2018-01-17 Pontificia Università Cattolica 2018-01-17 Pontificia Università Cattolica 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ትምህርት ወደ ሕብረተሰቡ የሚዳረስባቸውን መንገዶች ጠቆሙ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአርጀንቲና ትምህርትን ወደ ማሕበረሰብ ዘንድ በሚገባ ለማዳረስ እንቅፋት የሆኑ ዋነኛ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት ዛሬ መልካም ውጤትን እያስገኘ ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባልና፣ ካቶሊካዊ ስልጣኔ በሚል መጠሪያ ለሚታወቅ ጥንታዊ መጽሄት ዋና አዘጋጅ የሆኑት ክቡር አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በትውልድ አገራቸው፣ በአርጀንቲና እያሉ ትምህርትን ወደ ሰዎች ዘንድ በሚገባ ለማዳረስ እንቅፋት የሆኑ ዋነኛ ተግዳሮቶችን  ለመቅረፍ ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት፣ ዛሬ መልካም ውጤትን እንዳስገኘ በመጽሔታቻው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል።

በትምህርት አሰጣጥ ላይ የሚደርሱ ፈተናዎች ወይም ተግዳሮቶች የሚሉ ርዕሠ ጉዳዮች ርዕሠ ሊቃነ ፍራንችስኮስን የሚያሳስቡ ርዕሶች መሆናቸውን የገለጹት ክቡር አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ፣ ሰባቱን ዋና ዋና መሠረታዊ የሆኑ የትምህርት አምዶችን ዘርዝረዋል። አንደኛ፣ ማስተማርና ያስተማሩት እውቀት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፣ ሁለተኛ፣ ከትምህርት የሚገኘውን እውቀት መቀበልና ልዩነቶችም ካሉ እንደሁኔታው ማስተናገድ፣ ሦስተኛ፣  በማሕበራዊ ሕይወት ሊከሰቱ የሚችሉ ለውጦችን ተቀብሎ ለማስተናገድና ለመቋቋም ጥረት ማድረግ፣ አራተኛ፣ ትምህርትን ለመቅሰም እንዲሁም የቀሰምነውን ለሌላ ለማስተላለፍ የሚረዱ መንገዶችን ወይም ዘዴዎችን አጥብቆ መያዝ፣ አምስተኛ፣ ጥያቄዎችን የማዘጋጀት ስልቶችን ማወቅ፣ ስድስተኛ፣ እውቀትን እንዳይቀሰም የሚያደርጉ ገደቦች መኖራቸውን አለመዘንጋት፣ ሰባተኛ፣ ፍሬያማነት የሚታይበት መልካም ቤተሰባዊ ኑሮን መኖር፣ የሚሉ እንደሆነ አስረድተዋል።

የትምህርት አድማስን ማስፋት፣

የካቶሊካዊ ስልጣኔ የሚል መጽሔት ዋና አዘጋጅ የሆኑት ክቡር አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ በመጽሔታቸው ላይ ባወጡት ጽሑፋቸው እንዳሰፈሩት ከሰባቱ የትምህርት መቅሰሚያ ዜዴዎች ጎን ለሌሎች ሦስት ጠቃሚ ንዑስ ርዕሶች እንዳሉ ጠቅሰዋል። እነዚህም፣ ለትምህርት ዘርፍ ወይም ዓይነት የሚደረግ ምርጫ፣ በተመረጠው የትምህር ዘርፍ የሚኖር ፍላጎት እና ለተመረጠው የትምህርት ዓይነት ያለን ፍቅር የሚሉ እንደሆኑ አስረድተዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የማስተማር ጥበብ እጅግ ትልቅ ደስታን እንደሚሰጥና የዕውቀት አድማስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲሰፋ ያደርጋል ማለታቸውን ክቡር አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ተናግረዋል። ከትምህርት የሚገኝ እውቀት በግል ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን ማሕበራዊ እሴት እንደሆነ በጽሑፋቸው የገለጹት ክቡር አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትምህርት ቤት ማሕበራዊ ውሕደትን ለማምጣ እጅግ አስፈላጊ መንገድ እንደሆነ መናገራቸውን አስታውሰዋል።

አስተማሪዎች የፈጠራ ችሎታቸውን በድፍረት ያሳዩ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቀዳሚነት የሚጠቅሱት፣ ከትምህርት የሚገኘውን እውቀት በመቀበል፣ ልዩነቶችም ካሉ እንደ አመቺነቱ ማስተናገድ መቻል የሚል እንደሆነ የገለጹት ክቡር አባ አንቶኒዮ ልዩነቶች እንደ አዎንትዊ ተግዳሮቶችና እሴቶች መታየት እንጂ እንደ እንቅፋት መታየት የለባቸውም ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በትምህርት ሂደት የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን ከማሕበራዊ ኑሮ ፈተና ጋር አያያይዘውታል ያሉት ክቡር አባ አንቶኒዮ፣ ማሕበርዊ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይችልም ብለው ከእነዚህ ችግሮች ለመሸሽ መሞከርም መፍትሄ አይሆንም ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እንደተናገሩት ሁሉ፣ ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ ወደ ሌላ ለማስተላለፍ የሚረዱ መንገዶችን ወይም ዘዴዎችን አጥብቆ መያዝ ያስፈልጋል ብለዋል።  ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ለአስተማሪዎች ባቀረቡት አደራ፣ አስተምሪዎች ደፋርና የፈጠራ ችሎታቸውን በግልጽ የሚያሳዩ መሆን ያስፈልጋል እንጂ የሚደብቁ መሆን የለባቸውም ማለታቸውን ክቡር አባ አንቶንዮ ገልጸዋል። በመጨረሻም ትምህርት ስልት ብቻ ሳይሆን ፍሬያማነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚገለጥበት፣ ማሕበራዊ ልምድ በትውልድ ውስጥ የሚታይበት መንገድ እንደሆነ፣ የካቶሊካዊ ስልጣኔ መጽሄት ዋና አዘጋጅ፣ ክቡር አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ አስረድተዋል።    

31 August 2018, 16:45