ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ  

ብጹዕ ካ. ብርሃነየሱስ በኢትዮጲያ የሚገኘውን የጣሊያን ኤምባሲ ጎበኙ።

መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳትን በመወከል በአዲስ አበባ የጣልያን ኤምባሲ ተገኝተው በጣልያን ሀገር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለከቡር አምባሳደሩ ልክቡር አርቱሮ ሉዚ እና ለኤምባሲው ማኅበረሰብ ገልጸዋል፡፡ ብፁዕነታቸው ከክቡር አምባሳደሩ እና የኤምባሲው ማኅበረሰብ ጋራ በመሆን በወረርሺኙ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ፣ በአሁኑ ሰዓት በህመም እና ስቃይ ላይ የሚገኙትን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲፈውስ፣ ለህሙማኑ እርዳታ በማድረግ የሚለፉትንም እግዚአብሔር እንዲጠብቃቸው, አለማችንም ከገጠማት ፈተና በድል እንድትወጣ እግዚአብሔር እንዲረዳት ጸሎት አድርሰዋል፡፡

ምንጭ የኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋና ጽሕፍት ቤት

01 April 2020, 20:54