2018-02-02 studenti all interno di Angola 2018-02-02 studenti all interno di Angola 

በካሜሩን በአንድ ትምህርት ቤት 79 ተማሪዎች መታገታቸው ተነገረ።

በምዕራብ ካሜሩን፣ በባሜንዳ ክፍለሃገር፣ በንኩዌን መንደር በሚገኝ የፕሮቴስታን ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ውስጥ በተማሪዎች ላይ በደረሰው ጥቃት የትምህርት ቤቱ ሾፌርና ሌላ የትምህርትቤቱ ሰራተኛ እንደሚገኝ ታውቋል። በመሳሪያ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የዋሉት ተማሪዎች ዕድሜአቸው ከ11 እስከ 17 መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በምዕራብ ካሜሩን መሣሪያ የታጠቁ የተገንጣይ ቡድን አባላት ወደ አንድ የቤተክርስቲያን ትምሕርት ቤት ገብተው 79 ተማሪዎችን ማገታቸው ታውቋል። አጋቾቹ የካሜሩን መንግሥት በደልና ጭቆና አድርሶብናል፣ በሕዝቦችም መካከል ልዩነትን ፈጥሯል በማለት መገንጠልን የመረጡ የምዕራብ ካሜሩን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ክፍለ ግዛት መሣሪያ ታጣቂዎች መሆናቸው ታውቋል።

በምዕራብ ካሜሩን፣ በባሜንዳ ክፍለሃገር፣ በንኩዌን መንደር በሚገኝ የፕሮቴስታን ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ውስጥ በተማሪዎች ላይ በደረሰው ጥቃት የትምህርት ቤቱ ሾፌርና ሌላ የትምህርትቤቱ ሰራተኛ እንደሚገኝ ታውቋል። በመሳሪያ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የዋሉት ተማሪዎች ዕድሜአቸው ከ11 እስከ 17 መሆኑ ታውቋል። መሳሪያ ታጣቂዎች የሚፈልጉት የገንዘብ ካሳ ሳይሆን ትምህርት ቤቱ እንዲዘጋ መጥየቃቸውን በካሜሩን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን መሪ አስታውቀዋል። የቤተክርስቲያኒቱ መሪ እንደገልጹት የታጣቂዎቹ ዓላማ ቤተክርስቲያንን ለማጥቃት ሳይሆን መንግሥት ይፈጽምብናል የሚሉትን በደሎች ለማስቀረትና ለመገንጠልም ከሚታገሉ ቡድኖች የተሰነዘረ የመንግሥት ተቃውሞ ነው ብለዋል።

እገታው በማሕበራዊ ሚዲያ በኩል ይፋ ሆኗል፣

በመሣሪያ ታጣቂዎች የታገቱ ተማሪዎች የቪዲዮ ምስል በማሕበራዊ ሚዲያ በኩል ይፋ መሆኑ ታውቋል። አንሳ የተባለ የኢጣሊያ የዜና አውታር እንደገለጸው በቪዲዮ ምስል የታዩት ተማሪዎች ማንነት በውል ባይታወቅም ቪዲዮን የተመለከቱ አንዳንድ ወላጆች ከተማሪዎች መካከል ልጆቻቸውን መመልከታቸውን አረጋግተዋል። ከአጋቾቹ መካከል አንዱ ለተማሪዎቹ ባስተላለፈው መልዕክት ነጻ የሚለቀቁት ትግላቸው ሲያበቃና ትምህርታቸውንም የሚከታተሉት በቁጥጥር ስር ባሉበት መንደር እንደሆነ መናገሩ ተደምጧል።

ታጣቂዎቹ በሌላ አካባቢም ተማሪዎችን አግተዋል፣

የሰሜን ምዕራብ ክፍለሃገር የመንግሥት ቃል አቃባይ የሆኑት ሉዊ ማሪ ቤኜ እንደገልጹት መሳሪያ ታጣቂዎቹ ወደ ትምህርት ቤት የገቡት ማታ ላይ ተማሪዎቹ በመኝታ ክፍላቸው ተኝተው እያለ መሆኑን ተናግረዋል። ተማሪዎችን ከመኝታቸው ቀስቅሰው ወደ መኪናቸው እንዲገቡ ማድረጋቸውንም አስረድተርዋል። እንደ ቃል አቃባዩ ገለጻ አጋቾቹ በተለያዩ ቡድኖች የተከፋፈሉ እንደሆኑና በሌሎች ትምህርት ቤቶችም ተመሳሳይ ጥቃት ሳይፈጸሙ እንዳልቀረ ተናግረዋል። ባለፈው መስከረም ሰባት ተማሪዎችና የትምህርት ቤቱ ርዕሠ መምህር  በመሣሪያ ታጣቂዎች ተይዘው መወሰዳቸውን በኋላም መለቀቃቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አለም አቀፍ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል።

የካሜሩን አመጽ በሁለት ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል ያለው ልዩነት ነው።

የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የነበረች የምዕራብ አፍሪቃ አገር ካሜሩን የተለያዩ ግጭቶች የተፈራረቁባት መሆኑ ሲታወቅ ከ2008 ጀምሮ  የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑት የሰሜንና የደቡብ ምዕራብ ክፍለ ግዛቶች ከተቀረው የሃገሪቱ ክፍል በመገንጠል አምባዞኒያ በመባል የሚታወቅ ራስ ገዝ ግዛት ለመመስረት የሚታገሉ ሃይሎች መኖራቸው ታውቋል። ለመገንጠልም ዋና ምክንያት ብለው የሚያቀርቡት ማዕከላዊው መንግሥት ከተቀረው የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ለይቶ በደልንና ጭቆናን እንዲሁም ልዩነትን ስለሚያደርስብን ነው ማለታቸው ታውቋል።

ፕሬዚደንቱ ማንኛውንም አመጽ ያወግዛሉ፣

ከሃገሪቱ ነዋሪዎች መካከል 20 በመቶ ብቻ ነዋሪዎች የሚኖርበት የእንግሊዝኛ ተናጋሪዎች ከቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ አመጾችን እንዳካሄዱ፣ ከ1974 ዓ. ም. ጀምሮ በስልጣን ላይ የቆዩት የአገሪቱ ፕሬዚደንት ፖል ቢያ ስልጣናቸውን እንዲለቁ አማጺያኖቹ መጠየቃቸው ታውቋል። 85 ዓመት ዕድሜ የሆናቸው ፖል ቢያ በስልጣን ላይ ለመቆየት ያለፈው መስከረም ወር 2011 ዓ. ም. ለሰባተኛ ጊዜ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ
06 November 2018, 16:34