ፈልግ

በፈረንሳይ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት በሀግሪቷ ውይይት ይደርግ ዘንድ ጥሪ አቀረቡ በፈረንሳይ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት በሀግሪቷ ውይይት ይደርግ ዘንድ ጥሪ አቀረቡ 

በፈረንሳይ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት በሀግሪቷ ውይይት ይደርግ ዘንድ ጥሪ አቀረቡ

በፈረንሳይ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ተቃዋሚዎች እና መንግሥት ውይይት እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ተገለጸ። ከሳምንታ በፊት የፈረንሳይ መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ አድርጎት የነበረውን የዋጋ ጭማሪ በመቃወም በርካታ የሆኑ “ብጫ ለባሽ” የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ሰዎች የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎችን በማድረግ ላይ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ተቃውሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ ነውጥ እየፈጠረ፣ ውድመት እያስከተለ ብዙ ሰዎችን ለጉዳት የዳረገ የሚገኝ ክስተት እየሆነ እና እየተስፋፋ በመምጣት ላይ እንደ ሚገኝ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ከሰፈሩ መረጃዎች እና ዜናዎች ለመረዳት የሚችላ ሲሆን ይህ በነዳጅ ላይ በተደረገ የዋጋ ጭማሪ የተነሳ በመንግሥት እና በተቃዋሚዎች መካከል እየተከሰተ የሚገኘው ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተወግዶ ችግሩ በውውይት ይፈታ ዘንድ በፈረንሳይ የሚኖሩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጥሪ መቀረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በፈረንሳይ በኖርማንዲ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት በነዳጅ ዋጋ ላይ መንግሥት ባደርገው ጭማሪ የተነሳ በመንግሥት እና በተቃዋሚዎች መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ እንዳሳሰባቸው በምልእክታቸው አክለው የገለጹት ጳጳሳቱ በዚህም ምክንያት ይህ ግጭት በሰላማዊ መንገድ ይፈታ ዘንድ መንግሥት እና ተቃዋሚዎች ተቀራርበው በመወያየት ለችግሩ እልባት እንዲፈልጉ ጨምረው ገለጸዋል። “ለቄሳር ግብር መክፈል ይኖርብናል ውይ?” የሚለውን በማቴዎስ፣ በማርቆስ እና በሉቃስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን ቃላት አርስት አድርገው በመጠቀም ብጹዕን ጳጳሳቱ ባስተላላፉት መልእክት በፈረንሳይ ሀገር የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአከባቢያቸው ለሚገኙ ሌሎች ሰዎች መልካም አብነት እንዲሆኑ በመልእክታቸው  አሳስበዋል።

ወይይት እና ሰላም

“የቄሳርን ለቄሳር የእግዚኣብሔርን ለእግዚኣብሔር” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ መርዕ በእግዚኣብሔር ላይ ያለንን እምነት ጠብቀን እንድንሄድ የሚመክረን እና እንደ ማነኛውም ዜጋ የሀገር ግዴታችንን መወጣት ይኖርብናል የሚል ትርጉም የሚሰጠው መርዕ ሲሆን ብጹዕን ጳጳሳቱ የዜጎችን መብት እና ድርጊት ለመገደብ አስበው ሳይሆን ቅዱስ ወንጌልን በዋቢነት በመጥቀስ የግብር ጥያቄዎች ብዙን ጊዜ የተሸሸጉ ብዙ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ተሸሽገው የሚገኙበት ጥያቄ በመሆኑ የተነሳ ይህን በነዳጅ ላይ የተደርገውን የዋጋ ጭማር እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ከዋናው ዓላማ ውጪ የሆኑ ስውር አጀንዳዎች ማስፈጸምያ እንዳይሆን ካላቸው ስጋት በመነጨ መልኩ ያስተላለፉት መልእክት እንደ ሆነም ተያይዞ ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።

በመግለጫው ከተካተቱ አራት ነጥቦች ውስጥ በቀዳሚነት የተገለጸው በብጥበት እና በሁከት ሊገኝ የሚችል ተጨባጭ የሆነ ምፍትሄ ሊኖር እንደ ማይችል በስፋት የሚገልጽ ሲሆን ነገር ግን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ውይይት በማድረግ ለችግሮች ሁሉ ተጨባጭ መፍትሄ ማስገኘት እንደ ሚገባ መግለጫው ያትታል። ለማነኛው ዓይነት ችግሮ መፍትሄ ሊገኝ የሚችለው የሚመለከታቸው ሰዎች ፊት ለፊት ቀርበው ሲነጋገሩ ብቻ እንደ ሆነ የገለጸው በፈረንሳይ በኖርማንዲ የሚኖሩ የካቶሊክ ቤት ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት መግለጫ በዚህ መሰረት መላው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ይህን ሐሳብ በጥልቀት በመረዳት የመፍትሄ ሐሳብ መጠቆ በሚችሉ በማነኛውም ዓይነት ውይይቶች ላይ ይሳተፉ ዘንድ ጳጳሳቱ በመግለጫቸው ጥሪ አቅርበዋል።

12 December 2018, 15:21