የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በመላው አለም ፍትሃዊ ያልሆነ የክትባት ስርጭት አወገዘ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የኮቪድ 19 ክትባቶች ፍትሃዊ ስርጭትን ለማሳካት የሚሰሩ አጋሮቻቸው ረቡዕ ዕለት በየካቲት 10/2013 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም / ቤት ባካሄዱት ስብሰባ ግጭቶች በሚካሄዱባቸው ቀጠናዎች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እንኳን ሳይቀር የኮቪድ 19 ክትባት የማግኘት መብታቸው እንዲረጋገጥ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንዳሉት ክትባቶችን ለሁሉም የማቅረብ ግብ “የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትልቁ የሞራል ፈተና” ነው በማለት መናጋራቸው የሚታወስ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረቡዕ የካቲት 10/2013 ዓ.ም በበይነ መረብ በተካሄደው ከፍተኛ የፀጥታው ም / ቤት ስብሰባ ላይ ባዳረጉት ንግግር ነበር ይህንን አሳባቸውን እና ተግድሮቶቹን የገለጹት።
“በጭካኔ ያልተስተካከለ እና ኢ-ፍትሃዊ” የሆነ ተግባር
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀላፊ በየካቲት 10/2013 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የደኅንነት ም / ቤት ስብሰባ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የትም ቦታ የፀረ-ኮቪድ 19 ክትባት መርሃ ግብር ተደራሽ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። ሐብታም በሚባለው የምዕራባዊያኑ እና ድሃ በሚባሉ የምስራቃዊያኑ አከባቢዎች መካከል “በጭካኔ መንፈስ ባልተስተካከለ እና ኢ-ፍትሃዊ” ክትባቶች ስርጭትን ክፉኛ ተችተዋል። ከ 130 በላይ አገራት ምንም ዓይነት ክትባት ያላገኙ መሆኑን የገለጹ ሲሆን 10 የሚሆኑ የአለማችን አብታም የሚባሉ አገራት ደግሞ ከሁሉም ክትባቶች 75 ከመቶውን ድርሻ እንደ ወሰዱ እና የሁኔታው አሳሳቢነትን የሚያሳይ ከፍተኛ ልዩነት በመካከላቸው እንዳለ እንደ ሚያሳይ እንደ ሆእን አክለው ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ የሆኑት አንቶኒዮ ጉተሬዝ በየአገሩ ያሉ ሰዎች ሁሉ በተቻለ ፍጥነት ክትባት እንዲያገኙ ዓለም አቀፍ ጥረት እንዲደረግ የጠየቁ ሲሆን በግጭቶች እና በጸጥታ ችግር የተጎዱ ወገኖች ወደ ኋላ የመተው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ “የእኛ ደህንነት የሚጠበቀው የሁሉም ሰው ደህንነት የተጠበቀ ከሆነ ብቻ ነው” ብለዋል።
የኮሮና ቫይረስ እስካሁን ድረስ ከ110 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በበሽታው የተጠቁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 2.4 ሚሊዮን ሰዎችን ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። አምራቾች የክትባት ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ በሚታገሉበት በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሀገራት ባለመካተታቸው የተነሳ ቅሬታ ያሰማሉ፣ የበለፀጉ ሀገሮችም እንኳን የክትባቱ እጥረት እያጋጠማቸው መሆኑን በቅረታ በመግለጽ ላይ እንደ ሚገኙ ተገልጿል።
ለክሮና ቫይረስ ክትባ የሚደርገው ድጋፍ
የዓለም ጤና ድርጅት እና ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸው ለዓለም ድሃ ለሆኑ አገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ለመግዛት እና ለማድረስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለመግዛት ፕሮግራሞችን ቀርጸው እየተንቀሳቀሱ እንደ ሆነም ተዘግቧል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የበለጠ ጥርት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ፣ ፍትሃዊ የክትባት ስርጭትን ማረጋገጥ የሚችሉትን ማለትም ሳይንቲስቶችን ፣ የክትባት አምራቾችንና ጥረቱን በገንዘብ ሊደግፉ የሚችሉትን በአንድ ላይ ለማሰባሰብ አስቸኳይ የአለም አቀፍ ክትባት እቅድ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም የቡድን 20 አገራት በመባል የሚታወቁት የዓለም ዋና ዋና የኢኮኖሚ ኃይሎች ዕቅዱን ለመተግበር፣ ለማቋቋም እና አተገባበሩን እና ፋይናንስን ለማቀናጀት አስቸኳይ ግብረ ኃይል ማቋቋም እንደ ሚገባቸው አክለው አሳስበዋል።
ሀብታም በሆኑት ሀገሮች ውስጥ ክትባት በተጀመረበት ወቅት የኮሮና ቫይረስ ክትባት በድሃ ሀገሮች ውስጥ ክትባቶችን ለመጀመር የራሱን ግብ እንዲቀመጥ ማድረጉን የተገለጸ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ለመሸመት ይቻለው ዘንድ ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እንደ ሚያስፈልገው መግለጹ ይታወሳል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ፈንድ
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) እንዲሁ የኮቪድ 19 ክትባት ለሁሉም ሰዎች ተደራሽ ይሆን ዘንድ ጥሪ ማቀረቡም ተገልጿል። የዩኒሴፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሄንሪታ ፎር በየካቲት 10/2013 ዓ.ም በተካሄደው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት "ከዚህ ወረርሽኝ ለመገላገል የሚያስችለው ብቸኛው መንገድ ክትባቶች ለሁሉም ሰው ተደራሽ መሆኑን ማረጋገጥ ነው" ብለዋል ፡፡
የፍትህ ጉዳይ
በዚህ ታሪካዊ ጥረት በግጭትና አለመረጋጋት ውስጥ የሚገኙ አገራት ሕዝቦች ወይም ግጭቶችን በመሸሽ ላይ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መካተት እንደ ሚኖርባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ፈንድ ዋና ኃላፊ ይገለጹ ሲሆን ዩኒሴፍ በአመቱ መጨረሻ ላይ ሁለት ቢሊዮን የመድኃኒት ግዥዎችን በማፈላለግ ለኮቭድ -19 ክትባት ስርጭት ዝግጅት አገሮችን ለመርዳት ጥረት እያደረገ እንደ ሆነ ተገልጿል።
“ይህ ታሪካዊ ጥረት ታሪካዊ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ፈንድ ዋና ኃላፊ የግጭቱን አስከፊ ሁኔታ ተቋቁመው ቤተሰቦቻቸውን እና ማህበረሰቦችን ጨምሮ - በዋሻው መጨረሻ ላይ ያለው ብርሃን በሁላችን ላይ እንዲበራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።
በግጭት ውስጥ የሚኖሩትን ጨምሮ ለሁሉም ሰዎች ፍትሃዊ የክትባት ተደራሽነት አስፈላጊ ነው ፣ እንደ ፍትህ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ይህን ወረርሽኝ ከአለም ላይ ለማጥፋት እና የእንክብካቤ ዘር ለመዝራት ብቸኛው መንገድ በመሆኑ የተነሳ በተለይ ድሃ ለሆኑ አገራት ተደራሽ ማደረግ ተገቢ መሆኑ በስብሰባው ወቅት ተገልጿል።
ሀገሮች ምንም ይሁን ምን ወይም በመንግስት ቁጥጥር ስር ባልሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ቢሆኑም ሁሉም ሰዎች በብሔራዊ የክትባት ዕቅዶች ውስጥ መካተታቸውን እንዲያረጋግጡ አገሮች የፀጥታው ም / ቤት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ዓለም አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በመጋቢት እ.አ.አ በ2020 ዓ.ም ባወጣው አቤቱታ ዓለም አቀፍ የተኩስ አቁም አስፈላጊ መሆኑን ሲያጎላ የዩኒሴፍ ሃላፊም በወረርሽኙ ጊዜ ቆመው የነበሩትን የኩፍኝ ፣ የፖሊዮ እና ሌሎች በሽታዎችን የመከላከል ዘመቻ እንደገና እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል። “በአንዱ ገዳይ በሽታ ላይ የምናደርገው ውጊያ ከሌሎች ጋር በሚደረግ ውጊያ መሬት እንድናጣ ሊያደርገን አይገባም” ማለታቸው ይታወሳል።