ቅ. ማክሲሚላን “ሕይወትን ለሌላ አስልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር የለም”

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ዛሬ ማለትም በነሐሴ 08/2010 ዓ.ም የሰማዕቱ የቅዱስ ማክሲሚላን ማሪያ ኮልቤ አመታዊ በዓል መከበሩ ይታወቃል። ሰማዕቱ ቅዱስ ማክሲሚላን ማሪያ ኮልቤ የፖላንድ ሀገር ተወላጅ የሆነ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህን የነበረ ቅዱስ እንደ ሆነ ከታሪካቸው ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በወቅቱ በነበረው የጀርመን የናዚ ርዕዮተ ዓለም አራምጆች አይሁዳዊያንን ደብቀኃል፣ ለእነርስም ትወግናለህ የሚል ክስ ይደርሳቸዋል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዚህ ክስ የተነሳ በወታድሮች ይያዛሉ፣ የናዚ እስረኞች በሚታሰሩበት በፖላንድ ሀገር በሚገኘው የእስረኞች ማጎሪያ ቤት ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል። ከታሪክ እንደ ምንረዳው የናዚ የእስረኛ ማጎሪያ ጣቢያዎች የሞት ፍርድ ተፍርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ እስረኞች የሚገኙበት፣ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች በአብዛኛው የሚስተዋሉበት የሞት ቤት ተድርጎ እንደ ሚቆጠር ያታወቃል።

ሰማዕቱ ቅዱስ ማክሲሚላን ማሪያ ኮልቤ ወደ እዚህ የናዚ የእስረኞች ማጎሪያ ቤት እንዲገቡ ከተደረገ በኋላ ግን ሁኔታው ይቀየራል። ተስፋ ለቆረጡ እስረኞች ተስፋን በመስጠት፣ ሞትን በእግዚኣብሔር ኃይል መጋፈጥ እንደ ሚቻል፣ እግዚኣብሔር መሐሪ እና በርኅራኄ የተሞላ አበት በመሆኑ ነብሳቸውን በይቅርታ እንደ ሚቀበል በማስተማር፣ መስዋዕተ ቅዳሴን በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ በማሳረግ፣ እስረኞ የውዳሴ ዜማ ወደ አምላክ እንዲያቀርቡ የተቻላቸውን ሁሉ በማድረግ የሞት ቤት የነበረውን የናዚ የእስረኞች የማጎሪያ ቤት በሕይወት እና በተስፋ የተሞል ስፍራ እንዲሆን በማድረግ ሂደት ውስጥ ሰማዐቱ ማክሲሚላኖ ማሪያ ኮልቤ ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ አድርጉዋል።

ሕይወትን ለሌላ አስልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር የለም

በወቅቱ ከሰማዕቱ ማክሲሚላን ማሪያ ኮልቤ ጋር ታስረው የሞት ፍርዳቸውን ይጠባበቁ የነበሩ እስረኞች በእስርቤቱ አለቃ ትዕዛዝ የተፈረደባቸውን የሞት ፍርድ ለመቀበል እንዲሰለፉ ይታዘዛሉ። በወቅቱ በሰልፉ መጀመሪያ ላይ የነበረው አንድ የቤተሰብ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው ሲሆን እርሱም የሞት ቅጣቱ ሊፈጸምበት በተቃረበበት ወቅት “ወይኔ ወይኔ ሚስቴን፣ ወይኔ ልጆቼን. . .” እያለ መጮኽ ይጀምራል። በዚህን ጊዜ ሰማዕቱ ቅዱስ ማክሲሚላኖ ኮልቤ የዚህ አባት ጩኸት በጣም ልባቸውን ይነካል፣ ሚስቱን እና ልጆቹን ጥሎ መሞቱ በጣም እንዳሳዘነው ስለገባቸው “እኔ በእርሱ ቦታ መሞት እፈልጋለሁ! እኔ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህን ነኝ፣ ሚስትም ልጆች የሉኝም፣ እኔ በእርሱ ፈንታ ለመሞት እፈልጋለሁ” ብሎ ጮክ ብሎ ይናገራሉ።

የእስር ቤት አለቃ ይህንን በሰማ ጊዜ “አንተ ከእኔ ትዕዛዝ ውጪ በማንም ሰው ሕይወት ውስጥ ጣልቃ ለመግባት አትችልም፣ ይህ ባሕሪ ለእኔ ያለህን ከባድ ንቀት ያሳያል፣ በማለት ከፍተኛ ቅጣት በአባ ማክሲሚላኖ ማሪያ ኮልቤ ላይ እንዲጣል ያደጋል። በዚህም መሰረት አባ ማክሲሚላኖ ማሪያ ኮልቤ ወደ አንድ ልዩ የማጎሪያ ክፍል ውስጥ ብቻቸውን እንዲታሰሩ ይደረጋል፣ በዚያም ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ጥቃት ከተፈጸመባቸው በኋላ ጥቃቱ ከምግብ እጥረት ጋር ተዳምሮ በጣም ስላደከማቸው ከሁለት ሳምንታት በኋላ እ.አ.አ በነሐሴ 14/1941 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከሕይወቱ ታሪካቸው ለመረዳት ተችሉዋል፣ ይህንን ሁሉ ስቃይ መቀበላቸው “ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም (ዮሐንስ 16.13) የሚለውን የእግዚኣብሔር ቃል በሕይወታቸው መስክረው ለሰዎች ያላቸውን ፍቅር በተግባር በማሳየት ያለፉ ሰማዕት ናቸው።

አባ ማክስሚላን ማሪያ ኮልቤ በአንድ ምንም ጥፋት በሌለበት፣ ነገር ግን በናዚ ርዕዮተ አራማጆች የሞት ፍርድ የተፈረደበትን አንድ አባት ለማዳን የራሳቸውን ሕይወት አስልፈው በመስጠታቸው አባ ማክስሚላን ሞቱዋል ማለት አይችላም፣ ነገር ግን “ሕይወቱን ለወንድሞቹ አሳልፎ በመስጠቱ” ሕያው ሆኖ በእግዚኣብሔር ዘንድ ለዘለዓለም ይኖራሉ። የአባ ማክስሚላን ሞት እውነተኛ ሞት ሳይሆን “ሕይውቱን ለወንድሞቹ ብሎ አስላፎ በምሰጠቱ” ከምድራዊ ሕይወት ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ተሻግረዋል።

14 August 2018, 12:33