ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ 25ኛው የውጭ አገር ሐዋርያዊ ጉብኝት።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ 25ኛው የውጭ አገር ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተገለጸ።

ቅዱስ አባታችን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከኢጣሊያ ውጭ የሚያደርጉትን 25ኛ ዙር ሐዋርያዊ ጉብኝት ምክንያት በማድረግ የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ሦስት የባልቲክ አገሮች እነርሱም ሊቷኒያ፣ ሌቶኒያንና ኤስቶኒያን መሆናቸው ታውቋል። ለእነዚህ አገሮች ምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክት የሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ዓላማ የአገሮቹ ሕዝቦች ነጻነትን ያገኙበትን 100ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓልን በጋራ ለማክበር እንደሆነ ገልጸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከቅዳሜ መስከረም 11-15 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ ወደ ባልቲክ አገሮች የሚያደርጉትን የአራት ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፣ በጨለማ፣ በአመጽና በመከራ ዘመናትም ቢሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእያንስዳንዳችን የተሰጠ የነጻነት ተስፋ ክብርን በማግኘት የበለጠ ያድጋል እንጂ አይጠፋም ብለዋል። በመሆኑም በጋራ ሆነን ፍትሃዊና የወንድማማችነትን መንፈስ የተላበሰ ሕብረተሰብን መገንባት ይስፈልጋል ብለዋል።

ይህ ነጻነት ዘላቂነት እንዲኖረው ለማድረግ እንክብካቤ ሊደረግለት እንደሚገባ አሳስበው ወደ ዛሬው ነጻነት ለመድረስ ተጋድሎን ያደረጉትንና መስዋዕትነት የከፈሉትን በሙሉ አስታውሰዋል።

20 September 2018, 16:00