ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ‘ጽናት በችግር ጊዜያት ጥንካሬን፣ ለበጎ ተግባር ክትትልና ትጋትን የሚሰጥ ምግባር ነው’ አሉ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት የሚያደርጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች በስፍራው እንደሚሰበሰቡ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው ረቡዕ ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በአዲስ መልክ ክፉ እና መልካም ስነ-ምግባር በሚል ዓብይ አርዕስት ጀምረውት ከነበረው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ‘ጽናት’ በሚል ንዑስ አርዕስት ባደረጉት የክፍል 13 አስተምህሮ “ጽናት በችግር ጊዜያት ጥንካሬን፣ ለበጎ ተግባር ክትትልና ትጋትን የሚሰጥ ምግባር ነው” ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በእለቱ የተነበበው የምጽሐፍ ቅዱስ ክፍል

“ጆሮህን ወደ እኔ መልሰህ ስማኝ፤ ፈጥነህ አድነኝ፤ መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ ታድነኝም ዘንድ ምሽግ ሁነኝ። አንተ መጠጊያዬ ነህና፣ በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ። እግዚአብሔርን ተስፋ የምታደርጉ ሁሉ፤ በርቱ፤ ልባችሁም ይጽና (31፡2.4.24)።

ክቡራት እና ክቡራን የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ሚያዝያ 02/2016 ዓ.ም ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ትርጉሙን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን...

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የዛሬው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የሚያተኩረው መሰረታዊ ምግባራት ከሚባሉት ውስጥ አንዱ በሆነውና ጽናት በተሰኘው ሦስተኛው ምግባር ላይ ያተኮረ ነው። በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ውስጥ  በተሰጠው መግለጫ እንጀምር፡- “ጽናት በችግር ጊዜያት ጥንካሬን፣ ለበጎ ተግባር ክትትልና ትጋትን የሚሰጥ ምግባር ነው። ፈተናን ለመቋቋምና በግብረገባዊ ሕይወት የሚያጋጥሙ መሰናክሎችን ለማለፍ ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራል።  ጽናት አንድ ሰው ፍራሃትን፣ የሞትን ፍራቻ እናኳን ሳይቀር ለማሸነፍ ፈተናና ስደትን ለመቋቋም ያስችለዋል” (1808) በማለት ስለጽናት ይናገራል።

እዚህ ላይ እንግዲያውስ በጣም ጥሩ "የተጋድሎ" ስነ-ምግባር አለ ለማለት እንችላለን። የመጀመሪያው መሰረታዊ ስነምግባር የሆነው አስተዋይነት በዋነኝነት ከሰው ምክንያት ጋር የተያያዘ ከሆነና ፍትህ ለሌሎች ሰዎች የሚገባቸውን ነገር የመስጠት ጽኑና ያልተቆጠበ ፈቃድን የምያመለክት ቢሆንም፣ ይህ ሦስተኛው ጽናት የተሰኘው መሰረታዊ ምግባር ብዙውን ጊዜ በሊቃውንት ደራሲያን የጥንት ሰዎች ዘንድ "ግልፍተኛ የሆነ ከፍተኛ መሻት” ብለው ይጠሩታል። የጥንት አስተሳሰብ ሰውን ስሜት አልባ አድርጎ አላስቀመጠም ነበር፣ ሰው ያለ ስሜት እሱ ድንጋይ ይሆናል። ምኞቶችም የግድ የኃጢአት ቅሪት አይደሉም፣ ነገር ግን የተማሩ፣ የተነደፉ፣ በጥምቀት ውሃ የሚነጹ ወይም የተሻሉ በመንፈስ ቅዱስ እሳት መሆን አለባቸው። ድፍረት የሌለው ክርስቲያን የራሱን ጥንካሬ ወደ መልካም የማይለውጥ ማንንም የማያስቸግር ክርስቲያን ከንቱ ክርስቲያን ነው። ኢየሱስ የሰውን ስሜት የማያውቅ እና የሰውን ማንነት ጥርት ባለ መልኩ በግልጽ የማያውቅ አሳቢ አምላክ አይደለም። ነገር ግን እርሱ በተቃራኒው ጎራ ነው የሚሰለፈው።  የወዳጁን አልዓዛርን ሞት በሰማበት ወቅት ፊቱ በእንባ ጠብታዎች ተሞላ፣ እናም የእሱ ከፍተኛ እና የጋለ ስሜት በአንዳንድ ንግግሮቹ ውስጥ ይታያል፣ ለምሳሌ፡- “እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኰስ ነው፤ አሁኑኑ ቢቀጣጠል ምንኛ ደስ ባለኝ” (ሉቃስ 12:49) እናም በቤተ መቅደሱ የሚሸጡ እና የሚለውጡ ሰዎችን በተመለከተ ጊዜ በኃይል ምላሽ እንደ ሰጠ እናመለከታለን (ማቴ. 21፡12-13)።

አሁን ግን በህይወታችን ፍሬያማ እንድንሆን የሚረዳን የዚህን ጠቃሚ በጎነት ነባራዊ መግለጫ እንፈልግ። የጥንት ሰዎች - ሁለቱም የግሪክ ፈላስፎች እና የክርስቲያን የነገረ-መለኮት ሊቃውንት - በጽናት ባህሪይ ምግባር ውስጥ ሁለት ነገሮችን እናገኛለን አንደኛው በቀጥታ ተሳታፊ ያልሆነ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ንቁ ተሳታፊ ነው። የመጀመሪያው በራሳችን ውስጥ ይመራል። በስጋት፣ በቁጭት፣ ጭንቀት፣ በጥፋተኝነት ስም የሚሄዱ የውስጥ ጠላቶች አሉ፡ ውስጣችን ውስጥ የሚቀሰቅሱ እና በአንዳንድ ሁኔታዎች ሽባ ያደርጉናል። ፈተናውን ገና ሳይጀምሩ ስንት ተዋጊዎች ይሸነፋሉ! ጥንካሬ በመጀመሪያ በራሳችን ላይ ድል የማድረግ ስሜት መጎናጸፍ ነው። በውስጣችን የሚነሱት አብዛኛዎቹ ፍርሃቶች ከእውነታው የራቁ ናቸው እና በጭራሽ እውን አይደሉም። እንግዲያውስ መንፈስ ቅዱስን መለመን እና ሁሉንም ነገር በትዕግስት በጽናት መጋፈጥ ይሻላል፡ ቀስ በቀስ፣ በመጀምሪያ ደረጃ በደረጃ አንድን ችግር መፍታት፣ በምንችለው መጠን፣ ነገር ግን ብቻችንን ሊሆን አይገባም! በእርሱ ከታመንን እና መልካሙን በቅንነት ከፈለግን ጌታ ከእኛ ጋር ነው። ከዚያም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እኛን የሚከልለን መንፈሳዊ ትጥቅ የሚሰጠን እና መንፈሳዊ ጥበቃ የሚያደርግልን በእግዚአብሔር መሰጠት ላይ መተማመን እንችላለን።

እናም ከዚያ የጽናት ምግባር የሚቀጥል ሁለተኛ እንቅስቃሴ አለ ፣ በእዚህ ጊዜ የበለጠ ንቁ ተፈጥሮ ያስፈልጋል። እንደ ውስጣዊ ፈተናዎች የውጭ ጠላቶች አሉ፣ እነሱም የህይወት ፈተናዎች፣ ስደት ችግሮች ያልጠበቅናቸው እና እኛን የሚያስደንቁ ናቸው። በእርግጥ በእኛ ላይ ምን እንደሚደርስ ለመተንበይ ልንሞክር እንችላለን፣ ነገር ግን በትልቅ ደረጃ እውነታው የማይታለፉ ክስተቶች ሊኖሩት ይችሉ ይሆናል፣ እናም በዚህ ባህር ውስጥ አንዳንድ ጊዜ ጀልባችን በማዕበል ይናወጣል። ከእዚያም ጽናት ያላቸው የማይፈሩ ወይም የማይደፈሩ መርከበኞች ያደርገናል።

የጽናት ምግባር በዓለም ላይ ያለውን የክፋት ፈተና በቁም ነገር ስለሚመለከት መሰረታዊ በጎነት ነው። አንዳንዱ የሌለ አስመስሎ፣ ሁሉም ነገር መልካም እየሄደ ነው ብሎ ሊያስብ ይችል ይሆናል፣ የሰው ፈቃድ አንዳንድ ጊዜ አይታወርም፣ ሞት የሚያመጡ የጨለማ ኃይሎች በታሪክ ውስጥ አይደበቁም። ነገር ግን እኛ በከፊል ሰለባ የሆኑብን እና ከፊል ወንጀለኞች የሆንባቸው እኩይ ተግባራት፡ ጦርነትን፣ ዓመፅን፣ ባርነትን፣ የድሆችን ጭቆና፣ ፈውስ ያላገኙ ቁስሎች እና አሁንም ድረስ ያሉብንን እኩይ ተግባራት ለማወቅ በታሪክ መጽሃፍ፣ ወይም በሚያሳዝን ሁኔታ ጋዜጦችን ማየት በቂ ነው፣ በየስፍራው መድማት ይታያል። የጽናት ምግባር ለዚህ ሁሉ ምላሽ እንድንሰጥ እና “አይሆንም” ብለን እንድንጮህ ያደርገናል። በምቾት በምዕራቡ ዓለም፣ ሁሉን ነገር የሚያረሰርስ በሚመስልበት ዓለም፣ ፍጽምናን ፍለጋ ወደ ቀላል ተፈጥሮአዊ ልማት የለወጠው፣ ሁሉም ነገር ተመሳሳይ ስለሚመስል ትግል የማያስፈልገው፣ አንዳንድ ጊዜ ለነቢያት ያለን ጤናማ ናፍቆት ይሰማናል። ነገር ግን ይህንን ነገር የሚያጨናግፉ ባለራዕይ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው። ከተቀመጥንበት ለስላሳ ቦታ ቀስቅሶ “ለምን” ለክፋት እና ወደ ግዴለሽነት ወደሚያመራው ነገር ሁሉ በቆራጥነት እንድንደርስ የሚያደርግ ሰው ያስፈልጋል።

እንግዲያውስ በወንጌል የኢየሱስን ጥንካሬ ደግመን እንወቅ እና ከቅዱሳን ምስክርነት እንማር።

ይህንን ዝግጅት በድምጽ ለማዳመጥ ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ
10 April 2024, 15:27

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >