ር.ሊ.ቃ. ፍራንቸስኮስ፡ ከሮም ሀገረ ስብከት ካህናት ጋር በግንቦት 6/2010 ዓ.ም ተገናኙ ወቅት ር.ሊ.ቃ. ፍራንቸስኮስ፡ ከሮም ሀገረ ስብከት ካህናት ጋር በግንቦት 6/2010 ዓ.ም ተገናኙ ወቅት  

ር.ሊ.ቃ. ፍራንቸስኮስ፡ ከሮም ሀገረ ስብከት ካህናት ጋር ተገናኙ

ር.ሊ.ቃ. ፍራንቸስኮስ፡ መንፈሳዊ ዝለት ወይም መንፈሳዊ በሽታዎችን ማስወገድ ይገባል

ር.ሊ.ቃ. ፍራንቸስኮስ፡ ከሮም ሀገረ ስብከት ካህናት ጋር ተገናኙ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 6/2010 ዓ.ም ከሮም ሀረስብከት ካህናት ጋር በሮም ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ዩሐንስ ዘ ላቴራን ቤተክርስቲያን ውስጥ ተገናኝተው በተለያዩ ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ ያደርጉት ንግግር ትኩረቱን አድርጎ የነበረው መንፈሳዊ ዝለት ወይም ደግሞ መንፈሳዊ በሽታዎች በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ ጭብጥ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ቁምስናዎች ውስጥ ቅዱስ ወንጌል በማብሰር ሂደት ውስጥ የሚታየውን ድክመት እና ተነሳሽነት የማጣት ስሜት ከግምት ያስገባ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህንን ድክመት ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ የማነቃቂያ ተግባሮች እንዲሰሩ የሚያሳስብ ንግግር እንደ ሆነ የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ የሆነችው በኔዴታ ካፔሊ ካጠናከርችው ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

አንድ የሕክምና ባለሙያ የታካሚውን የጤና ሁኔታ በማጥናት ለታካሚ ፈውስ ማስገኘት የሚችሉ መፍትሄዎች እንደ ሚያፈላልግ ሁሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እራሳቸው በበላይነት በሚመሩት የሮም ሀገረ ስብከት ችግር እና ተግዳሮት በጥልቀት እንዲጠና ካደርጉ በኃላ ለእነዚህ ተገኙ ለተባሉት ድክመቶች እና ተግዳሮቶች መፍትሄ ለምሰጠት በማሰብ ያደርጉት ንግግር እንደ ሆነ የገለጹት የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ በኔደታ ካፔሊ ቅዱስነታቸው በግንቦት 06/2010 ዓ.ም በሮም ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ዩሐንስ ዘ ላቴራን ባዚሊካ ከሮም ሀገረ ስብከት ካህናት ጋር በነበራቸው ቆይታ በአሁኑ ወቅት ቅዱስ ወንጌልን በማብሰር ሂደት ውስጥ በሮም ከተማ የሚገኙ ቁምስናዎች እያጋጠማቸው የሚገኙትን ተግዳሮቶች እና ድክመቶች ከግምት ባስገባ መልኩ በእዚያ ከተገኙ ካህናት ጋር በውይይት መንፈስ የተደርገ ቆይታ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ ከተመረጡ በኃላ በእነዚህ አምስት አመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ሦስት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳኖችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን እነዚህም Evangelii gaudium  በአማሪኛ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ” የሚለው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በእዚህም ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ላይ መሆን እንዳለባት እና ቤተ ክርስቲያን ሐዋሪያዊ ተልዕኮዋን ለማከናውን እና ሰዎችን ወደ እግዚኣብሔር ለመመለስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መሄድ እንዳለባት የሚያሳስብ ቃለ ምዕዳን በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ amoris laetitia በአማሪኛው “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ያስታሙት ቃለ ምዕዳን በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር፣ በቤተሰብ ውስጥ ስለሚታዩ ተግዳሮቶች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለቤተሰብ ማድረግ ሰለሚጠበቅባቸው ሐዋሪያዊ እንክብካቤ የሚያወሳ ድህረ ሲኖዶስ አዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል።

በመጨረሻም በቅርቡ “Gaudete ed Exsulate” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “ደስ የበላችሁ ሕሴት አድርጉ” በሚል አርእስት ለንባብ ባበቁት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳናቸው ቅድስና ለሁሉም ሰው የቀረበ ጥሪ መሆኑን የሚገልጽ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን እንደ ነበረ ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በእነዚህ ሦስት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳኖች እና በሌሎችም ሐዋሪያዊ መልእክቶቻቸው ውስጥ ትኩረት በመስጠት በአጽኖት የሚናግሩት ቤተክርስቲያን ተቆልፋ ካልቸብት በመውጣት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ወደ ሕዝቡ በመጓዝ ሕዝቡን ወደ እግዚኣብሔር መምራት ይኖርባታል የሚል አጠቃላይ የሆነ ጭብጥ የያዘ መሆኑ ቀደም ባሉ ጊዜያት በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

14 May 2018, 13:05