ር. ሊ. ጳጳስት ፍራንችስኮስ ከክቡር አባ ፌዴሪኮ ሎምባርዲ ጋር ር. ሊ. ጳጳስት ፍራንችስኮስ ከክቡር አባ ፌዴሪኮ ሎምባርዲ ጋር  

አባ ሎምባርዲ፥ “የቫቲካን ሬዲዮ ተልዕኮ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ማገልገል ነው” አሉ

የቫቲካን ሬዲዮ ዋና ሥራ አስኬያጅ የነበሩት ክቡር አባ ፌዴሪኮ ሎምባርዲ፣ ቫቲካን ሬዲዮ የተቋቋበትን 90ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ “ላ ቺቪልታ ካቶሊካ” ለተባለ ታዋቂ መጽሔት የመጨረሻ እትም፣ ጽሑፍ አበርክተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በቀድሞ ር. ሊ. ጳ ፒዮስ 11ኛ ጥያቄ መሠረት፣ አቶ ጉሊዬልሞ ማርኮኒ የተባሉት ጠቢብ ሰው ያስጀመሩት የቫቲካን ሬዲዮ ጣቢያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት 90ኛ ዓመት የተከበረው ዓርብ የካቲት 5/2013 ዓ. ም. ነው። አዲሱን ሬዲዮ ጣቢያ የኢየሱሳዊያን ማኅበር አባል የሆኑት አባ ጁሰፔ ጃንፍራንቸስኪ እንዲንከባከቡት ተወሰነ። እንደሚታወቀው ከመጀመሪያው አንስቶ የቫቲካን ሬዲዮ ጣቢያ ዋና ተልዕኮ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ወንጌልን ለዓለም ሕዝቦች በሙሉ በማብሰር ለሚያበረክቱት ሐዋርያዊ አገልግሎት መሣሪያ በመሆን እና መላውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናንን መምራት እንዲችሉ ለማድረግ ነው። ይህ ተልዕኮ ለረጅም ዓመታት በመቀጠል በርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት በኩል ተደጋጋሚ እውቅንቅን በማግኘት የቤተክርስቲያኒቱን ጠንካራ ማንነት ማረጋገጥ ችሏል።  

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ድምጽ

አዲስ የቫቲካን መንግሥት ምስረታን ተከትሎ የቫቲካን ሬዲዮ እ.አ.አ በ1931 ዓ. ም. ተቋቋመ። የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመከተል በወቅቱ በአቶ ጉሊዬልሞ ማርኮኒ የተመሠረተው የቫቲካን ሬዲዮ ጣቢያ፣ ከጣሊያን መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖረው የቴሌ ግራፍ እና የሬዲዮ አገልግሎቶን በግሉ መስጠት ጀመረ። ለአጭር ሞገድ ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባው እና እንደ ዛሬው በርካታ የአጭር ሞገድ ስርጭቶች ባልነበሩበት ዘመን ስርጭቱን ወደ ሌሎች አህጉራትም ዝቅተኛ የኃይል አቅርቦትን በመጠቀም ማድረስ ችሏል። የቫቲካን ሬዲዮ ስርጭቱን ማስተላለፍ በጀመረበት ጊዜ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ካቶሊካዊ ምዕመናን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ድምጽ ለመጀመሪያ ጊዜ ማድመት ችለዋል።

እ.አ.አ 1930ቹ ዓመታት አምባገነናዊ መንሥታት የነበሩበት ዘመን ነበር። በወቅቱ የር. ሊ. ጳ ፒዮስ አቋም ጠንካራ እና ደፋርም ስለነበሩ በሚጋጥማቸው ችግሮች ሳይበገሩ ቤተክርስቲያንን በልበ ሙሉነት መርተዋል። በተለያዩ ቋንቋዎች አማካይነት የር. ሊ. ጳጳሳትን መሪነት እና እገዛን ማግኘት የአውሮፓ ካቶሊካዊ ምዕመናን አስቸኳይ ጥያቄ ነበር። ሬዲዮ ጣቢያውን በአዳዲስ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች በማደራጀት እና “የር. ሊ. ጳጳሳት ጣት” በመባል የሚጠራውን ረጅም አንቴና በቫቲካን አትክልት ውስጥ እንዲቆም በማድረግ ሬዲዮ ጣቢያው ከፍተኛ እድገትን እንዲመጣ ክቡር አባ ጁሰፔ ጃንፍራንቸስኪ ብዙ ጥረት አድርገዋል። እርሳቸው ካረፉ በኋላ እ.አ.አ ከ1934 ዓ. ም. ሬዲዮ ጣቢያውን እንዲመሩ አደራ የተሰጣቸው የ34 ዓመት ዕድሜ ወጣት የነበሩ ክቡር አባ ፊሊፖ ሶኮርሲ ነበሩ። ጂኦግራፊያዊ ርቀት ሳያግደው ስርጭቱን ያለ ምንም እንቅፋት ማስተላለፍ የጀመረው የቫቲካን ሬዲዮ ኮርፖሬሽን እ.አ.አ በ1936 ዓ. ም. የዓለም አቀፍ ዕውቅናን አገኘ። የሰው አቅም ማነሱን የተገነዘቡት ክቡር አባ ፊሊፖ ሶኮርሲ፣ በተለያዩ አገራት የሚገኙ የማኅበራቸው አባላት ጽሑፎችን በማረም እና በድምጽ በማቅረብ እንዲተባበሯቸው ጠየቁ። በወቅቱ በጀርመንኛ ቋንቋ የሚተላለፍ የሬዲዮ ፕሮግራም ከፍተኛ ተደማጭነት ነበረው።

በአሳዛኝ የጦርነቱ ወቅት ሰላምን በማወጅ አጋርነቱን ይገልጽ ነበር

የቫቲካን ሬዲዮ በጦርነቱ ዋዜማ እ.አ.አ በ1939 ዓ. ም. በቋሚነት የሚተላለፉ የጣሊያንኝ፣ የፈረንሳይኛ፣ የእንግሊዝኛ፣ የጀርመንኛ፣ የስፔን፣ የፖርቱጋል፣ የፖላንድ፣ የዩክሬን እና የሊቷኒያ ቋንቋዎች ዝግጅቶች ነበረው። ጦርነቱ የሚያስከትለውን ከፍተኛ የሰው እና የንብረት ውድመት በመቃወም፣ የጦርነቱ ሰላባ የሆኑትን በማገዝ፣ በማጽናናት እና ተስፋን በመስጠት የቤተክርስቲያን አለኝታ ሆኖ ማገልገሉ ይታወሳል። በጦርነቱ ዘመን የቀድሞ ር. ሊ. ጳ ፒዮስ 12ኛ የሚያስተላልፉት የሬዲዮ መልዕክት በመላው አውሮፓ ውስጥ በጉጉት የሚጠበቅ እና ከፍተኛ ትኩረት ይሰጠው ነበር። የር. ሊ. ጳ ፒዮስ 12ኛ ድምጽ ኃይለኛ እና ጦርነቱን ለሚመሩት የፍትህ እና የሰላም መልዕክት በማስተላለፍ ይታወቅ ነበር። ከዚህም በላይ የቫቲካን ሬዲዮ በጦርነቱ ወቅት የሚታወቅበት ሌላ አገልግሎት ነበረው። ይህም በር. ሊ. ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ ጥልቅ ፍላጎት መሠረት ከቫቲካን መንግሥት የመረጃ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር፣ በጦርነቱ ወቅት የሞቱትን ሰላማዊ ሰዎች፣ የሠራዊት አባላት እና እስረኞችን ስም ዝርዝር ለወላጅ ቤተሰብ ከማሳወቅ በተጨማሪ የሰላምታ እና የማስታወሻ መልዕክቶችን የሚለዋወጡበት መንገድ ማመቻቸት ነበር። የቫቲካን ሬዲዮ እነዚህን አገልግሎቶች በቀን ከ12 – 13 ሰዓታት በሳምንት ደግም ለ70 ሰዓታት ከፍ ማድረጉ ይታወሳል።            

የቤተክርስቲያን ድምፅ

የቫቲካን ሬዲዮ በአውሮፓ ውስጥ ይካሄድ የነበረው ጦርነት ካበቃ በኋላ በጦርነት ምክንያት ጉዳት እና የሞራል ውድቀት ለደረሰባቸው የአውሮፓ አገሮች ሕዝቦች የሞራል እና የመንፈስ ማበረታቻ አገልግሎትን መስጠት ሲሆን በሌላ ወገን እ.አ.አ በ1950 ዓ. ም. በተከበረው ቅዱስ ዓመት የቤተክርስቲያንን አስፈላጊነት ማደስ ትልቅ ሃላፊነት ነበር። ወቅቱ የምስራቅ አውሮፓ አገሮች በኮሚኒስት መንግስታት ጭቆና ስር የወደቁበት እና በበርካታ የምስራቅ አውሮፓ አገራት ውስጥ የምትገኝ ካቶሊክ ቤተከርስቲያን ለስደት እና መከራ የተጋለጠችበት ወቅት መሆኑ ይታወሳል። ይህ ወቅት የቫቲካን ሬዲዮ ምዕመናን በወንጌል መልካም ዜና እና መንፈሳዊ አስተምህሮዎች ራሳቸውን የሚያጽናኑበት፣ ከር. ሊ. ጳጳሳት ጋር እና ከኩላዊት ቤተክርስቲያን ጋር ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክሩበት ብቸኛው መንገድ ነበር።

ግብዓቶች በጣም ውስን ቢሆኑም በምስራቅ አውሮፓ አገራት ቋንቋዎች የሚዘጋጁ ፕሮግራሞች ብዙ በመሆናቸው ተጨማሪ የአየር ሰዓት ተሰጣቸው ነበር። ከ1940 ጀምሮ በፖላንድ፣ በጣሊያን፣ በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በስፔን እና በጀርመን ቋንቋዎች የሚቀርቡ ዝግጅቶች ግንባር ቀደም ነበሩ። ቀጥሎም በቼክ፣ ስሎቫኪያ፣ ሃንጋሪ፣ ሊጧኒያ፣ ላጥቢያ፣ ሩሲያ፣ ክሮዋሺያ፣ ስሎቫኒያ፣ ዩክሬን፣ ሮማኒያ፣ ቡልጋሪያ፣ በላሩሲያ እና በአልባኒያ ቋንቋዎች የሚቀርቡ ዝግጅቶች ተከትለዋል። ለአስርት ዓመታት ያህል በነበሩ የጭቆና ዓመታት ወቅት የቫቲካን ሬዲዮ እና የእምነት ነጻነታቸውን ለተነፈጉት እና እምነታቸውን በተግባር እንዳይኖሩ ለተከለከሉ ምዕመናን፣ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት፣ ካህናት እና ጳጳሳት ዘላቂ የሬዲዮ ዝግጅቶችን ሲያስደምጥ ቆይቷል። የፖላንድ እና ስሎቫክ ቋንቋዎች ጥቂት አድማጮች ቢኖሩትም እንደ ር. ሊ. ጳጳሳት ፍላጎት መሠረት የቫቲካን ሬዲዮ ዋና ዓላማ የአድማጭ ቁጥር በመብዛት ወይም በማነስ ሳይሆን አድማጭ የሚገኝበትን አስቸጋሪ የሕይወት ሁኔታን የሚያገናዝብ እና የሚያተኩር ነበር። በቫቲካን ሬዲዮ ከሚተላለፉት ቋንቋዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የምስራቅ አውሮፓ አገሮች ቋንቋዎች የሆኑበት ምክንያትም ለዚህ ነው።

ማኅበራዊ ግንኙነት ኅብረትን ለመፍጠር ነው

በ 1970 ዓ. ም. የቫቲካን ሬዲዮ የዝግጅት ክፍሉን እና ስቱዲዮዎቹን በቂ ቦታ ወደሚገኝበት በካስቴል ሳንት አንጄሎ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ጽሕፈት ቤት እንዲዛወር በማድረግ ለአስርት ዓመታት ዋና ጽሕፈት ቤቱን እዚያው አድርጎታል። እ.አ.አ 1973 ዓ. ም. አባ ሮቤርቶ ቱቺ ከአባ ማርቴጋኒ የሬዲዮ ጣቢያውን ሃላፊነት ተረከቡ። ቅዱስ ዓመት በተከበረበት እ.አ.አ 1975 ዓ. ም. የቫቲካን ሬዲዮ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በማሻሻል፣ የር. ሊ. ጳጳሳት የሚመሯቸውን መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓቶችን እና አስተምህሮችን እና በቂ መረጃዎችን በበርካታ ቋንቋዎች ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ከዓለም ዙሪያ ወደ ሮም ለሚመጡት መንፈሳዊ ነጋዲያን የተለያዩ መንፈሳዊ አገልጎቶችን እና መረጃን ማቅረብ ነበር።

የቫቲካን ሬዲዮ ፕሮግራሞች መሪ ሆነው የሰሩት ክቡር አባ ፓስኳለ ቦርጎሜዎ እና ማዕከላዊ ኤዲቶሪያል ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ክቡር አባ ፌሊክስ ዩዋን ካባሴስ በጋራ ሆነው የሬዲዮ ጣቢያውን ዓለም አቀፍ ግንኙነት በማሳደግ፣ በተለይም ከአውሮፓ ብሮድካስቲንግ ህብረት ጋር ግንኙነት በማሳደግ፣ እንዲሁም የሰነዶችን እና የዝግጅት መርሃግብር አደረጃጀትን በማሻሻል ከፍተኛ ለውጥ እንዲታይ አድርገዋል። የቫቲካን ሬዲዮ የጋዜጠኝነት ሞያዊ ብቃትን በማሳደግ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገቶችን በማስመዝገብ ዕለታዊ ፕሮግራሞችን ማሰራጨት ብቻ ሳይሆን ዋና ጽሕፈት ቤቱ ተስፋ እንዳደረገው ሁሉ ባለሞያዎችን ከምዕመናን ወገንም በመቀበል በቤተክርስቲያን ሕይወት በመሳተፍ ማኅበራዊ ግንኙነትን በማሳደግ ላይ ይገኛል።

06 February 2021, 19:33