ፈልግ

የሕሙማንን ነፍስ በሕክምና ዕርዳታ ማሰናበት የሕሙማንን ነፍስ በሕክምና ዕርዳታ ማሰናበት  

ካቶሊካዊ የሐኪሞች ማኅበር በሕክምና ዕርዳታ ነፍስን ማጥፋት በጽኑ ተቃወመ

በጣሊያን ውስጥ እ. አ. አ በ2010 የታተመው ሰነድ የሕሙማንን ነፍስ በሕክምና ዕርዳታ የማሰናበት ሂደት ተግባራዊ እንዲሆን የሚደነግግ መሆኑ ይታወሳል። ይህን ውሳኔ ማኅበራቸው በጽኑ የሚቃወም መሆኑን ካቶሊካዊ የሕክምና ዶችተሮች ማኅበር አስታውቋል። በሰነዱ ውስጥ የተደነገገው ሃሳብ በአገሪቱ ጤና ሥርዓት ላይ ችግሮችን መቀስቀሱን የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቦሻ አስታውቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የጣሊያን ካቶሊክ ዶክተሮች ማኅበር፣ የሕሙማንን ነፍስ በሕክምና ዕርዳታ ማሰናበትን የተቃወመው ምክንያታዊ መንገዶችን በመከተል መሆኑ ሲነገር፣ በማንኛውም መንገድ ነፍስ እንዲጠፋ የሚያስችል ሕግ በጤና ሥርዓት ላይ ችግር እንደሚፈጥር በድጋሚ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኢ-ሰብዓዊነትን በአዘኔታ መለወጥ አያስፈልግም

በጣሊያን ውስጥ የሚገኙ ካቶሊካዊ ዶክተሮች የያዙት አቋም በሕክምና እና ነፍስን በማሰናበት መካከል ያለውን ፍጹም አለመጣጣምን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በጣሊያን ውስጥ የሚሰጥ የሕመም ማስታገሻ እንክብካቤ፣ ሕክምና አገልግሎት የማግኘት አስፈላጊነትን የሚያረጋግጥ፣ “ነፍስን በሕክምና ድጋፍ የማሰናበት” ተግባር ደካማ እና አደጋን የሚያስከትል በመሆኑ በጽኑ አውግዘው፣ "በሕክምና እንክብካቤ ዘርፍ ኢ-ሰብዓዊነትን በአዘኔታ መለወጥ ስህተት መሆኑን ገልጸዋል። በዶክተሮቹ ማኅበር ፕሬዝዳንት በአቶ ፊሊፖ ማሪያ ቦሺያ የተፈረመው ጽሑፍ እንዳስረዳው፣ “አንዳንዶች በሕይወት እና በሞት መካከል እንዲሁም በክብር መሞት መካከል ያለውን ልዩነት መለየት መጀመሩን ያሳያል ብለዋል።

“በሕክምና ዕርዳታ ራስን የማጥፋት ጥያቄ ብዙውን ጊዜ የሚመጣው በአስጊ ሁኔታ ላይ እና በከባድ ስቃይ ውስጥ ሲገኙ እንደሆነ እንገነዘባለን” ያለው የሐኪሞቹ መግለጫ፣ “ቢሆንም ከአዘኔታ የተነሣ ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ በሕክምና ዕርዳታ ነፍስን የማሰናበት እርምጃ ትክክል ባለመሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል” ብሏል። ብቁ ሞት ለሁሉም ሰው እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ይቻላል ያለው የሐኪሞቹ መግለጫ፣ አስፈላጊ የፈውስ መርሆ እና እርምጃ በመከተል ሕሙማኑ ወደ መጨረሻ የሕይወት ደረጃዎች ሲደርሱ በሕክምና እገዛ አቋራጭ  መንገዶችን ተጠቅሞ ነፍስን ማሰናበት ትክክል አለመሆኑን ገልጿል።

የማስታገሻ እንክብካቤ ሕግን ቶሎ ተግባራዊ ማድረግ

እነዚህን ምክንያቶች ታሳቢ በማድረግ ለሕሙማን፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአእምሮ ሕሙማን የሚሰጡ የሕክምና ድጋፎች መከልከል እንደሌለባቸው ማኅበሩ ጠይቋል። ሕዝባዊ የአስተዳደር ተቋማት የሕመም ማስታገሻ አገልግሎት ተደራሽነት ዋስትናን ለማረጋገጥ በሕግ ቁጥር አንቀጽ 38/2010 የተቀመጠውን ሕግ ተግባራዊ ለማድረግ እና ለሕይወት ፍጻሜ ለተቃረቡ ሰዎች ተገቢውን እንክብካቤን በመስጠት በሕይወት እንዲቆዩ ማድረግ ያስፈልጋል" ብሏል። ይህም በሕክምና ዕርዳታ የሚፈጸመውን ነፍስ የማጥፋት ተግባርን በማስቀረት፣ ሕሙማን የተሻለ ዕርዳታ እና እንክብካቤን አግኝተው በሕይወት እንዲቆዩ ማድረግ ከፍተኛ ጥረትን የሚጠይቅ መሆኑን በጣሊያን ውስጥ የሚገኝ ካቶሊካዊ የሕክምና ዶክተሮች ማኅበር በመግለጫው አመልክቷል።

24 January 2022, 14:58