የ “ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ኤኮኖሚ” አቅጣጫን የሚደግፉ የ “ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ኤኮኖሚ” አቅጣጫን የሚደግፉ  

የቁማር መጫወቻ ማሺኖች ለማኅበራዊ ዕድገት ጠንቅ ናቸው ተባለ

በጣሊያን ውስጥ ከሚገኙ ክልሎች መካከል አሥራ ሰባቱ፣ በርካታ ማኅበራት እና ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች የተካፈሉበት ሰልፍ ቅዳሜ ሐምሌ 3/2013 ዓ. ም. መካሄዱ ታውቋል። የሰልፉ ዓላማ የ “ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ኤኮኖሚ” አቅጣጫን በመደገፍ በየቡና ቤቱ የሚገኙ ቁማር መጫወቻ ሳጥኖች እንዲዘጉ የሚጠይቅ መሆኑ ታውቋል። በጣሊያን ውስጥ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ቡና ቤቶች እና የንግድ ተቋማት ባለቤቶች ከኤኮኖሚ ባለሞዎች ጋር በመተባበር በየቡና ቤቶች እና የንግድ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ የቁማር መጫወቻ ማሽኖች በማኅበረሰብ መካከል የኑሮ አለ መመጣጠንን እና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲስፋፋ የሚያደርጉ መሆኑን አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በጡረታ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሰዎች በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ከሃምሳ እስከ ስልሳ ሺህ ዩሮ ለቁማር ጨዋታ እንደሚያወጡ የገለጸው አንድ የሰልፉ ተካፋይ እነገለጸው እነዚህ እናቶች እና አባቶች ይህን ያህል ገንዘብ ለቁማር የሚያወጡ ከሆነ ለልጆቻቸው የትምህረት ቤት ክፍያን ልብስን እና ልዩ ልዩ ወጭዎችን መሸፈን የማይችሉ መሆኑን አስረድቷል። እ. አ. አ ከ1982 ዓ. ም. ጀምሮ ወላጆቹን በማገዝ ቡና ቤት ውስጥ ሲሰራ መቆየቱን የገለጸው አቶ ፋቢዮ ኮንዴሎ፣ በቡና ቤታቸው ውስጥ ቁማር መጫወቻ ማሽን እንደነበር አስታውሶ፣ ቡና ቤቱ ብዙ ሰዎች የሚገናኙበት እና እርስ በእርስ የሚተዋወቁበት ሥፍራ እንደነበር አስታውሷል። በወቅቱ በቡና ቤታቸው ውስጥ የተቀመጠው የቁማር መጫወቻ ማሽን በሰዎች ላይ ስነ ልቦናዊ ቀውሶችን በተለይም ብቻቸውን በሚኖሩ ሰዎች መካከል ከፍተኛ የጤና ቀውስን ሲያስከትል እንደነበር አስታውሷል።     በተመሳሳይ መልኩ ወላጆቹ እ. አ. አ በ2014 ዓ. ም. ሌላ ሱቅ መክፈታቸውን ያስታወሰው አቶ ፋቢዮ ኮንዴሎ፣ አካባቢው በርካታ ስደተኞች የሚኖሩበት፣ ማኅበራዊ ልዩነት የሚታይበት፣ አደንዛጽ እጾችን በመጠቀም እርሱ ራሱ ከሕሊናው ውጪ የሆነበት ወቅት መሆኑን አስታውሷል። ይህ መሆኑን ባስተዋለበት ጊዜ የቁማር መጫወቻ ማሽኖቹን ከቡና ቤቱ ለማስገድ መወሰኑን እና ወደ ሙሉ ጤና ሊመለስ መቻሉን አስረድቷል። በጣሊያን ውስጥ በበርካታ ቡና ቤቶች ውስጥ የተተከሉ ቁማር መጫወቻ ማሽኖች በሰዎች ጤና ላይ የሚያስከትሉትን ቀውሶች በመገንዘብ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ማስተካከል እንደሚያስፈልግ አቶ ፋቢዮ ኮንዴሎ አሳስቧል።

በጣሊያን ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ካስከተለው ቀውስ ቀጥሎ የቁማር መጫወቻ ማሽኖች የሚያስከትሉት የስነ ልቦና ቀውሶች እና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮች በአገሪቱ ውስጥ ትልቅ እንቅፋት እየሆነ መምጣቱን የ “ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ኤኮኖሚ” ሳይንሳዊ አቅጣጫ አስተባባሪ የሆኑት ክቡር አቶ ሉዊጂ ብሩኒ አስታውቀዋል።  የቁማር ኢኮኖሚ በርካታ ሰዎችን ለሞት አደጋ  እንደሚዳርግ በተለይም አቅመ ደካሞችን እና ድሆችን ሕይወት የበለጠ የሚጎዳ መሆኑን አስረድተዋል።

በጣሊያን ውስጥ አሲዚ ከተማ የሚገኝ የ “ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ኤኮኖሚ” ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ከጊዚ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ መሆኑ ታውቋል። በከተማው የሚገኙ ቡና ቤቶች የቁማር መጫወቻ ማሽኖችን ከንግድ ሥራዎቻቸው መካከል ማስወገዳቸው የ “ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ኤኮኖሚ” እንቅስቃሴ አባላት የሆኑት ወጣት ጃዳ ሮሲኞሊ እና ወጣት ገብርኤሌ ሳርናሪ አስታውቀዋል። ወጣቶቹ አክለውም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አገራቸው ክፉኛ መጎዳቷን አስታውሰው የጋራ ጥረት ካልተደረገ ማንም ሰው ከወረርሽኙ ብቻውን መትረፍ የምይችል መሆኑን አስረድተዋል። በአገሪቱ የማኅበራዊ ኤኮኖሚ ሥርዓትን ማሻሻል እንደሚገባ አሳስበው፣ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ማኅበራዊ ችግር ለእያንዳንዱ ሰው የሚተርፍ በመሆኑ ይህን ችግር ለማስወገድ ማኅበራዊ ጥረት እንደሚያስፈልግ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ማሳሰባቸውን አስታውሰዋል።   

12 July 2021, 16:39