2018.10.04 CARD. DIEUDONNE NZAPALAINGA, ARCIVESCOVO DI BANGUI/CENTRAFRICA 2018.10.04 CARD. DIEUDONNE NZAPALAINGA, ARCIVESCOVO DI BANGUI/CENTRAFRICA 

ካርዲናል ደዎዶኔ፣ ንጹሃን ዜጎችን ከሞት አደጋ ለማትረፍ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ።

ሊቀ ጳጳስ ደዎዶኔ በብዙ የአገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ገልጸው በዚህ የተነሳ በተለይም በርካታ ሕጻናት ለረሃብና ለበሽታ መዳረጋቸውን ገልጸዋል። ካርዲናል ደዎዶነ፣ በሕዝባቸው ላይ በአገር ውስጥም ሆነ በአገር ውስጥ የሚፈጸም ግድያና ስቃይ አቅመ ደካማና ራሳቸውን ለመከላከል በማይችሉ የሕብረተሰብ ክፍል ላይ እንደሚፈጸም ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የመካከለኛው አፍሪቃ ርፓብሊክ ዋና ከተማ የሆነችው የባንጊ ሊቀ ጳጳስ የብጹዕ ካርዲናል ደዎዶኔ ዛፓላይንጋ፣ በሃገሪቱ ውስጥ የንጹሐን ዜጎች ሕይወት በከንቱ ሲጠፋ በዝምታ መመልከት ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል። ካርዲናል ደዎዶነ የአሊንዳዎ ክፍለ ሃገርን ጎብኝተው ሲመለሱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግላጫቸው እንዳስገነዘቡት በስፍራ እ. አ. አ. ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ. ም. በንጹሃን ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ወደ 60 የሚጠጉ ዜጎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጸዋል።

በአንድ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተጠለሉት ሰዎች ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት መሣሪያ ታጣቂዎች በመካከለኛው አፍሪቃ ርፓብሊክ ሰላምን ለማምጣት የሚታገል ሃይል አባላት መሆናቸው ታውቋል። በአሊንዳኦ የስደተኞች መጠለያ የነበሩት በሙሉ ክርስቲያኖች መሆናቸው ሲገለጥ ከእነርሱም መካከል የከተማው ጳጳስና ሁለት ካህናት እንደነበሩ ያውቋል።

ሊቀ ጳጳስ ደዎዶኔ በመግለጫቸው እንደገለጹት መሣሪያ ታጣቂዎቹ በተፈናቃዩ ሕዝብ ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ማስፈራራትም የታከለበት እንድሆነ ገልጸው የአገሪቱ መንግሥትም ይሁን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግድያና ስቃይ የሚደርስበትን ሕዝብ ከአደጋ የመጠበቅና የመከላከል ብቃት እንደሚያንሰው አስረድተዋል። ሊቀ ጳጳስ ደዎዶኔ በብዙ የአገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ገልጸው በዚህ የተነሳ በተለይም በርካታ ሕጻናት ለረሃብና ለበሽታ መዳረጋቸውን ገልጸዋል። ካርዲናል ደዎዶነ፣ በሕዝባቸው ላይ በአገር ውስጥም ሆነ በአገር ውስጥ የሚፈጸም ግድያና ስቃይ አቅመ ደካማና ራስሳቸውን ለመከላከል በማይችሉ የሕብረተሰብ ክፍል ላይ እንደሚፈጸም ገልጸዋል።

ብጹዕ ካርዲናል ደዎዶኔ ከባንጊ ከተማ ኢማም ከሆኑት ከኦማር ኮቢን ላያማ ጋር ሆነው በሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫ በመካከለኛው አፍሪቃ ርፓብሊክ የሚካሄደው ጦርነትና አመጽ በሐይማኖቶች መካከል በሚፈጠር ግጭት እንዳልሆነ ገልጸዋል።             

ከመካከለኛው አፍሪቃ ሪፓብሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ የወጣው ዜና እንዳመለከተው፣ የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት በመጀመሪያ አንቀጹ እንደሚገልጸው ሰብዓዊ ፍጡር ቅዱስና ክብርም የማይጣስ መሆኑን አስታውሰው፣ ነገር ግን በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች ሕገ መንግሥቱን እንደሚቃረን ገልጸዋል። በመሆኑ የመካከለኛው አፍሪቃ ርፓብሊክ ብጹዓን ጳጳሳት በጎ ፈቃድ ላላቸው በሙሉ ባስተላለፉት መልዕክታቸው፣ በመሣሪያ ታጣቂዎች ጥቃት ሕይወታቸውን ያጡትን በሙሉ በጸሎታቸው እንዲያስታውሱ አደራ ብለው፣ ሕዳር 23 ቀን 2011 ዓ. ም. በአገሪቱ በሙሉ በአመጽ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡት የመታስቢያ ቀን ሆኖ እንዲታወጅ አሳስበዋል።

በቫቲካን የዜና አገልግሎት፣ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ክፍል ጋዜጠኛ ኦሊቬር ቦኔል ከብጹዕ ካርዲናል ደዎዳኔ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፣ ካርዲናል ደዎዳኔ እንደገለጹት ባሁኑ ወቅት በአገሪቱ የንጹሕን ዜጎች ሕይወት በከንቱ እየጠፋ መሆኑን የአገሩ መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እንዲያውቀው ማድረግ እፈልጋለሁ ብለው፣ እነዚህ ንጹሐን ዜጎች በከንቱ ሲገደሉ በዓይናቸው እያዩ መሆኑን ገልጸዋል። ካርዲናሉ በማከልም በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈለግለት፣ ግድያው ለሚፈጸምባቸው አቅመ ደካሞችና ሕጻናት ጥበቃ እንዲደረግላቸው ተማጽነዋል። ካርዲናሉ በተጨማሪም የአገሪቱ መንግሥትም ይሁን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አመጹንና ግድያን ለማስቆም የወሰዱት እርምጃ አለመኖሩን ገልጸው ይህን እንዳያደርጉ አቅም ያንሳቸዋል ብለዋል። ብጹዕ ካርዲናል ደዎዶኔ በመጨረሻም ከሰዎች በኩል የሚመጡ ስሞታዎች መልስ እያገኙ ሲሆን እኛ የክርስቲያን ወገኖችም ከተለያዩ ወገኖች በኩል በአገሪቱ የተነሳው ጦርነትና አመጽ እንዲቆም የሚያደርግ ክፍል ከተገኘ በማለት ጥሪያችንን ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን፣ ለዓለሙ ማሕበረሰብም ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል።             

28 November 2018, 11:07