ጸረ ዘረኝነት ሰልፍ በሰሜን አሜሪካ፣ ሚኒያፖሊስ፤ ጸረ ዘረኝነት ሰልፍ በሰሜን አሜሪካ፣ ሚኒያፖሊስ፤  

ዘረኝነትን የማናሸንፈው ለምን ይሆን!

ከሦስት ሳምንታት በፊት በሰሜን አሜሪካ፣ ሚኒያፖሊስ ግዛት ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ አፍሮ-አሜሪካዊ በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ መገደሉ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ሰሜን አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች፣ በአውሮፓ እና በአፍሪካ የጸረ ዘረኝነት ሰልፎች ሲካሄዱ መሰንበታቸው ይታወቃል። በጣሊያን ፓዶቫ ከተማ “አንቶኒዮ ፓፒስካ” ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ምሁር ከሆኑት መምህር ፓውሎ ዴ ስተፋኖ ጋር ቫቲካን ኒውስ ቃለ ምልልስ አድርጓል።  

የቫቲካን ዜና፤

ዓለማችን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጠቅቶ በሚገኝበት ጊዜ በተለያዩ የዓለማች ክፍሎች የጸረ ዘረኝነት ሰልፎች ሲደረጉ መሰንበታቸው ይታወቃል። በአፍሮ-አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ምክንያት በሚኒያሶታ የተቀሰቀሰው የተቃውሞ ሰልፍ ወደ ሌሎችም የአሜሪካ ግዛቶች እና አህጉራት መዛመቱ ይታወሳል። ስለ ዘረኝነት ሲነሳ ምናልባትም በቅድሚያ ከቃሉ ትርጉም መነሳቱ መልካም ነው ያሉት መምህር ፓውሎ ዴ ስተፋኖ፣ በማንኛውም ስነ ልቦናዊ እና ፖለቲካዊ መስክ አንድ የማኅበረሰብ ክፍል በሌላው ማኅበረሰብ ላይ ሕጋዊ የበላይነት ኖሮት እስከ ግድያ ተግባር በሚደረስበት ጊዜ ወደ ዘረኝነት ጥላቻ የሚቀየር መሆኑን አቶ ፓውሎ አስረድተዋል።

ሁሉ የተጀመረው ከ20 ቀናት በፊት ነበር፣

ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ አፍሮ-አሜሪካዊ ግድያን ተከትሎ ከሚኒያፖሊስ እስከ ኒው ዮርክ፣ ከለንደን እስከ ፓሪስ፣ እንዲሁም በሮም ከተማም ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ታውቋል። ከእነዚህ ሥፍራዎች በተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፎቹ የፓሲፊክ አገሮችን ጨምሮ በህንድ እና በአፍሪካ ውስጥም በኬንያ መቀስቀሳቸው ይታወሳል። የጆርጅ ፍሎይድ ሞት በመላው ዓለማችን ከፍተኛ ተቃውሞን ማስከተሉ ይታወቃል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለማችን በመስፋፋት ብዙ ሰዎችን ለሞት በመዳረግ ላይ በሚገኝበት ባሁኑ ጊዜ የጆርግ ፍሎይድ ግድያ ተጨማሪ አሳዛኝ ዜና ሆኖ መቅረቡ ዘረኝነትን በማስመልከት የሚነሱ ጥያቄዎችን ጎላ ማድረጉ ታውቋል። ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በኋላ በተከሰተው ሌላ ግድያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉ የተለያዩ ከተሞቹ አደባባዮችን በሰልፈኞች ማጥለቅለቁ ታይቷል። የሰልፎቹን ውጤት መመልከት ጠቃሚ እንደሚሆን የገለጹት መምህር ፓውሎ፣ ዘረኝነት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ በሰሜን አሜሪካ በሚደረጉ ምርጫዎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ርዕሠ ጉዳይ እንደሚሆን አስረድተዋል።

አፍሪካም የፍትህ ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል፣

ከሦስት ቀናት በፊት የአፍሪካ አገሮች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ምክር ቤት ጋር በአፍሮ-አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ላይ በተፈጸመው ግድያ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ይታወሳል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የቡርኪና ፋሶ አምባሳደረ፣ 54ቱን የአፍሪካ አገሮች በመወከል ጠንከር ያለ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። አምባሳደሩ ያቀረቡት ጥያቄ ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን ስነ ልቦናዊ ይዘት ያለው መሆኑ ታውቋል። “የሰው ልጅ አንዱ ከሌላው የተለየ ነው” የሚያስብል ምክንያት ምንድር ነው የሚለው የአምባሳደሩ ጥያቄ ፖለቲካዊ ሳይሆን ስነ ልቦናዊ ጥያቄ እንደሆነ፣ በሰዎች መካከል የሚነሱ የልዩነት ጥያቄዎች ታሪክን ተከትለው የመጡ ኤኮኖሚያዊ ይዘት ሊኖራቸው እንደሚችል የተናገሩት አቶ ፓውሎ፣ ይህ ጥያቄ ለምን በ21ኛ ክፍለ ዘመን ሊነሳ ቻለ በማለት ጥያቄአቸውን አቅርበዋል።

የቅኝ ግዛት ውርስ ነው፣

በጣሊያን፣ ፓዶቫ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጠብቃ ጥናት መምህር የሆኑት አቶ ፓውሎ ዴ ስተፋኖ፣ የዘረኝነት ጥያቄ የቅኝ ግዛት ሥርዓት ውርስ መሆኑን ለቫቲካን ኒውስ ገልጸዋል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና የጸረ ዘረኝነት ሰላማዊ ሰልፎች ግንኙነት አላቸው ያሉት መምህር ፓውሎ፣ ሥርዓቱ በኤኮኖሚ ወደ በለጸጉ አገሮች ያደላል ብለው፣ ወረርሽኙን በመድሃኒት ለመቆጣጠር እና ለመከላከል በሚሊያርድ የሚቆጠር ዶላር ማውጣትን ይጠይቃል ብለው አሁን የተከሰተውን የጤና ቀውስ ከሁሉም የዓለማችን ክፍሎች እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ጥያቄ አቅርበዋል። የዘረኝነት ችግር ከዚህ በፊት ከነበረው በእጅጉ መቀነሱን ያስታወሱት መምህር ፓውሎ፣ አሁንም ቢሆን ለማንነት ጥያቄዎች ከፍተኛ ትኩረትን በመስጠት ዘረኝነትን አጥብቆ መዋጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለዘረኝነት ዕድል መስጠት አያስፈልግም፣

ስለ ሰው ልጅ ቅድስና እየሰበክን ዘረኝነትን እና መገልልን በዝምታ መመልከት የለብንም በማለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ግንቦት 26/2012 ዓ. ም. ባቀረቡት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸው መናገራቸው ይታወሳል። ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጥልው የሰሜን አሜሪካ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳትም በሰሜን አሜሪካ ወስጥ በአፍሮ-አሜርካዊያን ላይ የሚደረግ የዘረኝነት ተጽዕኖ ለረጅም ዓመታት በዝምታ የቆየ መሆኑን ገልጸው ለእኩልነት በሚታገሉበት ጊዜ አመጽን ማካሄድ በሰው ሕይውት እና በንብረት ላይ ጉዳትን ማድረስ ይሆናል ብለዋል።  

16 June 2020, 18:33