ፈልግ

የሺዓ መሪ ሞክታዳ አል-ሳድር ደጋፊዎች የሺዓ መሪ ሞክታዳ አል-ሳድር ደጋፊዎች  (ANSA)

የሺዓዎች መሪ ሞክታዳ አል-ሳድር፣ በኢራቅ ውስጥ ሰላም ከተፈለገ የጦር መሣሪያን ማንሳት አያስፈልግም አሉ

በርካታ ሰዎች ከሞቱበት እና ከቆሰሉበት የሰኞ ነሐሴ 23/2014 ዓ. ም. ኃይለኛ ግጭት በኋላ የኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ሰላም የሰፈነባት እና የተረጋጋች እንደሆነ ሲታወቅ፣ በኢራቅ የሺዓ መሪ ሞክታዳ አል-ሳድር፣ ደጋፊዎቻቸው በባግዳድ አረንጓዴ ቀጣና ተብሎ የሚታወቀውን አካባቢ ለቀው መውጣታቸው ቢገልጹም አገሪቱ ከብዙሃኑ የሺዓዎች ውስጣዊ ቀውስ መቼ እንደምትወጣ አይታወቅም ተብሏል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ኢራቃውያንን ይቅርታ የጠየቁት በኢራቅ የሺዓዎች መሪ ሞክታዳ አል-ሳድር፣ ሥራ በመልቀቃቸው ምክንያት በባግዳድ ውስጥ ብጥብጥን እና አመጽ መቀሰቀሱን ገልጸው፣ በሰላማዊ ሰልፈኞች እና በፖሊስ ሃይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት 30 ሰዎች መሞታቸውን እና 700 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል። አል ሳድር ለተከታዮቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የጦር መሣሪያ መጠቀምን ካወገዘ በኋላ በባግዳድ ከተማ 'አረንጓዴ ቀጠና' የመንግሥት ተቋማት እና ኢምባሲዎች ባሉበት አካባቢ ጥቃት ያደረሱት ታማኞቻቸው በሕዝብ እና በመንግሥት ንብረት ጥፋትን የማያስከትል ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚቀርቡለት አቤቱታዎች የኢራቅ ጦር የሰዓት እላፊ አዋጁን እንዲያነሳ መጠየቁ ታውቋል። ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚንስትር ሙስጠፋ ካዚሚ የአል-ሳድርን ሁከት ለማስቆም ያቀረቡትን ጥያቄ “የአገር ፍቅር ምሳሌ” እንደሆነ ገልጸው፣ የሞክታዳ አል-ሳድር ተከታዮቹ ከቅርብ ሳምንታት በፊት በንብረት ላይ ጥፋት፣ ድንኳኖችን ማፍረስ መጀመራቸውን ለፓርላማቸው ተናግረዋል።

ከፖለቲካው ዓለም የመራቅ ስልት

አል ሳድር ከፖለቲካው መድረክ ለመውረድ እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን፣ ውሳኔያቸው በደጋፊዎቻቸው መካከል ለተነሳው ግጭት ምክንያት መሆኑ ሲነገር፣ የአገሪቱ የፖለቲካ ማዕቀፍም ለአንድ ዓመት ያህል በቆመበት መቅረቱ ታውቋል። ባለፈው ጥቅምት በተደረገው ድምጽ አሰጣጥ፣ አል ሳድር አብላጫውን መቀመጫ ያገኙ ቢሆንም መንግሥት መመስረት ሳይችሉ ቀርተዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከታዩት አስከፊ ቀውሶች መካከል አንዱን ሳያቆሙ የሺዓ መሪው መንግሥት እንዲፈርስ መጠየቃቸውም ይታወሳል። ሆኖም ግን የአል-ሳድርን ትክክለኛ የስልጣን መልቀቂያ ፍላጎትን በተመለከተ በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች መካከል ጥርጣሬ ነግሶ የቆየ ስሆን፣ ሀገሪቱን ወደ ምርጫው መመለስ ባለመቻላቸው መንግሥትን በሰላማዊ ሰልፍ ከስልጣን ለማውረድ ይሞክሩ ነበር ተብሎ ታስቧል። በዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጥናት ተቋም ከፍተኛ አማካሪ የሆነው እና የመካከለኛው ምሥራቅ ተመራማሪ ጋዜጠኛ ኡጎ ትራምባሊ፣ ጉዳዩን በግልፅ ሲያብራ፥ “አል ሳድር ከፖለቲካ መሰናበቻው ልቦለድ ነው ብሎ፣ ከመንግሥት ውጭ በመቆየት ምርጫው እንዲስተካከል ለመጠየቅ እና ልዩ የአስተዳደር መንገድን ለማበጀት ቢፈልጉም ነገር ግን ሕገ መንግሥቱ እንደማይፈቅድላቸው፣ ይህን ለማስፈጸም ድምጽ የሚሰጠው ፓርላማ ካልሆነ ምርጫ ማካሄድ የማይቻል መሆኑን አስረድቷል።

በሺዓዎች መካከል ግጭት የመቀስቀስ ስጋት

በአሁኑ ወቅት ሁኔታዎች ​​የተረጋጉ ይመስላል ያለው ጋዜጠኛ ኡጎ ትራምባሊ፣ “የአል-ሳድር ሚሊሻዎች 60 ሺህ ሰዎችን ያቀፈ እና ብዙዎቹም የሠራዊቱ አካል መሆናቸውን ገልጸዋል። አደጋው ቢያንስ ከሌሎች አካላት ጋር ማለትም ክርስቲያኖች፣ ኩርዶች እና ሱኒዎች ከሺዓዎች ጋር በሚደረግ ግጭት ሊሆን እንደሚችል ትራምባሊ አስረድተው፣ ግጭቱ በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት መካከል በአንጻራዊነት ሊከሰት እንደማይችል፣ በክርስቲያን ሚሊሻዎች ላይ ክርስቲያን ሚሊሻዎችን ለማነሳሳት ወደ ሊባኖስ መሄድ እንደሚያስፈልግ እና ይህም የማይታሰብ መሆኑን፣ በኢራቅ በተካሄዱ የ15 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነቶች ወቅት በሺዓ ሚሊሻዎች እና በሱኒ ሚሊሻዎች መካከል ጦርነት መካሄዱን አስረድቷል።

የኢራን ሚና ምን ሊሆን ይችላል?

በሁከት ምክንያት ከኢራቅ ጋር የሚያዋስናት ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኢራን በአሁኑ ወቅት ከፍት ያደረገችው ሲሆን፣ ዋናው ጉዳይ የኒውክሌር ስምምነቶችን ማዳን ስትችል ቴህራን ራሷል ማግለል እንደምትችል የገለጸው ጋዜጠኛ ኡጎ ትራምባሊ፣ የኒውክሌር ስምምነትን ማጽደቅ፣ በኢራን የተጣለው ማዕቀብ ማብቃት እንደሆነ ገልጾ፣ የኢራን ኢኮኖሚ ውድቀት ላይ መሆኑን አስረድቷል። በተጨማሪም አስቀድሞ በ 2015 ውስጥ አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና እና የአውሮፓ ኅብረት የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም የሚያስቆም ስምምነትን እንደሚፈርሙ እርግጠኞች የነበሩ ቢሆንም ይህ አለማሳካቱን ገልጿል።  ስምምነት ከተደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ኢራን በየመን፣ ሶሪያ፣ ሊባኖስ፣ ከሊባኖስ ሄዝቦላህ ጋር፣ በኢራቅ ከሃማስ እና ከፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ ጋር፣ በጋዛ ውስጥ "ጂኦ-ፖለቲካዊ" ተነሳሽነት መጨመሯን ትራምባሊ አስረድቶ፣ እስከ ዛሬ ድረስ “ኢራቅ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች ከሚቀሰቀሱ ውስጣዊ ቀውሶች መቼ ነጻ ልትወጣ እንደምትችል መገመት አይቻልም” ብሏል።

31 August 2022, 16:59