የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ አቶ ደመቀ መኮንን ቫቲካን ከካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን ጋር በተጋናኙበት ወቅት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ አቶ ደመቀ መኮንን ቫቲካን ከካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን ጋር በተጋናኙበት ወቅት 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ቫቲካንን መጎብኘታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ደመቀ መኮንን በጥቅምት 06/2012 ዓ.ም ቅድስት መንበር (ቫቲካን) ጎበኙ። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋር በተገናኙበት ወቅት በሁለቱ አገራት ማለትም በኢትዮጲያ እና በቫቲካን መካከል ያለውን በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ መልካም ግንኙነት  አስመልክቶ የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡ በተመሳሳይ ክቡርነታቸው ከኢትዮጵያ ልዑካን ጋር በመሆን በቫቲካን የሚገኘውን የአቢስንያ የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያንን እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮሌጅን ጎብኝተዋል፡፡ ክቡርነታቸው በቦታው ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ ፀጋዪ ቀነኒ የሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ ከኮሌጁ ማህበረስብ ጋር በመሆን የክብር አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ብፁዕነታቸውም ስለ ኮሌጁ አጠቃላይ ገጽታ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

የቫቲካን ዜና

የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ም/ጠቅላይ  ሚኒስቴር አቶ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በጉብኝቱ ወቅት  ባዮት እና በሰሙት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው በዚህ በተቀደሰ ቦታ ኢትዮጵያውያን ለእምነታቸው ብለው የከፈሉት መስዋዕትነት በዓለም ላይ እንኳን ታላቅ ቦታ እንዳሰጠም ምስክር መሆኑን ገልፀው፡፡ ኮሌጁ ካለበት መንፈሳዊ አስተምሮ በተጨማሪ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ግጭት በነበረበት ወቅት እንኳን የኢትዮጵያና የኤርትራ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ካህናት ልዩነት ሳይፈጥሩ የተማሩበት ቦታ መሆኑ የመቻቻል እና አብሮ የመኖር ተምሳሌት ሆኖ ይገለፃል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም ቅዱስ ተብለው በሚጠሩባቸው ሥፍራዎች እነዚህን የመሰሉ ርስቶች ስላሏትም ወጣቶች በአገራቸው ታላቅ ታሪክ ኮርተው ለእድገት እንዲነሳሱ የሚያደርግ ስለሆነ እንዲያውቋቸው መጣር አለብን ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በቫቲካን ውስጥ የራስዋ ኮሌጅ ያላት ብቸኛ ሃገር ናት፡

Photogallery

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ቫቲካንን መጎብኘታቸው ተገለጸ።
17 October 2019, 15:40