደ ሄይቲ ባሉ ሞትና ድህነት የተፈትሮ ኣደጋዎችና የተለያዩ ችግሮች በሰፊው በሚንፀባረቁበት ሃገር የሕፃናቱ በትምህርት ቤት መዋል መሠረታዊ እውቀትና የተለያዩ ለዕድሜአቸው የሚመጥን የሕፃናት ጨዋታዎችን እንዲያገኙ እንደሚረዳ ኣብራርቷል።

የመንግሥት ሥራ፤

የሄይቲ መንግሥት በቀጠናው ላይ በተድጋጋሚ በሚከሰቱ የተፈጥሮ ኣደጋዎችና የመሬት መንቀጥቀጦች በተፈጠሮ ዙሪያ እድለኛ ካለመሆኗም በላይ መንግሥትም በመማር ማስተማር ሂደትና ኣዝማማሚያ ላይ ያለው ኣቋም ለዘብ ያለ በመሆኑ ምክንያት በሄይቲ ያለው የተማረ የሰው ቁጥር ኣምብዛም እንዳልሆነ ኣስረድቷል።

በቼስቪ የትምህርት ማዕከል 800 ሕጻናት በተሻለና ቢያንስ መሠረታዊ ፍላጎቶችን ባሟላ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ

ለመማር ማስተማሩ ሂደት በቀን ውስጥ ወደ ቼስቪ የትምህርት ማዕከል የሚመጡት የኣዲስ ተማሪዎች ቁጥር ወደ 400 የሚጠጋ ሲሆን እነዚህም ተማሪዎች ከመዋዕለ ሕፃናት አስከ መካከለኛ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ሲሆኑ ለነዚህም ተማሪዎች በየዕለቱ በትምህርት ቤቱ የሚዘጋጅላቸውን ምግብ እዛው እንደሚመገቡ ታውቋል። ማዕከሉ በአካባቢው የሚኖሩ ሕፃናትን ለመንከባከብ እና ተጨማሪ የትምህርት ድጋፍ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግና በዚህም መልኩ የሚረዱት ሕፃናት ቁጥራቸው ከ 800 በላይ መሆኑን ጠቅሶ ይህ በቼዝቪ የሚገኘው ብቸኛ ማዕከል በኣካባቢው ለሚገኘው ከግማሽ ሚሊዎን በላይ ለሚሆነው ሕዝብ ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ቢገኝም ይህ ማዕከል በኣካባቢው የሚገኝ ብቸኛ ማዕከል በመሆኑ የሁሉንም ፍላጎት ለብቻው ለማሟላት እንድሚያዳግተው ኣስረድቷል።

08 September 2018, 17:18