ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የሲሮ-ማላባር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መሪ ሊቀ ጳጳስ ራፋኤል ታቲል በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የሲሮ-ማላባር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መሪ ሊቀ ጳጳስ ራፋኤል ታቲል በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ር.ሊ.ጳ ፍራችስኮስ ሕብረት መፍጠር ግዴታ ነው አሉ!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለበርካታ ዓመታት በከባድ የሥርዓተ አምልኮ ውዝግብ ተከፋፍላ ከነበረችው የሲሮ-ማላባር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መሪ ጋር በተገናኙበት ወቅት አንድነት መፍጠር እና ለቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች መታዘዝ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰኞ ግንቦት 5/2016 ዓ.ም ከሊቀ ጳጳስ ራፋኤል ታቲል የኬረላ ሲሮ-ማላባር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መሪ ጋር ተገናኝተው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ሊቀ ጳጳስ ታቲል ከሌሎች የሲሮ-ማላባር ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ጋር በመሆን ባደረጉት ንግግር በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን ይህም በኬረላ ቤተ ክርስቲያን ከነበረችበት ጥንታዊ ታሪክ አንስቶ ለተወሰኑ ዓመታት በዚያ ሲቀጣጠል የቆየው የሥርዓተ አምልኮ ክርክር ያካተተ እንደ ሆነም ተገልጿል።

ጥንታዊ ታሪክ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን የጀመሩት ስለ ሲሮ-ማላባር ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ እምነት በመናገር እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “የምትወዷት ቤተክርስትያን አማኞች በህንድ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የሚታወቁት በእምነታቸው እና በአምልኮአቸው ‘ብርታት’ ነው ብለዋል።

ለብዙ ዓመታት የምዕራባውያን ሚስዮናውያን የኬረላን ክርስቲያኖች በአውሮፓውያን ወጎች እንዲከተሉ ለማስገደድ ሲሞክሩ የነበረውን እውነታ በመጥቀስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደተናገሩት “አንዳንድ የእምነት አባላት” “በእናንተ ላይ አሉታዊ ድርጊት ፈጽመዋል”፣ ምክንያቱም የሕንድ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ጥንታዊነት ያለው ነው ብለዋል።

የሲሮ-ማላባር ቤተ ክርስቲያን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አክለውም እንደገለጹት ከሆነ በተለይ ዛሬ “ከአለፈው ጋር የሚያገናኘን ሥር መሠረታችንን መቆራረጥ” የተለመደ በሆነበት ወቅት በጣም አስፈላጊ ነው ያሉ ሲሆን “በምስራቍ ክፍል የሚገኙ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ከጥንታዊ እና አዲስ የመንፈሳዊነት ምንጮች እንድንወስድ ያስችሉናል፤ እነዚህ ለቤተክርስቲያኗ ሕይወት የሚያመጡ ትኩስ ምንጮች ይሆናሉ” ብለዋል።

አንድነት እና ታዛዥነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመካሄድ ላይ ያለውን የአምልኮ ሥርዓት ውዝግብ በመጥቀስ “በቅርብ ጊዜ ለምእመናን ደብዳቤ እና የቪዲዮ መልእክት ልከዋል፣ ይህም አደገኛ ፈተና በአንድ ዝርዝር ላይ እንዲያተኩሩ አስጠንቅቀዋል” ተብሏል።

ይህ አደጋ የሚመጣው “ራስን ከመጥቀስ፣ ይህም የራስን እንጂ ሌላ ዓይነት አስተሳሰብን ወደ አለመስማት ይመራል” ብሏል።

እናም እዚህ ነው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ “ዲያብሎስ ሾልኮ የሚገባው” በማለት የኢየሱስ ፍላጎት እኛ ደቀ መዛሙርቱ “አንድ እንሆን ዘንድ” (ዮሐንስ 17፡2) ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሥርዓተ አምልኮ ጉዳዮች ላይ የቤተክርስቲያኗን ውሳኔ ለመቀበል ፍቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች “እነሱን የሚወዳቸው እና የሚጠብቃቸው የአንድ ትልቅ ቤተሰብ አካል መሆናቸውን እንዲገነዘቡ” እና ሕበረትን ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንሥራ” እና “ያለማሰለስ እንጸልይ” ሲሉ አሳስበዋል።

“ያለ ፍርሃት ተገናኝተን እንወያይ፣ ነገር ግን ከምንም በላይ እንጸልይ፣ ልዩነቶችን የሚያስታርቅና ውጥረቶችን ወደ አንድነት የሚመልስ የመንፈስ ብርሃን፣ አለመግባባቶችን እንዲፈታ ልንጸልይ ይገባል፣ አንድ እርግጠኝነት አለ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጽንኦት ሰጥተው ነበር፡ “ትዕቢት፣ ነቀፋ እና ምቀኝነት ከጌታ የመጡ አይደሉም እናም ወደ ስምምነት እና ሰላም በጭራሽ አይመሩም፣ በእዚህ የተነሳ እነዚህን ተግባራት ልናስወግድ ይገባል” ብለዋል።

ማጠቃለያ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትንሣኤውን የተጠራጠረውን የቅዱስ ቶማስ - ከሞት ከተነሳው ኢየሱስ ጋር ያደረጉትን ቆይታ በማሰላሰል ንግግራቸውን አጠናቀቁ።

ኢየሱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ እራሱን ለቶማስ አሳይቷል እና በመስቀል ላይ እያለ የተጎዳውን ቁስል እንዲመረምር ጋበዘው ያሉት ቅዱስነታቸው “ሐዋርያው ቶማስ እነሱን ሲያስብ እና ጥርጣሬው እና ፍርሃቱ በእግዚአብሔር ታላቅነት ፊት ሲጠፋ ሲመለከት ምን ያህል ተገርሞ ይሆን! ተስፋን የሚያመነጭ፣ ለመውጣት፣ አዲስ ድንበር እንዲሻገር እና በእምነት አባት እንዲሆን ያነሳሳው መገረም ነው። ሁሉንም መሰናክሎች ለማሸነፍ የሚያስችለንን ይህን የእምነት መገረም እናዳብር!” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

13 May 2024, 14:14