ፍርሃትና መጨነቅ ፍርሃትና መጨነቅ  (AFP or licensors)

ፍርሃትና መጨነቅ

በአሁን ሰዓት የትኛውንም ሰው ምን አይነት ፍርሃት እንዳለው ብትጠይቀው አነሰም ተለቀም የሆነ የሚሰጋበት ነገር እንዳለው ይነግርሃል፡፡ ልዩነቱ ያለው የሚፈራና የማይፈራ ሰው በመኖሩና ባለመኖሩ ላይ ሳይሆን፣ አንዳንዱ ሰው ፍርሃቱን መጋቢ፣ ሌላኛው ሰው ደግሞ ፍርሃቱን አስራቢ በመሆኑ ላይ ነው።

የዚህ ዝግጅት አዘጋጅ እና አቅራቢ ባራና ባርጊኔ

አንተስ የምትፈራው ነገር ምንድን ነው? ይህንን ጥያቄ ስታነብ/ስትሰማ ፣ “አይ እኔ ምንም አይነት ፍርሃት የለብኝም” የሚል ሃሳብ ካለህ፣ የፍርሃትን ስሜት አምኖ በመቀበል የመጋፈጥ ፍርሃት እንዳለብህ ጠቋሚ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ አይነቱ ፍርሃት የድርብ ፍርሃት ሰለባ ያደርግሃል፡፡ አንዱ መጀመሪያውኑ ያለብህ ፍርሃት ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ፍርሃቱ እንዳይታወቅብህ ያለህ ፍርሃት ነው፡፡

እሺ፣ ፍርሃትን እምኖ በመቀበልና በመጋፈጥ አስፈላጊነት ከተስማማን፣ እንተም መስማትህን ቀጥል፡፡ ስለዚህ ወደነጥቤ ስመለስ . . . ፍርሃትህ ሁለት ገጽታ አለው፡፡ አንዱ ገጽታው ጤናማ ሲሆን ሌላኛው ገጽታው ደግሞ ጤና-ቢሱ ነው፡፡

የፍርሃት ጤናማ ገጽታው ከፍርሃቱ የተነሳ ልትወስድ የሚገባህን ጥንቃቄ በመውሰድ ሊወገድ ከሚችል እንቅፋትና ችግር የመጠበቅህ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ገጽታ ፍርሃቱን ካሸነፍክ በኋላ የምትገባበትን ደስ የሚል አለም ያጎላልሃል።

የፍርሃት ጤና-ቢስ ገጽታው ግን ከፍርሃቱ የተነሳ ሊደርስብህ የሚችለው ሁኔታ ሲጎላብህና ውጤቱ አስከፊ ወደሆነ ምላሽ ውስጥ ሲነዳህ ነው፡፡ ይህ ገጽታ የፈራኸው ነገር ቢደርስና ብትሸነፍ የሚሆንብህን አስከፊ ሁኔታ ያጎላብሃል።

ለፍርሃት ሊኖርህ የሚገባ ምላሽ ፍርሃትህን የማስራብ ምላሽ ቢሆን ተመራጭ ነው፡፡ ፍርሃትን ማስራብ ማለት ፍርሃትህን ከሚመግቡ ሃሳቦች፣ ሁኔታዎች፣ ማህበራዊ ትስስር መድረኮችና ሰዎች ራስን መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፍርሃቱ እያለም ሆነ ተወግዶ በፈጣሪህ እርዳታ ወደፊት ስትዘልቅ ልትገባበት የምትችለውን አስገራሚ የድል አለም ማሰላሰል ነው።

አፍጥጠህ ስላደርክ ወይም በብርድ ልብስህ ሽፍንፍን ብለህና ተደብቀህ ስላደርክ ፍርሃትን አታሸንፈውም፡፡ ዛሬ ማታ የምትፈራውን ነገር አድበስብሰኸው ሳይሆን አስበኸውና ልታሸንፈው እንደምትችል ውስጥህን አሳምነኸው ለመተኛት ሞክር።

ስለዚህ ወገኖቼ በፍርሃት መጨነቅ አቁሙና መሰራት ጀምሩ!

ከቁጥጥራችሁ ውጪ በሆኑና ፈጽሞ ለመለወጥ በማትችሏቸው ነገሮች ላይ ከማተኮርና ስለእነሱ ከመጨነቅ ይልቅ በቁጥጥራችሁ ስር ባለውና ለመለወጥ በምትችሉት ነገር ላይ በማተኮር ብትሰሩ ውጤቱ እጅግ የላቀ ነው፡፡

ፈጽሞ የማትችሉትን ለፈጣሪ አሳልፋችሁ በመስጠት መለወጥ የምትችሉት ላይ በማተኮር ስትሰሩ፣ ውስጣችሁ አረፍ ይላል፣ በአቅማችሁ የሰራችሁት ስራ ውጤት ሌላ አዲስ የእድል ደጅ ይከፍትላችኋል፣ የመተማመን መጠናችው ይጨምራል

በአጭርና ግልጽ በሆነ መልኩ ሲገለጥ፣ ያለፈ ልምምድን ማድመጥ ማለት ካለፉት ልምምዶቻችንና ገጠመኞቻችን የሚገባውን ትምህርት ቀስሞ ማለፍ ማለት ነው፡፡ ምናልባትም ራስህን ልትጠይቃቸው ከሚገቡህ ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ያለፈው ልምምዴ ምን አስተምሮኝ አለፈ? ያለፈው ስህተቴ ምን አስተምሮኝ አለፈ? ከዚህ በፊት ከደረሰብኝ ጉዳት ምን ትምህርት አገኘሁ? እንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን በመጠየቅና ትክክለኛውን መልስ ፈልጎ በማግኘት አስገራሚ የእድገት አለም ውስጥ ልትገባ ትችላለህ፡፡ ይህንን እውነት ብትለማመደው ካሳለፍካቸው ሁኔታዎች አንዱም እንኳ የሚወድቅ አይሆንም፡፡

አንዳንድ ሰዎች ለአመታት የሰሩትን ስህተት እንደገና ደጋግመው ሲሰሩ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ይህ የሚሆነው ያለፈው ልምምዳቸውን የማድመጥ ሁኔታ ስላላዳበሩ ነው፡፡ ስለዚህ ወጣት ሆይ! ከዚህ በፍት በህይወትህ ማድረግ ስገባህ ሳታደርገዉ ያለፈከዉና አሁን እጭ ያነ ይህን ባደረግኩ ኖሮ የሚትለዉ ነገር ካለ ለምሳሌ በት/ት ቤት ስትማር፤ በንግድ ዓለም  እንድሁም በቤተሰብ ዉስጥ ባሳለፍከዉ ፤ ካለፈው ልምምድህ መማር እና  ከዚህ በፊት የጨበጥከውን “እሳት” ደግመህ እንዳትጨብጥ ይረዳሃል፡፡ በሌላ አባባል፣ ከዚህ በፊት የጨበጥከው እሳት በእርግጥ አቃጥሎህ ከሆነ ደግመህ ያንኑ እሳት መጨበጥ የለብህም፡፡ ይህ እሳት የተለያዩ ነገሮችን የሚወክል ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሞክረህ አጉል ነገር ውስጥ ከጨመረህና ጉዳትን ካስከተለብህ ነገር መጠንቀቅን የሚነካ ጉዳይ ነው፡፡ ከሰራሃቸው ስህተቶች የተማርካቸውን ትምህርቶች ለይቶ ማወቅና የተሻለ ሰው ወደ መሆን ማደግህ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡

ካለፈው ስህተት መማር ከማህበራዊ ሕይወት አንጻርም ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በተመሳሳይ ሰዎች ደግመህ ደጋግመህ ከምትጎዳበት ግንኙነት ካልተማርክና ተገቢውን እርምጃ ካልወሰድክ፣ ካለፈው ልምምድህ የምትማር ሰው እንዳልሆንክ ጠቋሚ ነው፡፡ ከዚህ በፊት “በሞኝነትህ” ምክንያት ሰዎች ተጠቅመውብህና ጎድተውህ ከሆነ እንደዚህ አይነት ሰዎችን በመለየት በምን መልኩ እንደምትቀርባቸው በሚገባ ማቀድ አለብህ፡፡

ከዚህ በፊት አንድን ስህተት ሰርታችሁና ምናልባትም ያንኑ ስህተት ደግማችሁት ሰዎች በይቅርታ ሁለተኛ እድል ሰጥተዋችሁ ካወቃችሁ እናንተም ዛሬ ያንን እድል ለሰዎች እንድትሰጡ ላነሳሳችሁ፡፡ በአጭሩ፣ ሰዎችን ይቅር ማለት ከሚሰጣችሁ የስሜት ጤንነት፣ የአመለካከት ብሩህነትና የትኩረት ብቃት አንጻር አትራፊዎቹ እናንተው ናችሁ፡፡

ከዚህ በፊት የሰዎችን ይቅርታና የሁለተኛ እድልን ልምምድ ተለማምዳችሁ ባታውቁም እንኳን ወደፊት አንድ ቀን ሰዎች ሁለተኛ እድል እንዲሰጧችሁ የምትፈልጉበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርምና ዛሬ ለአንድ ሰው ሁለተኛ እድል ብትሰጡና አንድን ነገር በይቅርታ ብታልፉ ምን ይመስላችኋል?

ሰዎችን ይቅር ማለትና ሁኔታውን መርሳት ማለት ግን እንደገና ራስን ለጉዳት ማጋለጥ ማለት እንዳልሆነ ግን አትዘንጉ፡፡ ሰዎችን ይቅር በሉ፣ ከዚያ ወዲያ የሚኖራችሁን ግንኑነት ግን በጥበብ አድርጉ፡፡

ጭንቀት ሁለት ገጽታዎች አሉት። አንደኛው ጠቃሚ ሲሆን ሌላው ደግሞ ጎጂ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሁለቱንም ገጽታዎች ለይተን ማወቅ እንድንችል ይረዳናል።

እውነታው፦

ጭንቀት ያለመረጋጋት፣ የመረበሽ ወይም የስጋት ስሜትን ያካትታል። የምንኖረው አስተማማኝ ባልሆነ ዓለም ውስጥ በመሆኑ አልፎ አልፎ ማናችንም በጭንቀት ስሜት ልንዋጥ እንችላለን።

ንጉሥ ዳዊት “ልቤ በየዕለቱ በሐዘን እየተደቆሰ፣ በጭንቀት ተውጬ የምኖረው እስከ መቼ ነው?” (መዝሙር 13፡2) ሲል ጽፏል። ዳዊት ይህን ሁኔታ እንዲቋቋም የረዳው ምንድን ነው? በጸሎት አማካኝነት የልቡን ለአምላክ ያፈሰሰ ከመሆኑም ሌላ በአምላክ ታማኝ ፍቅር ሙሉ በሙሉ ይተማመን ነበር(መዝሙር 13፡5፣ 62፡8) አምላክ የከበደብብ በገር በእሱ ላይ እንድንጥል ጋብዞናል። አንደኛ ጴጥሮስ 5፡7 ላይ “የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ [በአምላክ] ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል” ይላል።

አንዳንድ ጊዜ በዕለት ተዕለት ኑሮዋችን ውስጥ እንደ ድብርት፣ ጭንቀትና ድካምን የመሳሰሉ ጥሩ ያልሆኑ ስሜቶች በተለያየ ምክንያት ሊሰሙን ይችላሉ። ሆኖም እነዚህ ስሜቶች ለረጅም ጊዜ እንዳይቆዩብንና ሥር እንዳይሰድዱ ልንቆጣጠራቸው ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን እነዚህ ስሜቶች ኑሮዋችንን ሊያናጉና በአካላዊ ጤንነታችንም ላይ ጉዳት ሊያመጡ ይችላሉ። ስለዚህ የአእምሮ ደህንነት ለአጠቃላይ የሰውነት ጤናም ሆነ ደስተኛ ኑሮ ለመኖር ወሳኝ ነው። የአእምሮ ደህንነት ስንል ስለአስተሳሰባችንና ስለአጠቃላይ ስሜታችን ጥሩ መሆን እንዲሁም በኑሮዋችን ለሚያጋጥሙን አይቀሬ ውጣ ውረዶች ጥሩ ምላሽ መስጠት መቻል ነው። ስለዚህ አንድ ሰው የአእምሮ ጤና አለው ሊያስብለው የሚችለው የአእምሮ በሽታዎችን ማስወገድ መቻሉ ብቻ ሳይሆን ያለውን እምቅ ችሎታ በአግባቡ ለመጠቀም መቻሉ፤ እንዲሁም የዕለት ኑሮውን ውጣ ውረድ ተቋቁሞ ለራሱ፣ በአካባቢው ላሉ ሰዎች፣ ለማህበረሰቡና በስራ ቦታው ላይ መልካም አስተዋጽዖ ማድረግ ሲችል ነው። የአዕምሮ ደህንነታችንን ለመጠበቅ በየዕለቱ የምናደርጋቸው ነገሮች እና ስሜቶቻችንን የመቆጣጠር ችሎታችን ትልቅ አስተዋጽዖ አላቸው።

30 July 2021, 15:21