ፈልግ

የብሪታንያ መንግስት ህገ-ወጥ የስደት ህግን በመቃወም የተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የብሪታንያ መንግስት ህገ-ወጥ የስደት ህግን በመቃወም የተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ  (ANSA)

የኢየሱሳዊያን ማህበር በብሪታኒያ ውስጥ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ኢሰብአዊ አያያዝ አውግዟል።

የእንግሊዙ የኢየሱሳዊያን ማህበር ያወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው ፥ በኬንት የሚገኘው ከአገልግሎት ውጭ የሆነ የጦር ሰፈር አሁን ላይ ወደ ጥገኝነት መጠየቂያ ማቆያ ካምፕነት የተቀየረው ፥ የናፒየር ባራክስ ነዋሪዎች ላይ ያለው በኢሰብአዊ አያያዝ አሰራሩ ስለተተቸ ፥ የብሪታንያ መንግስት እንዲዘጋው እና ለጥገኝነት ጠያቂዎቹ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተከበረ መጠለያ እንዲሰጥ አሳስቧል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ አዲስ አበባ

የብሪታንያ መንግስት አወዛጋቢው የህገ-ወጥ ስደት ህግ ፥ በተቃዋሚ ፓርቲዎች እና በሰብአዊ ድርጅቶች ከፍተኛ ትችት ውስጥ የገባ ሲሆን ፥ በዚው ጉዳይ የኢየሱሳዊያን ማህበር የስደተኞች አገልግሎት ረቂቅ ዘገባ አውጥቷል። ዘገባውም ይህ ረቂቅ ህግ ከወጣ በኋላ በእንግሊዝ ውስጥ የወደፊት የጥገኝነት እጣ ፈንታ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ነው ተብሏል።

እ.ኤ.አ. በመጋቢት 29 የተለቀቀው ይህ ዘገባ ፥ የናፒየር ባራክስ ጥገኝነት ጠያቂዎች ያጋጠሟቸውን ኢሰብአዊ ድርጊቶች ያወግዝ እና ይህ በኬንት ውስጥ የሚገኘው የጦር ካምፕ የነበረ በጊዜያዊነት ወደ ጥገኝነት መጠለያነት የተቀየረው እ.አ.አ. በመስከረም 2020 መሆኑን ይገልፃል። በመስከረም 2021 የብሪታኒያ መንግስት የዚህን ቦታ አገልግሎት ለተጨማሪ አምስት አመታት ለማራዘም የአደጋ ጊዜ ሃይልን አሰማርቷል።

እርምጃው የተወሰደው በቦታው ላይ በሚሰጡ አገልግሎት አሰጣጦች ላይ ከፍተኛ ትችት ቢሰነዘርባቸውም እና ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቦታው ለአገልግሎት በቂ እንዳልሆነ ብይን ቢሰጥም ፥ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ፅህፈት ቤቱ ህገወጥ ተግባሩን መስራቱን ቀጥሎበታል። እንዲሁም፣ በችሎቱ መሰረት ፥ ምንም እንኳን ይህ ማራዘሚያ አስፈላጊ ነው ቢባልም ፥ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የሚደረገውን ምክክር ወደ ጎን በመተው የአደጋ ጊዜ ሃይልን መጠቀሙ አግባብነት የለውም ተብሏል ።

 ኢሰብአዊ እውነታ

“የናፒየር ባራክ ኢሰብአዊው እውነታ” በሚል ርእስ የኢየሱሳዊያኑ ማህበር ያወጣው ዘገባ የተመሰረተው በድርጅቱ የሥራ ባልደረቦች እና በ2022 ካምፑ ዉስጥ ከነበሩት ሰዎች ጋር በተደረጉ ጥልቅ ውይይቶች ላይ ነው። ምንም እንኳ ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን በኋላ ፥ እነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች መፍትሄ ማግኘት ቢገባቸውም እስካሁን ተግባራዊ አልሆኑም ተብሏል።

የኢየሱሳዊያን የስደተኞች አገልግሎት ከጥቅምት 2020 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ያህል ለናፒየር አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

‘በመሬት ላይ የተከሰተው ነገር ይላል’ የዘገባው ማጠቃለያ ‘በጣም አስጨናቂ ነበር ፥ ጣቢያው የጨለመ እና የተበላሸ ፣ አካባቢው ደህንነቱ ያልተጠበቀ ፣ ማረፊያው በጣም የተጨናነቀ ስለነበር በነዋሪዎች የአእምሮ ጤና ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል’ ብሏል።

“ከ2 ወር በላይ በናፒየር ጦር ሰፈር ነበርኩ ፥ አሁን ያሳለፍኩትን ወደ ኋላ እየተመለከትኩ ነው ፥ ያ ተሞክሮ ምን ያህል አሰቃቂ እንደነበር አስባለሁ። አጠቃላይ የጥገኝነት ሂደቱ አሰቃቂ ነበር፣ እና የናፒየር ሰፈር የዚህ ምልክት ነጸብራቅ ነው”

ከእነዚህ ንግግሮች የተገኙ ቁልፍ ግኝቶች የሚያሳዩት ፥ ሰዎች ያለአንዳች ዕውቀት በመደበኛነት ወደ ካምፑ እንዲመጡ መደረጉ ከፍተኛ ጭንቀት እንዲሰማቸው ያደርጋል ፥ ከባድ ወታደራዊ እና እስር ቤት መሰል የኑሮ ሁኔታዎች ፣ መጨናነቅ እና ግላዊነት የሌሉበት ፥ የጤና እንክብካቤ ለማግኘት አለመቻል እንቅፋቶች እና የህግ ምክር አገልግሎት አለመኖር ፥ እንዲሁም በጥር 2021 መጨረሻ ላይ በካምፑ ላይ ከባድ የእሳት አደጋ ከተነሳ በኋላ የደህንነት ጉዳዮች አለመፈታታቸው የጉዳዩን አሳሳቢነት ይገልፃል ተብሏል።

ከእነዚህ ግኝቶች አንፃር የወጣው ባለ 35 ገፆች ዘገባ ፥ የእንግሊዝ መንግስት የናፒየር ባራክን ካምፕ በአስቸኳይ እና በቋሚነት እንዲዘጋ በማሳሰብ ፥ ሰፊ ተቋማዊ የጥገኝነት መጠየቂያ ካምፕ ለማድረግ ያቀደውን ሙሉ በሙሉ በመተው ፥ በምትኩ ለጥገኝነት ጠያቂዎቹ በእንግሊዝ ማህበረሰብ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተከበረ መጠለያ እንዲያቀርብላቸው አሳስቧል። ይህም ጥገኝነት ለሚፈልጉ ሰዎች እና ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ የአእምሮ ጤና የተሻለ ስለሆነ እና ውህደትንም ስለሚያመጣ ነው ይላል።

“እንዲህ ዓይነቱ መጠለያ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ይጎዳል ፣ እረፍት የሚነሳ እና ከሰፊው ማህበረሰብ እንዲርቁ ያደርጋል ፥ እንዲሁም ውህደትን አያበረታታም”

የኤጲስ ቆጶሱ 'ባልእንጀራህን እንደራስህ ዉደድ’ ሰነድ

የኢየሱሳዊያኑ ዘገባ የወጣው የእንግሊዝ እና የዌልስ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ያወጣውን ፥ ፖሊሲ አውጪዎች የስደተኞች እና የጥገኝነት ጠያቂዎችን ሰብዓዊ ክብር እንዲያስከብሩ የሚጠይቅ በቅርቡ ያሳተመውን ህትመት ተከትሎ እና ማንኛውም የስደተኞች ህግ የሚተገበረው የእያንዳንዱን ሰው ተፈጥሮአዊ ክብር በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት ያሳስባል። 'ባልእንጀራህን ውደድ' በሚል ርዕስ የወጣው ይህ ህትመት ፥ ማንኛውንም የስደተኞች ህግ ሊመሩ የሚገባቸው በካቶሊክ ማህበራዊ ትምህርቶች እና በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትምህርተ ክርስቶስ ላይ የተመሰረቱ 24 መርሆችን ዝርዝር አቅርቧል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ አዲሱ የኢሚግሬሽን እቅድ ላይ እየበዙ የመጡ ትችቶች

 ህገ ወጥ ስደተኞች በእንግሊዝ መተላለፊያ መንገዶች ላይ በትናንሽ ጀልባዎች የሚደረጉትን አደገኛ ጉዞ እንዲሁም ወደ እንግሊዝ እንዳይገቡ የሚከለክለውን እና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አልያም ‘ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ’ የተባሉት ሶስተኛ ሃገሮች እንዲሄዱ የሚያስገድደውን አዲሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክን የስደተኞች ህግ በመቃወም የሚወጡ ህትመቶች እየበዙ መምጣታቸው ተነግሯል።

እርምጃው ከዓለም አቀፍ ህግጋት ከሆኑት ፥ የአውሮፓ የሰብአዊ መብቶች ኮንቬንሽን ስምምነቶች ውስጥ እንደ የስደተኞች ስምምነት ፣ የህጻናት መብቶች ስምምነት ፣ የስደተኞች ግሎባል ኮምፓክት የሆኑት እናአስተማማኝ ፣ ሥርዓታማ እና መደበኛ ፍልሰት ከመሳሰሉት ጋር መከበሩን በሚመለከት የህግ ጥያቄዎችን እንዲሁም በርካታ ስነ-ምግባራዊ ጥያቄዎችን አስነስቷል።

ከ60 የሚበልጡ የብሪታኒያ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ የሌበር ፣ የሊበራል ዴሞክራቶች እና የአረንጓዴው ፓርላማ አባላት እና ምሁራን የቀረበው ህግ አላስፈላጊ ሞት እንደሚያስከትል እና ዘመናዊ ባርነትን ያቀጣጥላል በማለት ህጉ እንዲሰረዝ ለሱናክ በደብዳቤ ጠይቀዋል። ከፈራሚዎቹ መካከል የዓለም አቀፍ ፀረ-ባርነት ህብረት እና በእንግሊዝ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የስደተኞች እና የስደተኞች መብት ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ስቲቭ ቫልዴዝ ሲሞንስ ይገኙበታል።

 

 

31 March 2023, 14:24