የኢየሱስ እናት የኢየሱስ እናት 

የኢየሱስ ክርስቶስ እናት በሕገ ቀኖና የተገለጠችበት ሥነ-ጥበብ

በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር እናት የሆነች የቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓልን ታከብራለች። ይህም እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ጥቅምት 11/431 ዓ. ም. የተካሄደው የኤፌሶን ጉባኤ በሕገ ቀኖና በይፋ አስታውቋል። ሥነ ጥበብም ከዚህ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ሥነ መለኮታዊ ጥበብን ለምዕመናን በመተንተን የእምነትን እውነት ሲያሳውቅ ቆይቷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

አዳኝን ወደ ዓለም ያመጣች የድንግል ማርያም ምስጢር በምስል አማካይነት መግለጽ ቀላል አይደለም። ከስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልዕክቶችን እና ተጓዳኝ ተግባራትን በጥበብን ማሳየት በ431 ዓ. ም. በኤፌሶን የተካሄደው ጉባኤ ይፋ ባወጣው ሕገ ቀኖና ጸድቋል።   

ከጥንት ግሪክ እስከ ካታኮምብ ድረስ

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ በመባል የሚታወቀው መንፈሳዊ ምስል በቁስጥንጥንያው ባሲሊካ ውስጥ የሚገኝ የእመቤታችን መንፈሳዊ ምስል ነው። ይህ መንፈሳዊ ምስል የ“ምልክቱ ድንግል” በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ እመቤታችን እጆቿን ዘርግታ ከፊት ለፊቷ የሚባርክ ሕጻን አስቀድማ የምትታይበት ምስል ነው። በጣሊያን፣ ኤሚሊያ ሮማኛ ክፍለ ሀገር ውስጥ በቆሞስነት በማገልገል የሚገኙት እና የሥነ-መለኮት መምህር የሆኑት ክቡር አባ ጃንሉካ ቡሲ ለቫቲካን ዜና እንደገለጹት፣ ስለ ሁለቱ መንፈሳዊ ምስሎች ሲገልጹ አንደኛው በፕሪሺላ ካታኮምብ ውስጥ የሚገኝ፣ ሕጻኑ ኢየሱ እጆቹን ለጸሎት እንደዘረጋ የሚያሳይ ምስል ሲሆን ሁለተኛው በጥንታዊ የግሪክ ከተማ ኢሉሲስ የሚከናወነውን መንፈሳዊ የጸሎት ሥነ-ሥርዓት የሚያስታውስ ምስል መሆኑን ገልጸዋል።    

ድንግል ማርያም በምስራቁ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል የምትታይ ምልክት ናት

መለኮታዊ መዳፎችን ለመንካት እጆቿን ዘርግታ ከሆነ ይህ የደስታን ምልክት የሚያሳይ ነው። ድንግል ማርያምም ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ምስጢር ጋር መገናኘቷን ያስረዳል። ይህ መንፈሳዊ ግንኙነት፣ ክቡር አባ ጃንሉካ ቡሲ እንደሚገልጹት፣ በእግዚአብሔር ልጅ ትውልድ መካከል ክርስቲያናዊ ትርጉምን ይዞ ይገኛል። ሕጻኑም በወርቅ በተለበጠ ማስቀመጫ ውስጥ እንዲቀመጥ ተደርጓል። ይህ የቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊ ምስል መንፈሳዊ አገልግሎትን በመስጠት ከጎርጎሮሳዊያኑ 1054 ዓ. ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ዘንድ መንፈሳዊ ምልክት ሆኖ ቆይቷል።    

በጣሊያን የሚገኝ ትምህርት ቤት

በምዕራቡ ዓለም የኢየሱስ እናት፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተለየ መንገድ ትገለጻለች። እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1204 ዓ. ም. የቁንስጥንጥንያ ዘመነ መንግሥት ካከተመ በኋላ የቢዛንታይ ጠበብት ወደ ጣሊያን ተጉዘው በጣሊያን ከሚገኝ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤት ጋር እንዲገናኙ ዕድል ፈጥሮ ነበር። በዚህ የተነሳ ከሰባተኛው እስከ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ባሉት ዓመታት ወላዲተ አምላክ” የሚል ስም እንዲሰጣት አስችሏል።       

ትንቢትን የሚናገር መጽሐፍ

“ይህ መንፈሳዊ ምስል በመጀመሪያ ብዙም የሚታወቅ አልነበረም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ኢየሱስን እንደጸነሰች በግልጽ የሚያሳይ ነው” በማለት አባ ጃንሉካ ቡሲ ያስረዳሉ። እመቤታችን ቅድስት ማርያም የነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተነገርበት መጽሐፍ ተገልጦ በእጇ ይዛው ትታያለች። “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች”። (ኢሳ. 7፡14) ብዙውን ጊዜ ከማርያም ጎን ልጇን ኢየሱስን እና የማርያምን ድንግልና የሚገልጹ፣ አበባዎችን የያዙ ሁለት የአበባ ማስቀመጫዎች ይታያሉ።

ሥነ-ጥበብ የስርዓተ አምልኮ ምርኩዝ ነው

መንፈሳዊ ምስሎች፣ ለሚገነዘቧቸው ሁሉ ስለ አምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማንነት በማስረዳት ለዘመናት ያህል እገዛን አድረገዋል። የሥነ-ጥበብ ውጤቶች የሆኑት መንፈሳዊ ምስሎች ለአምልኮ ስርዓትም እገዛን በመስጠት፣ ምዕመናን በሕገ ቀኖና ላይ ያላቸውን የግንዛቤ ማነስ የማስወገድ ኃይል አላቸው። ከስድስተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የሥነ-መለኮት ተልእኮ ዋና ዓላማ፣ የሥነ-ጥበብ አዋቂዎች መንፈሳዊ መጽሐፍትን እና ምስሎችን በሚገባ እንዲረዱ የሚያስችል ዕውቀት መስጠት ነው። ይህ ሥነ-መለኮታዊ ዕርዳታ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ወደ ቅዱሳት ምስሎች የመለወጥ ባሕል እንዲዳብር አድርጓል። መንፈሳዊ ምስሎችም በበኩላቸው ለሥነ-መለኮታዊ አስተንትኖ ከፍተኛ እገዛን አድርገዋል።

03 January 2021, 18:45