ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ከሸክ አህመድ አል ጣይብ ጋር በአቡዳቢ በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ከሸክ አህመድ አል ጣይብ ጋር በአቡዳቢ በተገናኙበት ወቅት 

የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ተባብረው ለሰላም መሥራት ይኖርባቸዋል።

“ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሐይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 26/2011 ዓ.ም የዛሬ ስድስት ወር ገደማ ማለት ነው ወደ እዚያው በማቅናት 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ማደረጋቸው ይታወሳል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ በተባበሩ የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ የዛሬ ስድስት ወር ገደማ እያደረጉት 27ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት “የሰላም መሳርያ አድርገኝ” የሚል መሪ ቃል ያነገበ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን እ.አ.አ በ13ኛው ክፍለ ዘመን የዛሬ 800 አመት ገደማ ማለት ነው ቅዱስ ፍራንቸስኮስ እና በወቅቱ የገብፅ ሱልጣን የነበሩት ማሊክ አል ካሚል ጋር በጣሊያን በተገናኙበት ወቅት የተጠቀሙበት መሪ ቃል በድጋሚ ለማስታወስ እና አሁንም ቢሆን ከ800 አመታት በኋላም ቢሆን እንኳን ዓለማችን በከፍተኛ ግጭቶች ውስጥ ስለምትገኝ በዚህ በግጭቶች እና በጦርነቶች እየተናጠች በምትገኘው ዓለማችን ሰላም ይሰፍን ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና መንግሥታት የራሳቸውን አዎንታዊ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ለማሳሰብ የተመረጠ መሪ ቃል እንደ ሆነ ቀድም ባሉ ዝግጅቶቻችን መዘገባችን ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአቡ ዳቢ በነበራቸው ቆይታ ከተለያዩ የእምነት ተቋማት መሪዎች እና ተወካዮቻቸው ጋር ቆይታ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በተለይም ደግሞ እርሳቸው “ወንድሜ እና ጓደኛዬ” በማለት ከሚጠሩዋቸው የግብፅ ታላቁ የአልዓዛር መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ ኢማም ከሆኑት አህመድ አል ጣይብ ጋር መገናኘታቸው እና በዓለም ዙሪያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የሁለቱ ሐይማኖት ተቋማት ተወካዮች ማለትም የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ምዕመናን በወንድማማችነት መንፈስ በመተጋገዝ እና በመደጋገፍ ይኖሩ ዘንድ የሚያስችላቸው የመግባቢያ የሰላም ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።

የክርስቲያን መሳሪያ እመንት እና ፍቅር ነው!

ቅዱስነታቸው በዚያው በአቡዳቢ የዛሬ ስድስት ወር ባደርጉት ታሪካዊው 27ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት በአቡዳቢ ከሚገኙ አጠቃላይ 10 ሚልዮን ከሚሆኑ ሕዝቦች ውስጥ 1 ሚልዮን የሚሆኑ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መካከል 180,000 ሺህ የሚሆኑ ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ ማስረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “የአንድ ክርስቲያን መሳሪያ እመንት እና ፍቅር ነው” ማለታቸውም ይታወሳል።

የሰላም ስምምነቱ ታሪካዊ ነው

በወቅቱ “ሰብዓዊ ወንድማማችነት” የሚል አርስት የተሰጠው የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት “የግብፅ ታላቁ የአልዓዛር መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ ኢማም ከሆኑት ሼክ አህመድ አል ጣይብ ጋር የተፈራረሙት የሰላም የመግባቢያ ሰንድ ታሪካዊ” መሆኑን ገልጸው “ይህም ሰብዐዊ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያስችል እና ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ሰነድ የተወለደ አዲስ ስምምነት ማድረጋቸው በጣም እንዳስደሰታቸው” ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን “ይህ የተፈረመው የሰላም የመግባቢያ ሰነድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስር መስረታቸውን በሁለተኛው ቫቲካን ጉባሄ ላይ ማድረጋቸውን የሚያሳይ አንድ እርምጃ” እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

ይህ የመግባቢያ ሰነድ የተወለደው ከእምነት ነው

ይህ ቅዱስነታቸው እና የግብፅ ታላቁ የአልዓዛር መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ ኢማም የሆኑት ሼክ አህመድ አል ጣይብ የተፈራረሙት የሰላም መግባቢያ ሰነድ የተዘጋጀው “ከፍተኛ የሆነ አስተንትኖ እና ጸሎት ከተደረገ” በኋላ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው “ይህ የሰላም መግባቢያ ሰነድ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በከፍተኛ ሁኔታ በመንጸባረቅ ላይ ያሉ አስከፊ የሆኑትን “ጦርነቶች፣ ውድመቶችን እና የእርስ በእርስ ጥላቻን” ለማስወገድ በማሰብ በጥንቃቄ የተዘጋጀ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። “እኛ አማኝ የሆንን ሰዎች እጅ ለእጅ መጨባበጥ፣ መተቃቀፍ፣ መሳሳም እና አብረን መጸለይ ካልቻልን፣ እምነታችን ተሸናፊ ይሆናል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም መሰረት ይህ እርሳቸው እና የግብፁ ታላቁ የአልዓዛር መስጊድ እና ዩኒቬርሲቲ ኢማም የሆኑት ሼክ አህመድ አል ጣይብ የተፈራረሙት የሰላም የመግባቢያ ሰነድ “የተወለደው የሁሉም አባት ከሆነውና የሰላም አባት ከሆነው በእግዚአብሔር ላይ ካለን እምነት ነው፣ እርሱም በታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የአሸባሪዎች ጥቃት ከሆነው ከቃየን የሽብር ዘመቻ ጀምሮ ያሉትን ውድመቶች እና የአሸባሪዎች ጥቃት ያወግዛል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

እ.አ.አ በሚያዚያ ወር 2017 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግብፅ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማደርጋቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ የአልዓዛር ታላቁ መስጊድ እና ዮኒቬርሲቲ ታላቁ ኢማም ከሆኑት አህመድ ሙሀመድ ኣል ታይብ ጋር በተገናኙበት ወቅት የሚከተለውን ንግግር አድረገው ነበር ...

የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንደመሆናችን መጠን ማነኛውንም ዓይነት ቅድስናን የሚያጎድፉ ብጥብጦችን እና ግጭቶችን፣ የኋጢኣት ሁሉ መንስሄ የሆነውን የራስ ወዳድነት መንፈስን በማውገዝ እውነተኛ የሆኑ የውይይት መድረኮችን መክፈት ይኖርብናል። በሰው ልጆች ክብር እና ሰብአዊ መብት ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን ለማውገዝ፣ በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ ጥላቻዎችን በመፍጠር፣ እነዚህን ጥላቻዎች በሐይማኖትና በእግዚኣብሔር  ስም እውነተኛ እንደሆኑ አስመስሎ ለማቅረብ የሚደርጉትን ጥረቶች በሙሉ ለማጋለጥ እና እነዚህን ጉዳዮች የእውነተኛው አምላክ ፍላጎቶች ሳይሆኑ ነገር ግን የጣዖት አምላክ ፍላጎቶች መሆናቸውን በማሳወቅ፣ የእውነተኛው እግዚኣብሔር ስም ቅዱስ፣ እርሱ የሰላም አምላክ፣ እግዚኣብሔር ሰላም መሆኑን በድፍረት መመስከር ይኖርብናል። ስለዚህ የተቀደሰ ነገር የሚባለው ሰላም ብቻ ነው፣ ስለሆነም በእግዚአብሔር ስም ምንም ዓይነት ግፍ፣ ብጥብጥ፣ ግጭት ሊፈጸም አይችልም፣ ምክንያቱም በእግዚኣብሔር ስም የሚፈጸሙ ግፎች ቅዱሱን የእግዚኣብሔር ስም ያረክሱታልና” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

20 July 2019, 12:18