ቅዱስነታቸው በሳናታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ ቅዱስነታቸው በሳናታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በደብሊን ያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በሰላም በመጠናቀቁ ምስጋና ለማርያም አቀረቡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነስኮስ ከነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 20/2010 ዓ.ም በደብሊን ያደርጉትን 24ኛው ሐዋርያዊ ጉኝት አጠናቀው በትላንትናው ምሽት ሮም በሰላም መመለሳቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እንደ ተለመደው ቅዱስነታቸው ማንኛውንም ሐዋሪያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው በፊት እና ማነኛውንም ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሮም በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ እንብርት ላይ በሚገኘው በማሪያም ስም ከተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በአውሮፓ አህጉር በትልቅነቱ እና በጥንታዊነቱ በሚታወቀው ሳንታ ማሪያ ማጆሬ በመባል በሚታወቀው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገኝተው ለማርያም  ምስጋና ማቅረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በሳንታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ ውስጥ በሚገኘው ባላቲን ቋንቋ “Salus Populi Romani” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም የሮም ከተማ ሕዝቦች አዳኝ ወይም ጠባቂ በመባል የምታወቀው እና በአብዛኞቹ  የሮም ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን የሚያሳየው ምስል ስር በመገኘት የምስጋና ጸሎት እንደ ሚያደርሱ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ከነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 20/2010 ዓ.ም በደብሊን ያደርጉትን 24ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው በትላንትናው ምሽት ወደ ሮም ከተማ መመለሳቸውን ቀድም መገለጻችን የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለትም በነሐሴ 21/2010 ዓ.ም በሳንታ ማርያ ማጆሬ ባዚልካ ተገኝተው ማርያም ስላደረገችላቸው ጥበቃ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና ማቅርባቸውን ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
27 August 2018, 15:21