ፈልግ

POPE-KAZAKHSTAN/

ቫቲካን ተገናኝቶ የመወያየት ባህልን በመገንባት የሴቶች ወሳኝ ሚና ላይ ትኩረት አድርጋለች።

በቫቲካን በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚካሄደው የሴቶች ኮንፈረንስ ሲጀመር የሴቶች ድምጽ "ከዳርቻው ወደ መሃል" መምጣት አለበት የሚል ሐሳብ እየተንጸባረቀ ጉድባሄ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ሴቶች በሀይማኖት ተቋማት መካከል የመገናኘት ባህልን መገንባት" በሚል ርዕስ ሴቶች በሐይማኖት ተቋማት መካከል ለሚደረጉት ውይይቶች የሚያበረክቱት ሚና በተመለከተ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በዚህ ሳምንት በሮም እየተካሄደ ነው።

ጉባኤው በቫቲካን በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚካሄደውን ውይይት በበላይነት በሚመራው ጳጳሳዊ ተቋም የተዘጋጀ ሲሆን ከዓለም ካቶሊካዊ የሴቶች ድርጅት (WUCWO) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።

በቫቲካን በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚካሄደውን ውይይት በበላይነት በሚመራው ጳጳሳዊ ተቋም ዋና ፀሐፊ የሆኑት የእኔታ አባ ኢንዱኒል ጃናካራትኔ ኮዲቱዋኩኩ ስለ ኮንፈረንሱ እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል የመገናኘት ባህልን የማጎልበት ግቡን አስመልክቶ ለቫቲካን ዜና አገልግሎት ዘጋቢ ቲዚያና ካምፒሲ ተናግሯል።

በሃይማኖታዊ ውይይት ውስጥ የሴቶች ሚና

ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት የሃይማኖቶች ጉባሄ ለምን ይዘጋጃል? የተሰኘው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር

መልስ

ይህን ውሳኔ በሚገባ ለመረዳት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን በጣሊያነኛ ቋንቋ “Fratelli Tutti” (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” የተሰኘውን ሐዋርያዊ መልዕክት መጥቀስ ያስፈልጋል እንዲህም ይላል፡- “በዓለም ዙሪያ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች አደረጃጀት ሴቶች ከወንዶች እኩል ክብርና ተመሳሳይ መብት እንዳላቸው በግልጽ ከማንጸባረቅ የራቀ ነው። በቃላት አንድ ነገር እንናገራለን ነገር ግን ውሳኔዎቻችን እና እውነታዎቻችን ሌላ ታሪክ ያሳያሉ።

ኮንፈረንሱ “በሃይማኖት ተቋማት መካከል ለሚያደርጉት ውይይቶች ልዩ አስተዋጽዖ” ቦታ ለመስጠት እና “ድምፃቸውን ከዳርቻው ወደ መሃል ለማምጣት እና ታሪኮቻቸውን ለማበረታታት” ቦታ ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል ።

ዓለም አቀፍ የሴቶች አውታረ መረብ

ሌላው ዓላማ በሃይማኖት ተቋማት መካከል በሚደረጉ ውይይቶች ላይ የሴቶች ትስስር መፍጠር ነው ብሏል። ተሳታፊዎች - ከ 23 የተለያዩ ሀገሮች የመጡ - ሲሆን ግንኙነቶችን እንዲፈጥሩ ይበረታታሉ፣ ወደ እየአገሮቻቸው ሲመለሱ የአካባቢ እና ብሔራዊ አውታረ መረቦችን መፍጠር እንዲችሉ ይረዳቸዋል።

ሃሳቡ ለቀጣይ ትብብር ማበረታቻ በዓመት ውስጥ አንድ በአህጉር ውስጥ ሌላ ተከታታይ በአካል በመገኘት ኮንፈረንሶችን ማካሄድ ነው ብሏል።

በሃይማኖቶች መካከል የመገናኘት ባህል መፍጠር

የመገናኘት ባህል አለ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት አባ ኢንዱኒል “ሌሎችን ማግኘት የምንማርክበት” አንዱ መንገድ ነው ያሉ ሲሆን ይህ መነሳሳት፣ “ከእኛ መንፈሳዊነት፣ ከሃይማኖታዊ አስተምህሮአችንም ሊመጣ ይገባል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የንግግር ወይም የውይት አምላክ ነውና፣ እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ጀምሮ ከሰው ልጆች ጋር ይነጋገራል፣ ይላል መጽሐፍ ቅዱሳችን በማለት ተናግረዋል።

ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በተገናኘንበት ወቅት ብዙ ልዩነቶችን እናገኛለን - "ሃይማኖቶች ሁሉም አንድ አይደሉም" - ነገር ግን ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች አሏቸው፣ ምክንያቱም "ኃይማኖቶች እርስ በርስ የሚጣመሩ እሴቶች ስላሏቸው "ሁለንተናዊ" እሴቶች ብለን እንጠራዋለን ህግ፣ ፍትህ፣ ሰላም፣ ስምምነት፣ አብሮ መኖር”

"በእነዚህ ሁለንተናዊ እሴቶች መሰረት" አባ ኢንዱኒል ጨምረው እንደ ተናገሩት ከሆነ “ድልድዮችን መገንባት እና ሁሉንም የሚያካትቱ ፕሮጀክቶችን ማቀድ እንችላለን” ብሏል።

 

27 January 2023, 16:32