ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ 'ቤተክርስቲያን ያለ ቀሳውስት ቁርጠኝነት ወደ ፊት መቀጠል አትችልም’ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የሰበካ ካህናት ለሲኖዶስ” በተሰኘው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ለሚሳተፉ የሰበካ ካህናት ደብዳቤ ልከዋል እና ምንም ያህል ግልጽ ቢመስልም፣ ቤተክርስቲያን ያለ ፍቅር፣ እምነት እና ትጋት መቀጠል እንደማትችል አጽንኦት ሰጥተው በመልእክታቸው ላይ ቅዱስነታቸው አስፍረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ቤተክርስቲያኗ ያለ እናንተ ቁርጠኝነት እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ፊት መጓዝ አትችልም” በማለት በመልእክታቸው ላይ ያስፈሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ ቃል “የሰበካ ካህናት ለሲኖዶስ” ዓለም አቀፍ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ በላኩት ደብዳቤ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ሦስት መቶ የሚሆኑ የሰበካ ካህናት በዚህ ሳምንት ከሮም ወጣ ብሎ በሚገኘው ሳክሮፋኖ በተሰነው ሥፍራ በተካሄደው የአምስት ቀናት ስብሰባ ለመስማት፣ ለጸሎት እና ለማስተዋል የተዘጋጀውን የአጥቢያ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ተልእኮ ላይ ትገኛለች የሚለውን ጥያቄ ለመፍታት ተዘጋጅቶ የነበረ ስብስባ ሲሆን በሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም መጠናቀቁም ተገልጿል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በታላቅ ፍቅር እንዳነጋገራቸው በመግለጽ በዓለም ዙሪያ የወንጌልን ዘር ለመዝራት በየቀኑ ለሚያደርጉት ለጋስ ሥራ ምስጋናቸውን እና አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ቅዱስ አባታችን በእነዚህ ቀሳውስት ፊት ለፊት የተጋፈጡ እውነታዎች ከፍተኛ ልዩነት እንዳላቸው በመገንዘብ የተለያዩ አመለካከቶቻቸውንና ልምዶቻቸውን ማምጣታቸው የሲኖዶሳዊውን ሂደት የበለጠ እንደሚያበለጽግ በመልእክታቸው ላይ አመላክተዋል።

ካህናት በእግዚአብሔር ሕዝብ ሕይወት ውስጥ እንዴት መግባት እንዳለባቸው ያውቃሉ

የሰበካ ካህናት፣ ደስታቸውን፣ ችግራቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን ጨምሮ በእግዚአብሔር ሰዎች ህይወት ውስጥ እንዴት መግባት እንዳለባቸው እንደሚያውቁ አጥብቆ ተናግሯል።

“በዚህም ምክንያት የአንድ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ካህናት ያስፈልጋታል” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ፣ ያለ ካህናት እንዴት በአንድነት መመላለስ እንዳለብን ተምረን ወደ ሲኖዶሳዊ ጎዳና መሄድ አንችልም ብለዋል።

"የሰበካ ካህናት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሕይወት ከውስጥ ያውቃሉ"

“አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶሳዊና ሰባኪ ካልሆኑ፣ ቤተ ክርስቲያንም አትሆንም” ሲሉ ያስጠነቀቁት ቅዱስነታቸው  

በሲኖዶሱ ሂደት ውስጥ የሚያገለግሉትን ማኅበረሰቦች እንዲያጅቡ፣ በተመሳሳይም በጸሎት፣ በማስተዋልና በሐዋርያዊ ቅንዓት ራሳቸውን እንዲሰጡ፣ ብፁዓን አበው ጳጳሳት አሳስበዋል።

ጌታ ያለ ፀጋው ብቻችንን አይተወንም።

ጳጳሱ እንዳሉት ጌታ ዛሬ የመንፈሱን ድምጽ እንድንሰማ እና ወደ እኛ በሚያመለክተው አቅጣጫ እንድንራመድ ይጠይቀናል። "አንድ ነገር እርግጠኛ መሆን እንችላለን: እርሱ ያለ ጸጋው ፈጽሞ አይተወንም" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል የሰበካ ካህናትን በተግባራቸው እና በተልዕኮአቸው ለማነሳሳት ሦስት ሃሳቦችን አቅርበዋል።

በመጀመሪያ፣ ጳጳሱ መንፈሱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ውስጥ የሚዘራውን ልዩ ልዩ ስጦታዎች በሚበልጥ አገልግሎት ልዩ የአገልግሎት መስዋዕትነታቸውን እንዲኖሩ አሳስቧቸዋል።

የህዝብህን ጸጋዎች አጉልቶ ማውጣት

"ብዙ እና ልዩ ልዩ የምእመናን የፀጋ ስጦታዎች፣ የትኛውንም ዓይነት የሰውን ሁኔታ እና መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን በእምነት ፈልጎ ማግኘት አጣዳፊ እና አንገብጋቢ ጉዳይ ነው” በማለት ጽኑ እምነት እንዳላቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው “ብዙ የተደበቁ ውድ ሀብቶችን” ለማብራት እና “በወንጌላዊነቱ ሥራ ውስጥ ብቸኝነት እንዳይሰማችሁ የምዕመኑን መንፈሳዊ ጸጋዎችን ፈልጎ በማግኘት መጠቀም ይኖርብናል ብለዋል።

"ይህንን ስታደርጉ ደግሞ በሌሎች ላይ እውነተኛ አባቶች የመሆንን ደስታ ታገኛላችሁ" ሲሉ ተናግሯል፣ "ይልቁንም በእነሱ ውስጥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ታላቅ እና ውድ እድሎችን ማምጣት ትችላላችሁ” ብለዋል።

ሁለተኛው ጉዳይ በሲኖዶሱ ጉዞ እና በሲኖዶሱ ጉባኤ ሂደት ውስጥ ጠቃሚ ሆኖ ያገኙትን “በመንፈስ የመነጋገር” ዘዴን ለዚሁ ዓላማ በመቀም የጋራ መግባባት ጥበብን እንዲለማመዱ አሳስበዋል።

"ከእሱ ብዙ መልካም ፍሬዎችን እንደምታጭዱ እርግጠኛ ነኝ፣ እንደ ሰበካ ጉባኤ ባሉ የኅብረት መዋቅሮች ብቻ ሳይሆን በሌሎች በርካታ መስኮችም ጭምር" ብለዋል።

ሦስተኛና የመጨረሻው አስፈላጊ ጉዳይ ጳጳሱ እንደ ተናገሩት ከሆነ የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ በመካከላቸው እና ከጳጳሶቻቸው ጋር በመጋራት እና በወንድማማችነት መንፈስ ላይ እንዲመሰረቱ አሳስቧቸዋል።

“መጀመሪያ ልጆች እና ወንድሞች ካልሆንን እውነተኛ አባቶች ልንሆን አንችልም” ብለዋል ፣ “እናም በአደራ በተሰጠን ማህበረሰቦች ውስጥ ህብረትን እና ተሳትፎን ማጎልበት አንችልም ፣ “ከሁሉም በፊት እነዚያን እውነታዎች እስካልተወጣን ድረስ በራሳችን መካከል መልካም ግንኙነት እስካልመሰረትን ድረስ" ለሌሎች መልካም ምሳሌ መሆን በፍጹም አንችልም ብለዋል።

' ከጎንህ ነኝ'

ሁለቱም ሲኖዶሳዊ እና ሚስዮናውያን ቤተ ክርስቲያን እና የ2021-2024 ዓ.ም የሲኖዶስ ሂደት፣ “ለሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን፡ ሕብረት፣ ተሳትፎ፣ ተልእኮ” የሰበካ ካህናትና ድምጻቸው እንደሚያስፈልግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ስለዚህም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “የሰበካ ካህናት ለሲኖዶስ” በተሰኘው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ የተሳተፉትን በመጀመሪያ በመካከላቸው እና ወደ አገራቸው ሲመለሱ ከየሰበካ ካህናት ጋር በመሆን የሲኖዶሳዊ ሚስዮናውያን እንዲሆኑ ጋብዘዋል።

“ውድ ወንድሞች፣ እኔ ራሴ በምሳተፍበት በዚህ ሂደት ከጎናችሁ ነኝ” በማለት ቅዱስ አባታችን አረጋግጠዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን በመስጠት፣ ጸሎታቸውን በመጠየቅ እና ሁልጊዜም መንገድ ከምታሳየን ከእመቤታችን ጋር እንዲቀራረቡ በማበረታታት አጠቃለዋል።

"ውድ ወንድሞቼ በዚህ ሂደት ከጎናችሁ ነኝ" ማለታቸውም ተገልጿል።

 

03 May 2024, 11:37