ፈልግ

የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤዎች የኮሙዩንኬሽን ኮሚሽነሮች ፕረዚዳንቶች እና የሀገረ ስብከቶች የማኅበራዊ ግንኙነት ጽ/ቤቶች ዳይሬክተሮች የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤዎች የኮሙዩንኬሽን ኮሚሽነሮች ፕረዚዳንቶች እና የሀገረ ስብከቶች የማኅበራዊ ግንኙነት ጽ/ቤቶች ዳይሬክተሮች   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የሰው ሰራሽ አብርኾት ለበጎ ነገር እንዲጠቀሙ አሳሰቡ!

የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤዎች የኮሙዩንኬሽን ኮሚሽነሮች ፕረዚዳንቶች እና የሀገረ ስብከቶች የማኅበራዊ ግንኙነት ጽ/ቤቶች ዳይሬክተሮች በሮም ለሦስት ቀናት በተካሄደው ኮንፈረንስ ላይ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መገናኛ ብዙኃንን ተቀብለው መዋዕለ ንዋያቸውን በእነርሱ ላይ እንዲያፈሱ ጠይቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ጠላት ሲኖርህ እና ሳታውቅ ስትቀር ህይወትህ ሁለት ጊዜ ለአደጋ ትጋለጣለች። ሆኖም የጠላትን መኖር በማወቅ እና በመገንዘብ አደጋው ይቀንሳል ብለዋል የምዕራብ አፍሪካ የክልል የጳጳሳት ጉባኤ ተወካይ አባ ጆርጅ ንዋቹኩ (RECOWA)።

የቫቲካን የኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ባዘጋጀው እና እ.አ.አ ከጥር 27-29/2025 በተካሄደው አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ከተሳተፉ በኋላ ናይጄሪያዊው ቄስ የቤተክርስትያን መሪዎች እና የቤተክርስቲያኗ ባለድርሻ አካላት ሁሉ የሚዲያ እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው የገለጹ ሲሆን የሚዲያ አድሎአዊነት፣ የመሳሳት ወይም ተገቢ ባልሆነ ተጽዕኖ የመጋለጥ አደጋን ይቀንሳል ብለዋል።

"ይህ ኮንፈረንስ በተለይ የመገናኛ ብዙሃንን ቦታ የሚቆጣጠሩ ብዙ ፕሮፓጋንዳ እና ባለስልጣናትን የምያግባቡ ሲኖሩን ለእኛ የማንቂያ ደወል ነው" ብለዋል። "መነሳት አለብን፣ ከፊት ለፊታችን ያለውን አደጋ እንመልከትና  በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እናድርግ ብለን ራሳችንን እንጠይቅ ብለዋል።

ለቫቲካን ዜና ሲናገሩ አባ ንዋቹቹ የጋራ ጠላትን ለመጋፈጥ የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲተባበሩ ያበረታቱ ሲሆን ጳጳሳትም በመገናኛ ብዙሃን ላይ ፍላጎት በማሳደር እና መዋለ ነዋያቸውን ፈሰስ በማድረግ ግንባር ቀደም ሆነው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በኮሙዩኒኬሽን ሂደት ውስጥ ደፋር መሆን  

ኮሙዩኒኬሽን ለአዎንታዊ ለውጥ እና አደጋዎች ቢኖሩም ግንኙነቶችን ለመገንባት መሳሪያ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ፣ የወንጌል እውነትን በህብረተሰቡ ውስጥ በማሰራጨት ረገድ መልእክተኞች ደፋር እንዲሆኑ ተጠርተዋል።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባሄ ተወካይ እና የሆሣህና አገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት አቡነ  ስዩም ፍራንሱዋ ተገኝተው በጉባዔው ላይ ደፋር መሆንን አስፈላጊነት ለቫቲካን ዜና ተናግረዋል።

"የኮሙዩኒኬሽን ሀላፊነትን ለመቀበል ደፋር መሆን አለብን" ብለዋል ጳጳሱ። "አንዳንድ ሰዎች በመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ላይ አዎንታዊ ናቸው፣ ነገር ግን አንዳንዶች መድረክን ለሐሰት ዜና ይጠቀማሉ እና የሰዎችን ገጽታ ያበላሻሉ። በዚህ መሃል እውነትን በመስበክ ደፋር መሆን አለብን ብለዋል።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እውን ነው

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፅንሰ-ሀሳብ መሆኑ ቀርቶ የዓለማችን ነባራዊ እና ንቁ አካል መሆኑ ክርስቲያኖች እንዲገነዘቡ፣ እንዲሁም በአጠቃቀሙ ክርስቲያኖች ጠንቃቃ እንዲሆኑ የምስራቅ አፍሪካ ጳጳሳት ጉባኤዎች ማኅበር የማኅበራዊ ግንኙነት ክፍል ሊቀመንበር ሆነው የምያገለግሉት አቡነ ስዩም ፍራንሷ ተናግረዋል።

"ቴክኖሎጂን ለክርስቲያኖች የሕነጻ ትምህርት እና ለበጎ ተግባራት ልንጠቀም ይገባል" ብለዋል።

"ስለዚህ ለእነዚህ ለውጦች ትኩረት ልንሰጥ እና በሰዎች የማሰብ ችሎታ መጨናነቅ ውስጥ እንዳንሳተፍ መጠንቀቅ አለብን" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም መዋል አለበት ሲሉም አክለዋል። " እስካላወቅን ድረስ ሰለባ ልንሆን እንችላለን። ስለዚህ ለሰው ልጅ በጎነት ለሕነጻ ትምህርት እንጠቀምበት ብለዋል።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አንፍራ

በካሪቢያን ደሴቶች በትሪኒዳድ እና ቶቤጎ ጋዜጠኛ ለሦስት አስርት ዓመታት በካቶሊክ ኮሙኒኬሽን ውስጥ ያገለገሉት ወይዘሮ ሊዛ ባጃን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በብዙ መስኮች ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ አረጋግጠዋል።

ወይዘሮ ባጃን እንደተናገሩት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች AI መጠቀምን መፍራት የለባቸውም፣ ምንም እንኳን በአግባቡ ለታዳሚዎቻቸው ጥቅም ማዋል አለባቸው ብለዋል።

"የ AI አጠቃላይ ሀሳብ እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ ያለውን ተጽእኖ ከመረመርን በኋላ ስለ አዲሱ ቴክኖሎጂ እና እንዴት በህብረተሰባችን እና በቤተክርስቲያናችን ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ፍርሃትን ማስወገድ አለብን" ብለዋል።

31 Jan 2025, 15:02