በቤርጋሞ ከሚገኙ መመገቢያ ጣቢያዎች መካከል አንዱ፣ በቤርጋሞ ከሚገኙ መመገቢያ ጣቢያዎች መካከል አንዱ፣ 

“እርስ በእርስ መተጋገዝ የኮሮና ቫይረስ ፍርሃትን ያስወግዳል”።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እጅግ በጎዳት የሰሜን ጣሊያን ከተማ ቤርጋሞ ከሚያስፈልጋት አስቸኳይ የመድኃኒት እርዳታ አቅርቦት በተጨማሪ በከታማው የሚገኙ ድሃ ቤተሰቦች በ“አባ አልቤርቶ ቤረታ” መመገቢያ ጣቢያ ውስጥ የምግብ እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ሲነገር ይህ ባይሆን ኖሮ ተረጂዎቹ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ራሳቸውን መመገብ የማይችሉ መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን 

በየቀኑ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ጀምሮ በመመገቢያ ጣቢያው ደጃፍ ሰዎች ወረፋቸውን መያዝ የሚጀምሩ መሆኑ ታውቋል። የዚህ መመገቢያ ጣብያ መስራች ጃና ቤረታ፣ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2004 ዓ. ም. የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅስናዋን ማወጃቸው ይታወሳል። ማዕከሉ ባሁኑ ጊዜ “ሲቲ ኤንጀል” ተብሎ በሚጠራ ማኅበር የሚመራ መሆኑ ታውቋል።

የማኅበሩ መሪ የሆኑት ክቡር አባ ሪካርዶ ኮርቲ እንዳስረዱት የቤርጋሞ ከተማ የኮሮና ወረርሽኝን ለመቀነስ ከሚቀርብላት አስቸኳይ የመድኃኒት እርዳታ በተጨማሪ ስዎች በቤታቸው እንዲቆዩ በተደረገበት ባሁኑ ወቅት በርካታ ሰዎች በየቀኑ ወደ መመገቢያ ጣብያቸው መጥተው የምግብ እርዳታን የሚያገኙ መሆኑን አስታውቀዋል። ከወረርሽኙ ቀደም ብሎ ማዕከላቸው ለከተማው ድሃ ቤተሰብ የምግብ እርዳታን ሲያቀርብ መቆየቱን ገልጽው ችግሩ እየተባባሰ ሲመጣ አገልግሎያቸውን ሳያቋርጡ በቀን ሦስት ጊዜ የምግብ እርዳታን የሚያከፋፍሉ መሆኑን አስረድተዋል።

ችግሮች ቢኖሩም ኅብረታችን መቋረጥ የለበትም፣

ከተረጂዎች መካከል አብዛኛ የውጭ አገር ዜጎች መሆናቸውን የተናገሩት አባ ሪካርዶ ኮርቲ፣ ጦርነትን እና ድህነትን አምልጠው የመጡ የአፍሪቃ እና የምስራቅ አውሮፓ አገሮች ስደተኞች ናቸው ብለዋል። ከጀርባቸው በርካታ የተለያዩ ታሪኮች ያሏቸውን እነዚህን ስደተኞችን ተቀብሎ የሕክምና እና የምግብ እርዳታ ካልተደረገላቸው ለብቸኝነት፣ ለሕመም እና ለረሃብ የሚጋለጡ መሆኑን አስረድተው፣ ከስደተኞቹ አንዱ ወደ መመገቢያ ማዕከል መምጣት ሳይችል ሲቀር፣ የተዘጋጀለትን ምግብ ጓደኛው የሚያደርስለት መሆኑን ገልጸዋል። ለማዕከላቸው በገንዘብ እና በምግብ ማቅረብ ለመርዳት የሚፈልጉ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን ያስታወቁት አባ ሪካርዶ የአካባቢው ቀይ መስቀል ማኅበር ከከተማው ሬስቶራንቶች የሰበሰባቸውን ምግቦች የሚያመጣላቸው መሆኑን ገልጸዋል። በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የከተማው ነዋሪዎች የተቻላቸውን እገዛ የሚያደርጉ መሆኑን አባ ሪካርዶ ገልጸው ዕርዳታው ከተለያዩ የጣሊያን ክፍለ ሃገራት የሚደርሳቸው መሆኑን ገልጸዋል።

16 April 2020, 14:14