በሊባኖስ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ተቃውሞ ሰልፍ፤ በሊባኖስ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ተቃውሞ ሰልፍ፤ 

በሊባኖስ፣ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች አገልግሎታቸውን ሊያቋርጡ ይችላሉ ተባለ።

በሊባኖስ ውስጥ ትምህርት በማዳረስ ከሚታወቁ የግል ተቋማት መካከል 80 ከመቶ የሚይዘው የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የትምህርት መስጫ ተቋማት፣ ከመንግሥት የሚሰጥ ድጎማ በመቋረጡ ምክንያት፣ በጎርጎሮሳዊያኑ 2020/2021 ትምህርት የመስጠት አገልግሎታቸውን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ ተነግሯል። ሊባኖስን ባጋጠመው ከፍተኛ የኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት፣ ጥራት ያለውን ትምህርት በመስጠት የሚታወቁ እውቅ የግል ትምህርት ቤቶች፣ ትምህርት የመስጠት አገልግሎታቸውን ሊያቋርጡ ይገደዳሉ ተብሏል።

የቫቲካን ዜና፤

መንግሥት የግል ትምህርት ቤቶችን ችላ ብሏል፣

በሊባኖስ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ጠቅላይ ጸሐፊ የሆኑት ክቡር አባ ቡትሮስ አዛር፣ ለአገሪቱ ፕሬዚደንት በላኩት ግልጽ ደብዳቤ እንዳስታወቁት፣ መንግሥት ለግል የትምህርት ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ በማቋረጡ ምክንያት፣ ካቶሊካዊ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎችም የግል ተቋማትም የትምህርት አገልግሎታቸውን ለማቋረጥ የሚግርደዱ መሆንስቸውን አስታውቀዋል። ክቡር አባ አዛር ለአገሪቱ ለፕሬዚደንቱ በጻፉት መልዕክት እንዳረጋገጡት፣ ግል የትምህርት ተቋማትን ያጋጠመው ችግር ከፍተኛ መሆኑን አስረድተው፣ የትምህርት ተቋማት መዘጋት አገሪቱን ለከፍተኛ ኪሳራ የሚዳርግ መሆኑን አስረድተዋል። በአገሪቱ ከሚታተም “ሎሬንት ለ ዡ” ከተባለ የፈረንሳይኛ ዕለታዊ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ክቡር አባ አዛር፣ ግል የትምህርት ተቋማት የትምህርት መስጠት አገልግሎት ለማቁረጥ የሚገደዱት፣ በሕግ አንቀጽ 46/2018 መሠረት የተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ ደንብ የግል ትምህርት ቤቶች መምህራንን ያላገናዘበ በመሆኑ እና መንግሥት ለግል የትምህርት ተቋማት የሚሰጠው ትኩረት ባለመኖሩ ነው ብለዋል።

ከሊባኖስ ሕዝብ ወደ ግማሽ የሚሆነው በድህነት ሕይወት የሚኖር ነው፣

ከኮሮርና ወረርሽኝ አስቀድሞም ቢሆን ሊባኖስ በከፍተኛ የኤኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደነበር ሲታወቅ፣ ባለፈው የጎርጎሮሳዊያኑ ዕእመት በርካታ ሰላማዊ ሰልፎች ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወቃል። ሊባኖስን ባጋጠመው ከፍተኛ የኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት የገንዘቡ ዋጋ ከዶላር ጋር ሲወዳደር ስድሳ ከመቶ ዝቅ ማለቱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የግል ንግድ ተቋማት ለኪሳራቸው መዳረውጋቸው እና በአግሪቱ ሦስት አራተኛ የሥራ አጥ ቁጥር መመዝገቡ ታውቋል። የግል ትምህርት ቤቶች መዘጋት የጀመሩት ያለፈው ጎርጎሮሳዊያኑ ዓመት በተካሄዱት ከፍተኛ የሰው ቁጥር የተሳተፈባቸው የተቃውሞ ሰልፎች መካሄድ በጀመሩበት ጊዜ መሆኑን ያስታወሱት ክቡር አባ አዛር፣ ቀጥሎም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሲጀመር ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለመኡሉ መጸጋታቸዋን አስረድተዋል።

ካቶሊክ ትምህርት ቤቶች አጥረት ላይ ይገኛሉ፣

በሊባኖስ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ጠቅላይ ጸሐፊ ክቡር አባ ቡትሮስ አዛር በመልዕክታቸው እንደገለጹት እርሳቸው የሚመሩት ትምህርት ቤቶች ለመዘጋት በሚገደዱበት ወቅት ተማሪዎቻቸው ወደ መንግሥት ትምህርት ቤት እንደሚዛወሩ፣ በሽህዎች የሚቆጠሩ መምህራኖቻቸው ሥራ እንደሚያቋርጡ፣ የሥራ አጥ ቁጥር እንደሚጨምር፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ ድህነት የሚጨምር መሆኑን አስረድተዋል።  ክቡር አባ ቡትሮስ አዛር አክለውም በአገሪቱ ከሚገኙ የግል ትምህርት መስጫ ተቋማት መካከል ጥቂቶቹ ለመምህራኖቻቸው ሙሉ የወር ደሞዛቸውን፣ ጥቂቶቹ ግማሽ ወርሃዊ ደሞዛቸውን፣ አብዛኛዎቻቸው ምንም ደመወዝ መክፈል የማይችሉ መሆኑን አስረድተዋል። በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ከፍተኛ ዕውቅና ያለው እና በኢየሱሳዊያን ማኅበር የሚተዳደረው የኖተር ዳም ጃሞር ኮሌጅም የመዘጋት ዕድል ያጋጠመው መሆኑን አባ አዛር አስታውቀው፣ የገንዘብ ችግር ለማቃለል ተብሎ በወጣው ዕቅድ መሠረት፣ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ አግሮች ከሚገኙ የቀድሞ ተማሪዎች የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ገልጸዋል።

የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ዕገዛ፣

በግንቦት ወር ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለተማሪዎች የነጻ ትምህርት ዕድል ለማመቻቸት የሚውል፣ የ200,000 ዶላር ዕርዳታ፣ በቤይሩት በሚገኝ የቅድስት መንበር እንደራሴ በኩል ማበርከታቸው ይታወሳል። በቤይሩት የቅድስት መንበር እንደራሴ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ስፒቴሪ እንደገለጹት አገሪቱ በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚደነቅ ሥርዓተ ትምህርት እንዳለው አስረድተው በፖለቲካ እና ኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ተማሪዎች ከፍተኛ ዋጋን በመስዋዕትነትን ለመክፈል መገደዳቸውን ገልጸዋል።        

08 June 2020, 18:40