ፈልግ

የዓለም የውሃ ቀን እ.አ.አ በመጋቢት 22/2022 ዓ.ም ይከበራል የዓለም የውሃ ቀን እ.አ.አ በመጋቢት 22/2022 ዓ.ም ይከበራል  

“የውሃ አስተዳደር ከቤት ይጀምራል”!

የተባበሩት መንግስታት የአለም የውሃ ልማት ሪፖርት ዋና አዘጋጅ የሆኑት ሪቻርድ ኮኖር እ.አ.አ በመጋቢት 22/2022 ዓ.ም ለሚከበረው የአለም የውሃ ቀን በፊት ባውጡት ሪፖርት ውሃን እና ሀብቱን በዘላቂነት መጠቀምን ያበረታቱ ሲሆን ይህም በዚህ አመት ወደ የከርሰ ምድር ውሃ ትኩረት ለመሳብ የተደረገ ጥረት ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“ውሃ መቆጠብ ትንሽ ነገር ሊመስል ይችላል፣ነገር ግን ሁሉም የድርሻውን ሲወጣ ትልቅ ነገር ይሆናል…ውሃ በምትቆጥብበት ጊዜ፣ በአካባቢያችሁ ያለውን ሀይቅ ወይም ጅረት እየጠበቅክ ብቻ አይደለም። ለአየር ንብረት እና ለፕላኔቷ ለሥነ-ምህዳር ከዚህ የበለጠ እየሰራን መሆን ይኖርበታል” ማለታቸው ተገልጿል።

በተባበሩት መንግስታት የአለም የውሃ ልማት ሪፖርት ዋና አዘጋጅ የሆኑት ሪቻርድ ኮኖር ይህ መልእክት በየአመቱ እ.አ.አ በመጋቢት 22 ቀን በሚከበረው የአለም የውሃ ቀን ለሁሉም የምድራችን ሰዎች ያስተላለፉት መልእክት ነው። ይህንን አስፈላጊ ሀብት ለመጠበቅ እና ለማስተዳደር ስለምንጠቀምበት የውሃ አጠቃቀም ግንዛቤ እንድናገኝ ይጋብዙናል።

ውሃ እና ንፅህና

የዓለም የውሃ ቀን በየዓመቱ የሚከበረው በዓለም ዙሪያ በጣም ድሃ የሆኑትን ጨምሮ በአሁኑ ጊዜ የንፁህ ውሃ አገልግሎት ሳያገኙ የሚኖሩ ከ2 ቢሊዮን በላይ ሰዎች ግንዛቤን ለመሳብ ነው።

አቶ ኮኖር በተለይ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ እና ደቡብ ምስራቅ እስያ ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች ጎልቶ የሚታየው የውሃ ችግር ብዙ ሰዎች ንጹህ ውሃ የማያገኙበት መሆኑን ጠቁመዋል።

የዚህ ቀውስ ሌላው ገጽታ 4 ቢሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የንፅህና መጠበቂያ ቦታዎች ስለሌላቸው እና ከ 800 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት አሁንም በቂ የመጸዳጃ ሥፍራዎች እና የንፅህና አጠባበቅ ማዕከሎች የላቸውም። የውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ ዘላቂ ልማት ግቦች ያስፈልጋሉ።

የከርሰ ምድር ውሃ

የዓለም የውሃ ቀን 2022 ጭብጥ “የከርሰ ምድር ውሃ - የማይታየውን እንዲታይ ማድረግ” ነው የሚለው ነው።

ጭብጡ በከርሰ ምድር ውሃ ውስጥ በውሃ ውስጥ እና ከመሬት ወለል በታች ባሉ የእርጥበት አዘል ዞኖች ውስጥ ያለውን ሁኔታ ይገልጻል። የከርሰ ምድር ውሃ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ሃብቶቻችን አንዱ ነው ምንም እንኳን ምናልባት ባናየውም ወይም እዚያ እንዳለ ባንገነዘበውም፤ ስለዚህ የማይታየውን እንዲታይ ለማድረግ የተዘጋጀ ጭብጥ እንደ ሆነም ተገልጿል።

አቶ ኮኖር የከርሰ ምድር ውሃ በብዙ የገጠር ህዝቦች ውስጥ ዋነኛው እና ተመጣጣኝ የውሃ ምንጭ እንደሆነ እና በነዚህ ማህበረሰቦች ልማት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ያብራራሉ። ስለዚህ በተመጣጣኝ ዋጋ ወይም በነጻ መገኘቱን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። በከተሞች ውስጥ እንኳን፣ በአሁኑ ጊዜ በግምት 50 በመቶው የከተማ ህዝብ በከርሰ ምድር ውሃ ላይ ስለሚተማመን በከርሰ ምድር ውሃ ላይ ያለው ጥገኛነት እየጨመረ ነው።

የከርሰ ምድር ውሃን ዘላቂ አጠቃቀም

በፕላኔታችን ላይ ያለውን አብዛኛው ውሃ የሚይዘው ጨዋማ ውሃ ለሰው ልጅ በቀላሉ የማይመጥን ቢሆንም፣ 99% የሚሆነው የንፁህ ውሃ ፍጆታ የከርሰ ምድር ውሃ ከፍተኛ ጥራት ያለው እና በጣም ዝቅተኛ ህክምና የሚያስፈልገው ነው።

አቶ ኮኖር እንዳሉት የከርሰ ምድር ውሃ ከገጸ ምድር ውሃ ጋር ሲወዳደር በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ባለመጎዳቱ ተጨማሪ ጠቀሜታ አለው፤ ምክንያቱም ከመሬት በታች ስለሆነ አይተላለፍም አይተንም። ይህንን ውድ ሀብት በዘላቂነት ጥቅም ላይ ማዋል እና ከብክለት መከላከል አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

“የከርሰ ምድር ውሃን ስትጠቀም በዘላቂነት መጠቀም አለብህ። ሁሉንም ከአንድ ቦታ ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ማፍሰስ አይችሉም። መዘርጋት አለብህ እና የከርሰ ምድር ውሃ በራሱ፣ በከርሰ ምድር ውሀ ዑደቶች ውስጥ እራሳቸውን እንዲሞሉ መፍቀድ አለብህ” ብሏል።

ውሃ፣ ግጭቶች እና ሰላም

ውሃ፣ በተለይም ንፁህ ውሃ፣ ለሰው ልጅ ሕይወት አስፈላጊ ነው፣ እናም ብዙ ቢሆንም የተገደበ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄደው ውጥረቶች አልፎ ተርፎም የብጥብጥ ምንጭ ሊሆን ይችላል፣ በተለይም በታላላቅ የውሃ አካላት ላይ ያሉ ሀገራት እንቅስቃሴ የታችኛው ተፋሰስ ዝቅተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ተደራሽ ላይሆን ይችላል።

አቶ ኮኖር አክለው እንደገለጹት በተለይ ድንበር ተሻጋሪ ውሀዎች ባሉባቸው ቦታዎች ውሃ ራሱ የግጭት ምንጭ እንጂ የአመራር ዘዴ መሆኑ በጣም አልፎ አልፎ እንደሆነ ያስረዳሉ።

እንደ የውሃ ማጠራቀሚያ ኮሚሽኖች (ከ 5,000 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ) ወይም የውሃ ተፋሰስ ኮሚሽኖች ድንበር ተሻጋሪ ውሃ ባለባቸው ሀገራት መካከል የመንግስት ስርዓቶችን መፍጠር ፣ ስለ ሀብቱ መረጃ ለመለዋወጥ እና በዘላቂነት ለመምራት የሚያስችሉ መንገዶችን መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን ያብራራል ።

ከዚህም በላይ ውሃ በተከራካሪ ማህበረሰቦች መካከል "የሰላም ደላላ ሊሆን ይችላል" ሁሉም ሰው "ውሃ ህይወት ነው" እና ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አስፈላጊ መሆኑን ይገነዘባል። የግጭት ምክንያት ሲኖርም በውሃ ላይ ሲተባበሩ የቆዩ ማህበረሰቦች የግጭቱን መፍታት የሚያስችል የግንኙነት መስመር ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ይጠቅሳሉ።

የውሃ አያያዝ እና ጥበቃ

"የውሃ አያያዝ የሚጀምረው በቤት ውስጥ ነው" ሲሉ አቶ ኮነር አበክረው ተናግረዋል።

በቤት ውስጥ ውሃን መቆጠብ የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች በማሳየት በቤቶች ውስጥ ብዙ ውሃ "ይባክናል እንጂ" በተገቢው ሁኔታ ጥቅም ላይ እንደ ማይውል አክለው ገልጸዋል።

ከዚያም ያገለገለው ውሃ ተለቅቆ መታከም አለበት፣ ይህ ሂደት ውሃን ከአካባቢው ለማከም ከሚያስፈልገው አምስት እጥፍ የበለጠ ሃይል ይጠይቃል፣ ምክንያቱም ያገለገለው ውሃ የበለጠ ቆሻሻ እና እንደ ሳሙና ያሉ ብዙ በካይ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል።

"ውሃ በሚቆጥቡበት ጊዜ የኃይል መጠንን ለመቀነስ አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው፣ ይህም ብዙ ጉዳዮች በተለይም በቅሪተ አካል ነዳጅ አጠቃቀም ላይ የራሱ አዎንታዊ አስተዋጾ አለው" ብለዋል።

"ስለዚህ ውሃን መቆጠብ አካባቢን ይረዳል እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ይረዳል" በማለት አክለው ተናግረዋል።

21 March 2022, 11:47