ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፦ “በእየሩሳሌም እና በቬንዙዌላ ሰላም ይወርድ ዘንድ መጸለይ ይገባል!”

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በግንቦት 12/2010 ዓ.ም “የሰላም ንግሥት ሆይ ደስ ይበልስሽ” ከሚለው ጸሎት በኃላ ለዓለም ያቀርቡት ጥሪ

 

“የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ! ይበልሽ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና!” ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 12/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊክ ለተሰብሰቡ ቀሳውስት እና ምዕመናንና  ቀደም ሲል ያስደመጥናችሁን  በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መስረቱን አድርጎ የነበረ አስተንትኖ ካደረጉ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከሚደረጉ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን እና በፋሲካ በዓል ሰሞን ባሉ ቀናት ውስጥ የሚደገመውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበለሽ፣ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለመላው ዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት ዛሬ እያከበርነው የምንገኘው የጴራቂልጦስ በዓል ለባችን የአይሁዳዊያን፣ የክርስቲያኖች እና የሙስሊም እመንት ተከታዮች ቅዱስት ከተማ ወደ ሆነችው ወደ እየሩሳሌም እንዲያመራ ያደርጋል በማለት መልእክታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በግንቦት 11/2010 ዓ.ም ምሽት ላይ በእየሩሳሌም ለሰላም ጸሎት መካሄዱን በመግለጽ መልእክታችውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሳቸውም በመንፈስ በእዚያ ጸሎት ላይ ተካፋይ እንደ ነበሩ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። ዛሬም በቅዱስቲቷ ሀገር እና በመላው የመካከለኛ ምስርቅ ሰላም ይሰፍን ዘንድ በሰዎች ልብ ውስጥ መልካም ፍላጎታቸውን እንዲያነሳሳ፣ የውይይት መንፈስ እንዲኖር እና እርቅ እንዲፈጠር መንፈስ ቅዱስ ያግዛቸው ዘንድ መጸለያችንን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል።

“ተወዳጅ የሆናችውን ቬንዙዌላን ለማስታወስ እፈልጋለሁ” በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቬንዙዌላ በሚኖሩ ሕዝቦች እና መሪዎች ላይ በመውረድ ወደ ሰላም እና ወደ አንደንት መጓዝ የሚችሉበትን መንገድ በጥበብ መምረጥ ይችሉ ዘንድ መንፈስ ቅዱሱ እንዲረዳቸው ጸልሎቴ ነው ብለዋል።

በጴንጤ ቆስጤ ቀን የተከሰተው ክስተት ለቤተክርስቲያን ዓለም አቀፍ ተልዕኮ መነሻ እንደ ሆናት በመግለጽ መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ምክንያት ነው ዛሬ ለሚቀጥለው ዓለማቀፍ መንፈሳዊ የተልዕኮ ቀን የሚሆን መልእክት በዛሬው እለት ያስተላለፍነው በእዚሁ ምክንያት ነው ካሉ በኃላ እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ” ካሉ በኃላ ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መሰናበታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

20 May 2018, 14:52