2018.10.23 Incontro Giovani e Anziani 2018.10.23 Incontro Giovani e Anziani 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች ፍላጎት ላላቸው ወጣቶች ተጽኖ ፈጣሪ መሆናቸው ተገለጸ።

በቅርቡ በሮም በሚገኘው በግሪጎሪያን ጳጳስዊ ዩኒቬርሲት ወጣቶችን እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ወጣቶች ከማኅበርሰቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ በተደረገው “ዓለማቀፍ ማኅበራዊ የማዳመጥ ጥናት” አውደ ርዕይ ላይ ከቀረበው መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው በአሁኑ ወቅት በዓለማቀፍ ደረጃ በመላው ዓለም ከሚገኙ ወጣቶች መካከል 4% ያህሉ ብቻ የካቶሊክn እመንት በተመለከተ የማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮችን በመጠቀም መልእክቶችን እና ሐሳቦችን መለዋወጣቸውን በተልይ ለቫቲካን ዜና ከደረሰው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የእዚህ ጥናት አስተባባሪ የሆኑት ክብርት ማሪያም ዴዝ ከቫቲካን ዜና ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ ገለጹት ይህ ጥናት የተደርገው በዛሬው ዓለማችን ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ከሐይማኖት ጋር ያላቸው ግንኙነት በምን ደረጃ ላይ እንደ ሚገኝ እና ወጣቶች ከእምነታቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመገምገም ታስቦ የተድረገ ጥናት እንደ ሆነ ጠቅሰው ይህንን እውነታ በጥልቀት ለመረዳት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ያለውን ሁኔታ መረጃ ላይ በተመረኮዘ መልኩ ማቀረብ አስፈላጊ ሆነ በመገኘቱ የተነሳ የትደረገ ጥናት እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ይህንን መረጃ ለማግኘት ጥናቱ ትኩረት ያደረገባቸው በተለየ ሁኔታ ወጣቱ ትውልድ በስፋት የሚጠቀምባቸው የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙዕን አውታሮች ትኩረት ተሰጥቶዋቸው ይህ ጥናት መደረጉን የገለጹት የጥናቱ አስተባባሪ ክብርት ማርያም ዴይዝ በዚህም መሰረት ይህ ጥናት ወጣቶች በስፋት የሚጠቀሙባቸው በፌስ ቡክ እና  ኢስታግራም የተሰኙ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ መከናወኑን ገለጸዋል።

ይህ ጥናት በቀዳሚነት “የወጣቶች እምነት እና በማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ላይ በወጣቶች ላይ በቀዳሚነት ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን” ትኩረት በመስጠት መከናወኑን የገለጹት የጥናቱ አስተባባሪ ክብርት ማርያም ዴይዝ በዚህም መስረት ይህ ጥናት ከ18-25 የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ የፌስ ቡክ እና የእስታግራም የመገናኛ አውታሮችን በሚጠቀሙ 540 ሚልዮን ወጣቶች ላይ መደረጉን ጨምረው ገለጸዋል። ከዚህ ጥናት ለመረዳት እንደ ተቻለው እምነትን በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው በማኅበራዊ የመገናኛ ዘርፎች ላይ መልእክቶችን በሚለዋወጡ ወጥቶች ላይ ተጽኖ ፈጣሪ ለመሆን የበቁ ተጽኖ ፈጣሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ከዚህ ጥናት ከተገኘው መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው 4% የዓለማችን ወጣቶች ብቻ ናቸው የካቶሊክ እመንትን በተመለከተ በማኅበራዊ ሚድያዎች ላይ ሐሳባቸውን መለዋወጣቸው ያመለከተው መረጃው በተያያዘም መልኩ ወጣቶች በአብዛኛው በማኅበራዊ ሚድያዎች ላይ የሚፈልጓቸው መረጃዎች ቁሳቁሶችን የመገበያያ መልክእቶች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት እንደሚያደርጉም ከጥናቱ ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

ከጥናቱ ከተገኘው መረጃ ለመረዳት እንደ ተቻለው የካቶሊክ እመንትን በተመለከተ በማኅበራዊ ሚድያዎች ላይ ሐሳባቸውን ከተለዋወጡ ወጣቶች መካከል 5 ሚልዮን የሚሆኑት ከብራዚል መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን 2 ሚልዮን ከፍሊጲንስ 1 ሚልዮን ከሕንድ፣ 900 ሺ የሚሆኑት ከአሜሪካ እና 700 ሺ የሚሆኑት ደግሞ ከጣሊያን መሆናቸውን ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ ጥናት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮችን በበቂ ሁኔታ ቅዱስ ወንጌልን ለማስፋፋት በስፋት ጥቅም ላይ የምታውለው ከሆነ በቀላሉ ከብዙ ሚልዮን የካቶልክ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች ጋር እንድትገናኝ የሚያስችላት እንደ ሆነ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም በበቂ ሁኔታ ያለ ብዙ ድካም የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮችን በመላው ዓለም ለማዳረስ እንደ ሚረዳም ተገልጹዋል።

24 October 2018, 14:42