ፈልግ

ሙዚቃ አቀናባሪ ማርሴሎ ፊሎቴ እና ፕሮዲዩሰር ማርኮ ዲ ባቲስታ ለ "7" ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ሙዚቃ አቀናባሪ ማርሴሎ ፊሎቴ እና ፕሮዲዩሰር ማርኮ ዲ ባቲስታ ለ "7" ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ  

“የዛሬው የተሰበረ ዓለም፣ በስቅለተ ዓርብ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጩሄቱን ያሰማል!”

የሙዚቃ አቀናባሪ ማርቼሎ ፊሎቴ በሃይዲን ላይ መሠረት ባደረገ ሥራው፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ የተናገራቸው የመጨረሻዎቹ ሰባት ቃላት" በሚል ርዕሥ፣ በጎርጎሮሳውያኑ ስቅለተ ዓርብ ዕለት የሚተላለፍ ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ዝግጅቱን አቅርቧል። አቶ ማርቼሎ ፊሎቴ የጥበብ ሥራውን፣ በተባለው ዕለት እንዲያቀርብ ድጋፍ ያደረገው የቫቲካን ሬዲዮ ጣቢያ መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በማቴ. 27:46 ላይ እንደተጻፈው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ "አምላኬ አምላኬ፥ ለምን ተውከኝ?" ብሎ የጮሄው በመስቀል ላይ ሲሞት የተናገረው ቃል ነው። ይህ አስደንጋጭ የኢየሱስ ክርስቶስ ጩኸቱ፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች ስቅለተ ዓርብን ሲያከብሩት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ ነፍሱን እንዴት አሳልፎ እንደሰጠ ያስታውሳል። 

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1786 ዓ. ም. በተከበረው ስቅለተ ዓርብ ዕለት እንዲቀርቡ የተደረጉት “ሰባቱ የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ላይ የመጨረሻ ቃላት” በዮሴፍ ሃይድ ልብ ውስጥ ያሉት ቃላት እና መነሳሻዎች ናቸው። የእርሱ ሙሉ የክላሲካል ኦርኬስትራ ሥራው፣ መግቢያው በዝግታ እና መደምደሚያው በፈጣን “የመሬት መንቀጥቀጥ” አምሳል የተቀረጹ ሰባት ዋና የአስተንትኖ ክፍሎችን ያቀፈ ነው።

እንደዚሁም ሁለት የጥበብ ሥራዎችን ጨምሮበት የዘመናችንን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በማርቼሎ ፊሎቴ የተቀናበረው የሙዚቃ ስልት የሃይድን ድንቅ ሥራ ትርጉም እና የሰው ልጅ ዛሬ የሚገኝበትን የመቅበዝበዝ፣ ግራ የመጋባት፣ የትንሳኤ እና የተስፋ ፍለጋ ስሜቶች ላይ በማሰላሰል የሙዚቃ አቀናባሪው ማርቼሎ ፊሎቴ የተዘጋጀ ነው።

ቁጥር “7” የሚል ርዕስ የተሰጠው እና አርቲስት ፊሎቴ በድጋሚ ያነበበው የሃይድን ድርሰት ስብስብ፣ ፊሎቴ እንደገለጸው፣ የዛሬውን ዓለም ጫጫታ እና ትርምስ የሚያንጸባርቅ እና ከጳጳሳዊ የሲስቲን ቤተ ጸሎት መዘምራን ጋር በኅብረት የሚዘምረው የፓትሪሲዮ ላ ፕላካ ድምጽ ነው።

በቫቲካን ሬዲዮ የሙዚቃ መርሐ ግብር ውስጥ ተካትቶ የሚቀርብ እና አቀናባሪው የሚገኝበት አስደናቂ የዜማ ሥራው፣ የሃዲንን ሥራ በብዙ መልኩ የሚያስተጋባ ሲሆን፣ በሕማማት ሳምንት በዓለም አቀፍ የሬዲዮ ፕሮግራም በቫቲካን የሰዓት አቆጣጠር እኩለ ሌሊት ከአንድ ደቂቃ ላይ በሆሳዕና ዕለት እሑድ መጋቢት 24/2015 ዓ. ም. የሚተላለፍ ይሆናል። የዜማ ቅንብሩን በቫቲካን ሬዲዮ ረቡዕ መጋቢት 20/2015 ዓ. ም. ማለዳ ላይ ያቀረበው ፊሎቴ፣ ከ50 በላይ የተለያዩ ቋንቋ ክፍሎች ባሉት ሬዲዮ ጣቢያ በኩል መቅረቡ እንዲመሰጥ ማድረጉን ተናግሯል።

የዜማ ቅንብሩ አየር ላይ የዋለበት ቀን ሩሲያ ዩክሬንን የወረረችበት ዕለት እንደበር የገለጸው ፊሎቴ፣ በቫቲካን ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ የሚሠሩት የሩሲያ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል አባላት ወደ ዩክሬን ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦቻቸው መጥተው ያተሰማቸውን ሐዘን መግለጻቸውን አስረድቷል።

የዜማ አቀናባሪው ፊሎቴ በመቀጠልም ጋዜጠኞች፣ ቴክኒሻኖች እና ሌሎች የሬዲዮ ጣቢያው ሠራተኞች ወደ ዩክሬይን ቋንቋ ዝግጅት ክፍል ሲደርሱ ድጋፋቸውን በመስጠት የማያቋርጥ የአብሮነት ስሜት ለዩክሬናውያን የሥራ ባልደረቦቻቸው ሲገልጹ መመልከቱን ተናግሯል። የዜማ ቅንብሩ የመጨረሻ ክፍል የሆነው “የመሬት መንቀጥቀጥ” የተሰኘ ሥራው፣ ከሃዲን የመጀመሪያ ሥራ ጋር የተገናኘ ሲሆን፣ የትርኢቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኞች ድምፅም፣ እያንዳንዱ በራሱ ቋንቋ እና በፊሎቴ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ቅንብር ማስተርስ ቅጂ የተዘጋጀለት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሞት "አምላኬ አምላኬ፥ ለምን ተውከኝ?" በማለት ጮሆ የተናገረውን ቃል የሚያሰማ እንደነበር ተደምጧል። ይህ የዛሬውን የተሰበረ የዓለም ድሆች እና የምድራችንን ጩኸት የሚያስተጋባ አሳዛኝ ለቅሶ፣ በቅድሚያ በዩክሬን ቋንቋ ቀጥሎም በሩሲያ ቋንቋ ተደምጧል።

30 March 2023, 16:12