ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮስ እመንት ሊጀምር የሚገባው ከነጻናት ስሜት ነው

እመንት ሊጀምር የሚገባው ከነጻናት ስሜት እንጂ ከግዴታ ሊሆን አይገባውም

ር.ሊ.ጳ.ፍራንቸስኮስ እመንት ሊጀምር የሚገባው ከነጻናት ስሜት እንጂ ከግዴታ ሊሆን አይገባውም” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

በእዚህ መሰረት በዛሬው እለት ማለትም በሰኔ 20/2010 ዓ.ም ያደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ትኩረቱን ያደረገው በኦሪት ዘዳግም በምዕራፍ 4፡32-35 ላይ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የእግዚእብሔር ፍቅር ከሕግ በላይ ሆኖ ሲታይ ትርጉም ይጣል፣ እመንት ሊጀምር የሚገባው ከነጻናት ስሜት እንጂ ከግዴታ ሊሆን አይገባውም” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በእለቱ የተነበበው የምጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ . . .

እግዚአብሔር አምላክ ነው

እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ቀን ጀምሮ እናንተ ከመኖራችሁ በፊት ስለ ነበረው የቀድሞ ዘመን ጠይቁ፤ ከአንዱ የሰማይ ጫፍ እስከ ሌላው የሰማይ ጫፍ ድረስ ጠይቅ፤ እንደዚህ ያለ ታላቅ ነገር ከቶ ተደርጎ ወይስ እንደዚህ ዐይነት ነገር ከቶ ተሰምቶ ያውቃልን? ከእሳት ውስጥ እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ድምፅ እንደ እናንተ የሰማና በሕይወት የኖረ ከቶ ሌላ ሕዝብ አለን? አምላካችሁ እግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ) በዐይናችሁ እያያችሁ ለእናንተ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ በፈተና፣ በታምራዊ ምልክቶችና በድንቆች፣ በጦርነት፣ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ወይም በታላቅና በአስፈሪ ሥራዎች ከሌላ ሕዝብ መካከል አንድን ሕዝብ የራሱ ለማድረግ የቻለ አምላክ አለን? እግዚአብሔር እርሱ አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኑን፣ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን ታውቁ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታዩ ተደረገ (ኦሪት ዘዳግም  4፡32-35)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው ዕለት (ሰኔ 20/2010 ዓ.ም)  በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እናጋብዛለን።

የዚህ ዝግጅት አጠናቃሪ-መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

“በእግዚኣብሔር ትዕዛዛት ላይ የጀመርነውን አስተምህሮ ዛሬውም በመቀጠል ቀደም ሲል እንዳልነው እነዚህን የእግዚኣብሔር ትዕዛዛት ከምንላቸው ይልቅ የእግዚኣብሔር ሕዝብ በደንብ ወደ ፊት ለመጓዝ ያስችለው ዘንድ እግዚኣብሔር የሰጠን በመሆናቸው የተነሳ የእግዚኣብሔር ቃላት ብለን ብንጠራቸው ይሻላል፣ በእዚህ አርእስት ላይ የጀመርነውን አስተምህሮ ዛሬ እንቀጥላለን። “ዐስርቱ ቃላት” የሚጀምሩት “ከግብፅ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ” (ዘጸዐት 20፡2) በማለት ይጀምራል። ይህ አጀማመር ከትክክለኛ ህግ ውጭ ያለ ነገር ይመስላል። ነገር ግን እንዲህ ነበር የተከሰተው። ለምንድን ነው እግዚአብሔር ይህንን ስለራሱ ማንነት እና ሰለ ከባርነት መውጣት የሚገልጸውን አዋጅ የተናገረው? ይህንንም ያደረገው ሕዝቡ የቀይ ባሕርን እንዲያቋርጥ ካደረገ በኃላ ነበር፣ የእስራኤል አምላክ በቅድሚያ ያድናል ከእዚያም በእርሱ እንድንታመን ይጠይቀናል። ይህም ማለት “ዐስርቱ ቃላት” የሚጀምሩት እግዚኣብሔር በቅድሚያ ለሕዝቡ ርኅሩ መሆኑን ካሳየ በኃላ ነው። እግዚኣብሔር አስቀድሞ ሳይሰጠን እኛ እንድንሰጠው አይጠይቀንም። የእኛ አባት እንዲህ ነው የሚያደርገው የእኛ አባት እንዲህ ደግ ነው። እናም “እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ” ብሎ የተናገረው የመጀመሪያው አዋጅ አስፈላጊ መሆኑ ይገባናል። ይህም እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር ያለውን ግንኙነት ያሳየናል። እግዚኣብሔር ከእኛ ርቆ የሚገኝ አምላክ አይደለም፣ “የአንተ አምልካ ነኝ” ይለናል። ይህ የዐስሩን ቃላት ምንነት ይገልጽልናል፣ ክርስቲያን እንዴት መጓዝ እንደ ሚኖርበትም ይገልጻል ምክንያቱም በተመሳሳይ መልኩ ኢየሱስ “አባቴ እንደ ወደደኝ እኔም ወደድኩዋችሁ” በማለቱ የተነሳ ነው። ክርስቶስ በአብ የተወደደ ሲሆን በተመሳሳይ ፍቅር እኛን ይወደናል። እርሱ የሚጀምረው ከራሱ ሳይሆን ከአባቱ ነው። ብዙን ጊዜ የምንሰራቸው ስራዎች ውጤታማ የማይሆኑበት ምክንያት በምስጋና ሳይሆን በራሳችን ጥረት እንደተደረገ በማሰብ ስለምንጀምር ነው። ከራሱ የሚጀምር ሰው የት ሊደርስ ይችላል? የሚደርሰው ራሱ ጋር ብቻ ነው። መንገድ ለመክፈት አቅሙ አይኖረውም። ወደ ራሱ ይመለሳል። ይህም የራስ ወዳድነት ባህሪይ ያንጸባርቃል፣ ሕዝቡም በማፈዝ “ያ ሰው ‘እኔ፣ ለእኔ በእኔ ከእኔ በማለት ከራሱ ይወጣል ወደ ራሱ ዞሮ ይመለሳል” በማለት ያፌዙበታል። ከሁሉም በላይ የክርስትና ሕይወት ለጋስ የሆነው እግዚኣብሔር የምስጋና ምላሽ ነው። ክርስቲያኖች የግል ተመክሮዎቻቸውን ወደጎን በመተው የእኛ የሁላችን አምላክ የሆነው እግዚኣብሔር የሰጠንን ኃላፊነት መወጣት ይኖርብናል። እኔ ይህንን ያንን እነዚያን ነገሮች መስራት ማከናወን ይኖርብኛል ማለት ግዴታ ይመስላል። በእዚህ ረገድ አንድ ነገር ይቀረናል፣ የእዚህ ግዴታ መስረቱ ምንድነው? የእዚህ ተግባር ስር መሰረቱ ሊሆን የሚገባው አስቀድሞ የሚለግስ በመቀጠል የሚያዘው የእግዚኣብሔር ፍቅር ነው። ግንኙነት ከመጀመራችን በፊት ትዕዛዝ ማስቀደም በእምነት ጉዞ ላይ ወደ ፊት እንድንጓዝ አይረዳም። ነጻ መውጣቱን በቅድሚያ ሳንነግረው በተቃራኒው ግዴታዎችን፣ ቁርጠኝነትን ማሳየት እንደ ሚገባው፣ ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት በመግለጽ አንድ ወጣት ለሆነ ክርስቲያን ለመሆን የሚፈልግ ሰው ይህንን ግዴታ በማስቀደም ብንጀምር እንዴት ክርስቲያን ለመሆን ሊነሳሳ ይችላል? ነገር ግን ክርስቲያን መሆን ማለት ወደ ነጻነት መጓዝ ማለት ነው። ዐስርቱ ትዕዛዛት ከራስ ወዳድነት መንፈስ ነጻ እንድንሆን ይረዱናል፣ ምክንያቱ በእነርሱ ውስጥ ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚያደርገን የእግዛኢብሔር ፍቅር በመኖሩ የተነሳ ነው። የክርስትና እመንት ትምህርት ወይም ህነጻ በአስገዳጅ ሁኔታዎች የሚጀምር አይደለም፣ ደኽንነትን መቀበል ማለት ነው፣ እግዚኣብሔር እንዲወደን መፍቀድ ማለት ነው፡ በቅድሚያ ቀይ ባህርን ማቋረጥ ከእዚያን በኃላ ወደ ሲና ተራራ መጓዝ። በቅድሚያ ነጻ መውጣት ወይም መዳን፡ እግዚኣብሔር በቅድሚያ ሕዝቡን በቀይ ባሕር ውስጥ አድኑዋቸው ያሻግራቸዋል ከእዚያን ወደ ሲና ተራራ በመውሰድ ምን ማድረግ እንደ ሚኖርባቸው ይነግራቸዋል። እነዚህ ሕዝቦች እነዚህን ትዕዛዛት መፈጸም እንዳለባቸው በሚገባ ያውቃሉ፣ ምክንያቱም የዳኑት በሚወዳቸው በአባታቸው እንደ ሆነ በሚገባ ስለሚያውቁ ነው። ምስጋና ማቅረብ በመንፈስ ቅዱስ የተጎበኘው የልብ ባህሪይ ነው፣ እግዚኣብሔርን በሚገባ ለመታዘዝ በቅድሚያ እርሱ ያደርገልንን ነግሮች ማስታወስ ያስፈልጋል። ቅዱስ ባሲሊዮስ እንደ ሚለው “እነዚያን የተቀበሉዋቸውን መልካም የሆኑ ስጦታዎች የማይረሱ ሰዎች በጥሩ መልካምነት እና በሁሉም የፍትህ ሥራ ላይ እነዚያን ስጦታዎች ያንጸባርቃሉ” ይለናል። እግዚኣብሔር ይህንን ከእኛ ይፈልጋል፣ እርሱ ያደረገልንን በጣም ብዙ መልካም ነገሮችን እንድናስታውስ ይፈልጋል። ሰማያዊ አባታችን ለእኛ ምን ያህል መልካም የሆነ አምላክ ነው? አሁን ግን ሁላችሁንም አንድ አትንሽ እንቅስቃሴ በዝምታ እንድታደርጉ እጠያቅችኃለሁ፣ ሁላችሁም መልሱን በልባችሁ ያዙት። አምላክ ለእኔ ምን ያህል መልካም የሆኑ ነገሮችን አድርጎልኛል? ይህ እኔ ለእናንተ ያቀርብኩላችሁ ጥያቄ ነው። እያንዳንዳችን በዝምታ እንመልስ። ይህ እግዚኣብሔር እኛን ነጻ ከማውጣቱ ጋር ይመሳሰላል። እግዚኣብሔር ብዙ መላካም የሚባሉ ነገሮችን አድጎልናል ነጻም አውጥቶናል። ምናአላባት አንዳንድ ሰዎች እግዚኣብሔር ነጻ እንዳወጣቸው የማይሰማቸው ወይም የማያስታውሱ ሰዎች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። ሊያጋጥም የሚችል ጉዳይ ነውና። ይህም ጉዳይ የተከሰተው ምንላባት ወደ ውስጣችሁ ስትመለከቱ አስገዳጅ የሚመስሉ ነገሮችን ብቻ በመመልከታችሁ ፣ የልጅነት መንፈስ ሳይሆን የአንድ አገልጋይ ስሜት ዓይነት ሰለተሰማችሁ ሊሆን ይችላል። ታዲያ በእዚህ ረገድ ምን ማድረግ ይኖርብናል? የእግዚኣብሔር ምርጥ ሕዝብ እንዳደርገው ማድረግ ይኖርብናል። የኦሪት ዘጸዐት መጽሐፍ እንደ ሚለው “ከብዙ ዓመት በኋላ፣ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያንም በባርነት ከደረሰባቸው ግፍ የተነሣ ይጮኹ ነበር፤ ከባርነት ቀንበር ለመላቀቅ ያሰሙት ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ደረሰ። እግዚአብሔርም የጩኸታቸውን ሲቃ ሰማ፤ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አሰበ። እግዚአብሔርም እስራኤላውያንን ተመለከተ፤ ስለ እነርሱም ገደደው” (ኦዘጸዐት 2፡23-25) እንደ ሚለው እግዚኣብሔር ለእኛ ያስባል። የእግዚኣብሔር ነጻ የማውጣት ተግባር የተከናወነው ሕጋጋቱን ሳይሰጥ በፊት ነበር። ትዕዛዛቱን ከመስጠቱ በፊት የእዚቡን ሮሮ አስቀድሞ በመስማት ነጻ ያወጣቸዋል፣ ከእዚያም ምን ማድረግ እንደ ሚኖርባቸው ለማስተማር ሕጉን ይሰጣቸዋል። እኛ ራሳችንን ማዳን አንችልም፣ ነገር ግን መዳን የምናገኘው ወደ እርሱ በምናቀርበው “ጌታ ሆይ አድነኝ፣ ጌታ ሆይ መነግድህን አስተምረኝ፣ ጌታ ሆይ ራራልኝ፣ ጌታ ሆይ ደስታን ስጠኝ” በማለት ወደ እርሱ በምንጮኽበት ወቅት እርሱ መልስ ይሰጠናል። ነገር ግን እኛም በፊናችን ከራስ ወዳድነት መንፈስ፣ ከኃጢኣት፣ ጠፍሮ ከያዘን ባርነት ለመላቀቅ መዘጋጀት ይኖርብናል። የእዚህ ዓይነት ጮኸት በጣም አስፈላጊ የሆነ ጩኸት ነው፣ እንደ ጸሎትም ይቆጠራል፣። በሕይወታችን ውስጥ ነጻ ያልወጡ በጣም ብዙ ነገሮች ይገኛሉ። “አድነኛ ነጻ አውጣኝ” ብለን ልንጠይቀው ይገባል። የእዚህ ዓይነቱ ጸሎት ደግሞ በጣም መልካም የሚባል ጸሎት ነው። እግዚኣብሔር እንደ እነዚህ ዓይነት ጩኸት እንድናቀብለት ይፈልጋል፣ ከተያዝነበት ከታሰርንበት ሰንሰለት ለመውጣት መፈለጋችንን ሊሰማ ይፈልጋል። ስእዚህ በቀጣይነት ወደ እርሱ መጮኽ ይኖርብናል ማለት ነው። እግዚኣብሔር በሕይወታችን ውስጥ ያደገውን ነገር በማስታወስ ወደ እርሱ ምስጋና ማቅረብ ይኖርብናል። ይህም በጣም መልካ የሚባል ነገር ነው። በሕይወታችን ውስጥ ስላደረገው እና እያደርገ ሰለሚገኘው ነገር እግዚኣብሔር ሁል ጊዜ የተመሰገነ ይሁን። አሜን! አመሰግባለሁ። ”

27 June 2018, 14:52