ቫቲካን 'የሰው ሰራሽ አብርኾት' (AI) በህጻናት ላይ ያለውን ስጋት እና እድሎች' ላይ ኮንፈረንስ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የመንግሥት ደንቦችን ከሥነ ምግባር አንጻር ማጠናከር፣ የልጆችን 'ደህንነት፣ የግል ስብዕና እና ክብር' በማዕከሉ ውስጥ ማስቀመጥ በሚል ጭብጥ ዙሪያ የሚከናወን ኮንፈረንስ ነው።
መጋቢት 11 ቀን በቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት የቀረበው የዝግጅቱ ዓላማዎች፡ ‘የ AI ለህጻናት አደጋዎች እና እድሎች፡ ልጆችን ለመጠበቅ የጋራ ቁርጠኝነት’ የሚል ጭብጥም ተካቶበታል።
በመጋቢት 12 እና 13/2017 ዓ.ም በመካሄድ ላይ ያለው ይህ ዝግጅት በጳጳሳዊ ሳይንስ አካዳሚ ከአለም የሕጻናት ፋውንዴሽን እና ከአንትሮፖሎጂ ኢንስቲትዩት (IADC) ጋር በመተባበር በጳጳሳዊ ጎርጎሪያን ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ ነው።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተሳተፉት የጳጳሳዊ ሳይንስ አካዳሚ ቻንስለር እና የማኅበራዊ ሳይንስ ጳጳሳዊ አካዳሚ ቻንስለር ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ቱርክሰን፣ የጳጳሳዊ የሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዮአኪም ቮን ብራውን፣ በጳጳሳዊ ግሪጎሪያን ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ተቋም የጥበቃ እርምጃዎችን እና የሕፃናትን እና የተጋላጭ ሰዎችን ጥበቃን ለማበረታታት የሚሰራው ተቋም (IADC) ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሃንስ ዞልነር፣ እና የዓለም የሕፃናት ፋውንዴሽን ምክትል ጸሐፊ የሆኑት ብሪታ ሆልምበርግ በኮንፈረንሱ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
AI በግለሰቦች እጅ ውስጥ መሆን የለበትም
ካርዲናል ቱርክሰን የፕሮጀክቱን የጋራ ባህሪ እና ቅድስት መንበር ለአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ያላትን ፍላጎት በማጉላት ንግግራቸውን ከፍተዋል። ካርዲናል ቱርክሰን “አልጎሬቲክስ” (የስለተ ቀመር ስነ-ምግባር) እየተባለ በሚጠራው የአልጎሪዝም ሥነ-ምግባር ላይ ከተደረጉት ውይይቶች ባሻገር፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አብርኾት) “በግለሰብ እጅ” ውስጥ ብቻ እንዳይቀር ለማድረግ እያንዳንዱ መንግሥታት ኃላፊነት መሟገት ያስፈልጋል ብለዋል።
ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ውይይት ማድረግ
ፕሮፌሰር ቮን ብራውን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር ተያይዘው የሚመጡ አደጋዎች ለሳይንስ ማህበረሰብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታዩ መሆናቸውን አጉልተው ገልጿል። እነዚህም የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ - የልጆችን አእምሮ እድገት በእጅጉ የሚጎዳ - የግለሰቦችን መብት ጥሰት እና የልጆችን ምርጫ ለንግድ ዓላማ መጠቀምን ያጠቃልላል ብለዋል።
ቮን ብራውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚቆጣጠሩትን ስልተ ቀመሮችን በማጣቀስ "ለዓመታት የሂሳብ ትምህርት ከሥነ ምግባራዊ አንድምታ ውጭ እንደ ተግሣጽ ይቆጠር ነበር" ብሏል። "ዛሬ ይህ ዋና ጉዳይ አይደለም" ብለዋል።
በፖለቲካው ዘርፍ ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ምሁሩ አሳስበዋል። ለምሳሌ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ይህንን የሚመለከት ረቂቅ ህግ ለሁለት አመታት እንዲታገድ ተደርጓል፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንደ አልፋቤት (የጎግል እህት ኩባንያ) ካሉ ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ውይይት ማድረግ ወሳኝ ነው። በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ፕሮፌሰር ቮን ብራውን እንዳሉት፣ ጳጳሳዊ የሳይንስ አካዳሚ ገንቢ ውይይቶችን ሊያመቻች ይችላል ብለዋል።
አላግባብ መጠቀምን ለመለየት ትብብር
እ.ኤ.አ. በ2017 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ "የቴክኖሎጂ እድገትን የሚመሩ ኩባንያዎች ተወካዮች" በልጆች ጥበቃ ውስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱትን የቅድስት መንበር አርቆ አሳቢነት ፕሮፌሰር ዞልነር አጽንኦት ሰጥተው አድንቀዋል።
ባለፉት አመታት፣ ይህ ሂደት ተቋርጧል፣ አሁን ግን መቀጠል አለበት—በተለይ ቤተክርስቲያን ተቀዳሚ ተልእኮዋ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን መጠበቅ ነው ብለዋል።
በኦንላይን የሚደረግ የመረጃ ምንተፋ ጥቃት
ብሪታ ሆልምበርግ ከ25 ዓመታት በፊት በስዊድን ንግሥት ሲልቪያ የተቋቋመው የዓለም ሕጻናት ፋውንዴሽን፣ በወቅቱ ጥቂት መሪዎች በግልጽ የተወያዩባቸውን ጉዳዮች ለመፍታት ያደረገውን ጥረት አቅርበዋል። በጣም ተጋላጭ የሆኑትን እንደ ስደተኞች፣ ወላጅ አልባ ህጻናት እና ቤት የሌላቸው ታዳጊዎችን የመጠበቅን አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ ሰጥጠዋል።
ሆልምበርግ የጠቀሱት በኢንተርኔት መስመር ላይ የሚፈጸመው ጥቃት መረጃ አስደንጋጭ ነው፡ ከአምስት ሴት ልጆች አንዷ እና ከሰባት ወንድ ልጆች አንዱ በኢንተርኔት ላይ የተለያዩ ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል።
"ቴክኖሎጂ የችግሩ አካል ነው፣ ነገር ግን የመፍትሄው አካል መሆን አለበት" ሲሉ ተናግረዋል፣ ይህን በማድረግም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተገለጹትን ተመሳሳይ ጥንድ ሐሳቦችን በማመልከት አዳዲስ መሳሪያዎች ሁለቱንም አደጋዎች እና እድሎች እንደሚያቀርቡ ደጋግመው አሳስበዋል።