ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ክፍለ ሃገር የሆነችውን የባሪ ከተማን እንደሚጎበኙ ተገለጸ።  ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ክፍለ ሃገር የሆነችውን የባሪ ከተማን እንደሚጎበኙ ተገለጸ።  

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ክፍለ ሃገር የሆነችውን የባሪ ከተማን እንደሚጎበኙ ተገለጸ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ክፍለ ሀገር ወደ ሆነችው ወደ ባሪ በመሄድ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስታወቁ።

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ክፍለ ሃገር የሆነችውን የባሪ ከተማን እንደሚጎበኙ ተገለጸ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የደቡብ ኢጣሊያ ክፍለ ሀገር ወደ ሆነችው ወደ ባሪ በመሄድ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስታወቁ።

ዮሐንስ መኮንን- ቫቲካን ከተማ

ቅዱስነታቸው ይህን መልዕክት ያስተላለፉት ባለፈው እሁድ ረፋዱ ላይ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ ከተሰበሰቡት ምዕመናንና ሃገር ጎብኝዎች ጋር የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከደገሙ በኋላ ነበር። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች አብያተ ክርስቲያናት መሪዎችና የክርስቲያን ማሕበረሰብ ጋር እንደሚገናኙ አስታውቀዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም ከእነዚህ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎችና መላው ምዕመናን ጋር በመሆን ጸሎታችንን ወደ ፈጣሪ ዘንድ የምናቀብበትና የአስተንትኖ ዕለት ይሆናል ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ ም ወደ ባሪ ከተማ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የአብያተ ክርስቲያናትንና ምእመናኖቻቸውን የሚያድሳትፍ በመሆኑ በእውነትም የአብያተ ክርስቲያናትን አንድነት የሚያመለክት እውነተኛ ምስክርነትና ታሪካዊ እንደሆነ የባሪ ቢቶንቶ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ሞንሲኞር ፍራንችስኮ ካኩቺ ገልጸዋል። ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ሞንሲኞር ፋራንችስኮ በመልዕክታቸው እንደገለጹት በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን አንድነት ለማጠናከር ያለን ምኞት በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሰላም እንዲወርድ አብሮ ከመጸለይ በተጨማሪ በሰላም ማጣት በጦርነት እና ጦርነት በሚያስከትለው አደጋ ለሚሰቃዩት ወገኖቻችንን የእርዳታ እጆቻችንን ለመዘርጋትና ለማጽናናት ይረዳል ብለዋል። የእርዳታ እጆቻችንን ስንዘረጋ ለክርስቲያን ማሕበረሰብ ብቻ ሳይሆን በሕዝቦች መካከል ልዩነት ሳናደርግ በችግር ላይ የወደቁትን በሙሉ ለመታደግ በመሆኑ መላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምታራምደውን በተግባር የሚታይ እውነተኛ ዓለም ዓቀፍነትን ገሃድ ያደርጋል ብለዋል።

በየ እሁዱ ባባሪ ከተማ ዉስጥ እንዲገለገሉባቸው በተሰጣቸው ካቶሊካዊ ቁምሳናዎች የተለያዩ አገሮች ምዕመናን እነርሱም የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የጆርጂያ እና እንዲሁም የሌሎች አገሮች ምዕመናን በየ አገሮቻቸው ስርዓተ አምልኮ መስዋዕተ ቅዳሴን ሲያሳርጉ መመልከት እና በባሕል ልብሶቻቸው ተውበው ማየት ደስ ከባሰኘት በተጨማሪ የአንድ ቤተ ሰብ አባልነታችንን በገሃድ ያሳያል ብለዋል። ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ሞንሲኞር ፋራንችስኮ በማከልም በሕዳር ወር 2009 ዓ ም ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተለሜዎስ አንደኛ የባሪ ከተማን በጎበኙበት ወቅት በከተማው የሚገኘውን የቅዱስ ልበ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን፣ የሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ምእመና ለጸሎት እንዲገለገሉበት በስጦታ መልክ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

የአብያተ ክርስቲያናት የህብረት ጉዞ ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ማግስት፣ በወቅቱ የባሪ ክፍለ ሀገር ጳጳስ የነበሩ ሊቀ ጳጳስ ሞንሲኞር ኒቆዲሞስ፣ ጉባኤውን ተካፍለው ከተመለሱ በኋላ የቅዱስ ኒኮላ ቤተ ክርስቲያንን ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ካበረከቱበት ጊዜ ወዲህ እንደሆነ አስታውሰዋል። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ውሕደት ምሳሌ በተግባር የተገለጸበት መሆኑን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ሞንሲኞር ፋራንችስኮ ገልጸዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የእምነት መሪዎችን፣ በተለይም የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች አብያተ ክርስቲያናትን ያሳተፉ ፍሬያማ ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየቱን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ሞንሲኞር ፋራንችስኮ አክለው ገልጸዋል። በእነዚህ ውይይቶች የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ በርካታ የወንጌላዊያንና የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሲሳተፉ መቆየታቸውን ታውቋል።

ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ሞንሲኞር ፋራንችስኮስ፣ መጭው ቅዳሜ፣ ሀገረ ስብከታቸው ወደ ሆነችው ወደ ባሪ በመጓዝ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፋራንችስኮስ ጋር ተገናኝተው፣ መስዋዕተ ቅዳሴን የሚሳተፉ እንግዶች ብዛት አስመልክተው ሲያስረዱ በስነ ስርዓቱ ላይ የሚገኙት እንግዶች የባሪ ሃገረ ስብከት ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ በኢጣሊያ የሚገኙ የሌሎች ሃገረ ስብከቶች ምዕመናን፣ አብያተ ክርስቲያናትና የውጭ አገሮች ምዕመናንም እንደሚገኙ ገልጸዋል። የባሪ ሃገረ ስብከት እነዚህን በርካታ እንግዶች ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ሞንሲኞር ፋራንችስኮስ በመጨረሻም ከዛሬ 31 ዓመት በፊት የባሪ ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ ሆነው ከካርዲናል ዊልብራንዲስ እና ከመልቦርን ሊቀ ጳጳስ ከብጹዕ ስቲሊያኖስ ጋር በመሆን ሐዋሪያዊ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታውሰዋል። በዚያን ወቅት ምዕመናኖቻቸውን በቅርብ ሆነው የሚከታተሉ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አባቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የክርስቲያኖች አንድነት ምሳሌ በሆነው በቅዱስ ኒኮላ እርዳታና በመታገዝ በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ሕብረት ለማጠናከር በብርታት ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረው፣ የባሪ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እንድሆን በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስሾም የአገልግሎት ሕይወትን በምስጋና መቀበላቸውን ገልጸዋል።              

05 July 2018, 10:27