የቅዱስ ጴጥሮ ባዚሊካ የቅዱስ ጴጥሮ ባዚሊካ  

በአፍሪካ የሚገኙ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ቁጥር ቀጣይነት ባለው መልኩ እያደገ መምጣቱ ተገለጸ

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር ቀጣይነት ባለው መልኩ እያደገ መምጣቱን እና አብዛኛ እድገት የተመዘገበው በአፍሪካ አህጉር መሆኑ ተገለጸ። በቅድስት መንበር ስር የሚተዳድረው የካቶሊክ ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከል ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር ቀጣይነት ባለው መልኩ እያደገ መምጣቱን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ባለፈው አመት ማለትም እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2017 ብቻ በዓለማቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ብዛት 1.1 % መጨመሩን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በአውሮፓ የሚገኙ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች በቁጥር እያነሱ ነው!

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ የሚገኙ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ምዕመናን ከባለፉት አመታት ጋር በንጽጽር ሲታይ ከአመት ወደ አመት ቀጣይነት ባለው መልኩ ቁጥራቸው እያደገ እና እየጨመረ መምጣቱን ከወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተለይም ደግሞ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2010-2016 ዓ.ም በአፍሪካ አህጉር ምስጢረ ጥምቀት የተቀበሉ ምዕመን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከአመት ወደ አመት በቁጥር ከፍ እያለ መምጣቱን የገለጸው መረጃው በተቃራኒው ግን በአውሮፓ አህጉር የሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር ከአመት ወደ አመት በቁጥር እያነሰ መምጣቱን መረጃው በሰፊው ያትታል።

በዓለም ዙሪያ 1ቢሊዮን 258 ሚሊዮን የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ይገኛሉ!

በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከል ጳጳሳዊ ጽህፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2015-2016 ዓ.ም ባሉት ሁለት አመታት ውስጥ ከተደረገው ጥናት ለመረዳት እንደ ተቻለው በዓለማቀፍ ደረጃ እ.አ.አ 2015 ዓ.ም 1ቢሊዮን 258 ሚሊዮን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በዓለም ዙሪያ እንደ ሚገኙ የገለጸ ሲሆን ይህ አሀዝ በ1.1% በመጨመር አሁንም እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር 1 ብሊዬን 299 ሚልዮን መድረሱን ለመረዳት ተችሉዋል።

በተያያዘ መልኩም በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የሚገኘው የሕዝብ ብዛት በቁጥር እያደገ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ይህ በፍጥነት እያደገ የሚገኘው የዓለማችን የሕዝብ ቁጥር ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር ከመጨመር ጋር በንጽጽር ሲታይ የካቶሊክ ምዕመናን ሕዝብ ቁጥር መጨመር ልቆ እንደ ሚታይ ከወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም አሀዛዊ በሆነ እና ለመረዳት በሚያስችል መልኩ ሲገለጽ እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም የዓለም የሕዝብ ቁጥር በ17.67% መጨመሩ እና በተመሳሳይ አመት በዓለማቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር በ17.73 % ማደጉን እና ከአጠቃላይ ዓለም ሕዝብ ብዛት መጨመር ጋር በንጽጽር ሲታይ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር በ0.6% ብልጫ መደጉን ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2017 ዓ.ም በአፍሪካ አህጉር የሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ቀጣይነት ባለው መልኩ በቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተቃራኒው ግን በአውሮፓ አህጉር የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በቁጥር እያነሰ መምጣቱ መረጃው በስፊው ያሳያል።

በእዚህም መሰረት በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ከአጠቃላይ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ቁጥር አኳያ በንጽጽር ሲታይ 17.6 % የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአፍሪካ አህጉር እንደ ሚገኙ በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከ ጳጳሳዊ ጽህፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2010 ዓ.ም በአፍሪካ አህጉር የነበረው የካቶሊክ ምዕመና ሕዝብ ቁጥር 185 ሚልዮን እንደ ነበረ እና ይህ አሀዝ በስድስት አመት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም 228 ሚልዮን እንደ ደረሰ በቅድስት መንበር ስር የሚተዳድረው የካቶሊክ ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው አመታዊ መረጃ የገለጸ ሲሆን በእነዚህ አመታት ውስጥ ከፍተኛ የካቶሊክ ምዕመና ቁጥር መጨመር የታየባቸው ሀገራት በቅደም ተከተል ሲቀመጥ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብልክ፣ በናይጄሪያ፣ በሁጋንዳ እና በንጎላ የተመዘገበው የካቶሊክ ምዕመን ቁጥር ከፍተኛ እንደ ሆነ ከወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተቃራኒው “አዛውንቱ አህጉር” በመባል በሚታወቀው የአውሮፓ አህጉር ግን የካቶሊክ ምዕመና ቁጥር በ0.2% ቅናሽ ማሳየቱ የተገለጸ ሲሆን ይህም በዓለማቀፍ ደረጃ ካለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን አጠቃላይ ቁጥር አንጻር ሲታይ በአውሮፓ አህጉር የሚኖር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን 22% እንደ ሆኑ ለመረዳት ተችሉዋል።

በእዚህም መሰረት በዓለማቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ብዛት በመቶኛ ሲቀመጥ ከፍተኛ የካቶሊክ ምዕመናን የሚገኙት ላቲን እና መካከለኛውን አሜርካ ጨምሮ 48.6 % በአሜርካ አህጉር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ 22% በአውሮፓ፣ 17.6% በፍሪካ፣ 11% በኢስያ እና 0.8% በሆሺኒያ አህጉር እንደ ሚገኙ በቅድስት መንበር ስር የሚተዳድረው የካቶሊክ ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ካደረገው አመታዊ መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ቁጥር 5,353 ገደማ ነው

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2010 -2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የነበረውን የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ቁጥር በንጽጽር የተመለከተው በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው የካቶሊክ ምዕመናን ብዛት ቆጠራ ማዕከል ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም ይፋ ያደረገው አመታዊ መረጃ እንደ ሚያስረዳው የካቶሊክ ብጹዕን ጳጳሳት ቁጥር በ5% ማደጉን የገለጸ ሲሆን በእዚህም መሰረት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ቁጥር 5,353 መደርሱን መረጃው ያስረዳል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከት ካህናት ብዛት 415.792 ገደማ ነው

ዜኒት በመባል የሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የዜና ማሰራጫ ማዕከል በድረ ገጹ ላይ ካሰፈረው ዘገባ ለመረዳት እንደ ተቻለው በአሁን ወቅት በዓለማችን ላይ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከት ካህናት ቁጥር 415,792 በመገናኛ ብዙሃን ገጹ ያሰፈረ ሲሆን፣ 54,599 የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት እና ገዳማት ካህናት፣ 44, 566 ቋሚ ዲያቆናት፣ 682,729 ደናግላን፣ 3,264,768 ካታኪስቶች፣ 116.939 የዐብይ ዘረዓ ክህነት ተማሪዎች፣ 102,942 የንዑስ ዘረዓ ክህነት ተማሪዎች በዓለም ዙሪያ እንደ ሚገኙ ዜኒት ከተባለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የዜና መስጫ ማዕከል ድዕረ ገጽ ላይ ከወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንፍሳዊ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ በመሰጠት ላይ እንደ ሚገኙ ለመረዳት ተችሉዋል።

በተጨማሪም ዜኒት የተባለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የዜና መስጫ ማዕከል ድረ ገጽ ላይ ከወጣው መረጃ በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚተዳደሩ 73,580 መዋለ ሕጻናት ውስጥ የሚማሩ 7,043,634 ሕጻናት እንደ ሚገኙ፣ 96,283 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ 33,516,860 ተማሪዎች እንደ ሚገኙ፣ በዓለም ደረጃ በሚገኙ 46,339 ሁለተኛ ደረጃ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤቶች ውስጥ ደግሞ 19,760,924 ተማሪዎች የትምህርት እድል አግኝተው በመማር ላይ እንደ ሆኑ ዜኒት ካወጣው መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ደረጃ ለ2,477,636 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና 2,719,643 የዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች የተለያየ ዓይነት ድጋፍ እያደርገች እንደ ምትገኝ ይታወቃል።

የሕክምና መስጫ ተቋማትን በተመለከተ ደግሞ በሁኑ ወቅት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ 5,158 ታላላቅ የሕክምና መስጫ ሆስፒታሎች እና 16,523 የጤና ክብካቤ መስጫ ጣቢያዎች እንደ ሚገኙ እና የተለያየ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1,221 ሆስፒታሎች እና 5,230 የጤና ክብካቤ መስጫ ጣቢያዎች በአፍሪካ እንደ ሚገኙ ከዜኒት ድረ ገጽ ካገኘበው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

 

02 May 2019, 17:27