ፈልግ

በሲኖዶሳዊ ጉዞ ላይ የሚታይ የውይይት፣ የመደማመጥ እና የማስተዋል ሂደት መቀጠሉ ተገለጸ

የቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ሂደት አህጉራዊ መድረክን የሚመሩ አባላት ኅዳር 19 እና 20/2015 ዓ. ም. በሮም ባካሄዱት ስብሰባ፣ የሲኖዶሳዊ ሂደቱን ከሚከታተሉ የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አባላት ጋር ተገናኝተዋል። ሰኞ ኅዳር 19/2015 ዓ. ም. የዓለም አቀፍ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ፕሬዚዳንቶች እና አህጉራዊ የሥራ አስተባባሪዎች በሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ተገናኝተው ስብሰባ አካሂደዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የየአህጉራቱ የሲኖዶሳዊ ሂደት ተወካዮቹ ሰኞ ኅዳር 19/2015 ዓ. ም. ባደረጉት ስብሰባው የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጥቅምት 17/2015 ዓ. ም. ያስተዋወቀውን አህጉራዊ መድረክ በተመለከተ መረጃ አቅርበዋል። በሲኖዶሳዊ ሂደት በቀጥታ የሚሳተፉ የእያንዳንዱ ክልል ተወካዮች፣ ማለትም የእስያ ፣ የአፍሪካ ፣ የኦሺኒያ ፣ የሰሜን አሜሪካ ፣ የመካከለኛው ምስራቅ ፣ የላቲን አሜሪካ እና የአውሮፓ ተወካዮች እንዲሁም ቀደም ሲል የነበሩ ስብሰባዎችን የተሳተፉ አባላት አኅጉራዊ ስብሰባዎችን ለማካሄድ የሚያግዙ ዓላማዎችን እና ዘዴዎችን በመረጃነት አቅርበዋል።

ልዩ ልዩ ልዑካን የአህጉራዊ መድረክ የሥራ ሰነድን ካነበቡ በኋላ የተሰጡ አስተያየቶች እንዳመለከቱት፣በየአገራቱ ሠራዊት ውስጥ የሚገኙ ምዕመናንን እና ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሥነ መለኮታዊ ይዘቱንም ማዳበር አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ብዙ ሰዎች ለስቃይና ለመከራ መጋለጣቸውን የጠቀሰው አስተያየቱ፣ እስካሁን በጳጳሳት ጉባኤዎች ደረጃ የተካሄደውን ሲኖዶሳዊ ሂደት በመገምገም፣ እንዴት ቤተክርስቲያን መሆን እንደሚቻል ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያቀረቡትን አዲስ ራዕይ ለመረዳት የሚያስችል መድረክ መዘጋጀቱ ታውቋል።

በአህጉራዊ ሰነድ ላይ የሚደረግ ተጨማሪ ውይይት

እስካሁን የተካሄዱ ሲኖዶሳዊ ደረጃዎችን የተካፈሉት የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽ/ቤት አማካሪ ክቡር አባ ጃኮሞ ኮስታ፣ የሲኖዶሱ አህጉራዊ ደረጃን ለማዋቀር የሚያግዙ አንዳንድ ዘዴዎችን አቅርበዋል። የአሠራር ዘዴ ዋና ዓላማ ለአህጉራዊ ደረጃ በቀረበው የሥራ ሰነድ ላይ የሚደረገው ውይይት ለማበረታታት መሆኑን አስረድተዋል። በሁሉም ቁምስናዎች፣ በሰበካዎችና በአገር አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ውይይቶችን የያዘ እና በሺህ የሚቆጠሩ ገፆች ያሉትን የምክክር ሂደት የውይይት ሰነድ ለተጨማሪ ውይይት መቅረቡት ያስታወቁት አባ ጃኮሞ ኮስታ፣ የመጨረሻ ሰነዱ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ለሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሚቀርበው ከተጨማሪ ውይይት በኋላ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል።

መሪ ጥያቄ

የመጨረሻ ሰነዱ በሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽ/ቤት ወይም በማኅበረሰብ ክፍል ጥናት ከተደረገ በኋላ የሚጸድቅ ሐዋርያዊ መመሪያ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሕዝብ የምክክር ፍሬ መሆኑን ክቡር አባ ኮስታ ጨምረው አስገንዝበዋል። በየአገራቱ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሕይወት እንዴት እንደሆነ እና መንፈስ ቅዱስ ወዴት እየመራን እንደሆነ ለመገንዘብ የምክክር ሂደቱ አሁንም እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። ይህን የምክክር ሂደትን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያግዝ ልዩ የልምድ፣ የግንዛቤ እና የጥያቄ ዘዴዎች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የየአገራቱ ቤተ ክርስቲያናት ሐዋርያዊ አገልግሎት ቅድሚያን በመስጠት አስተዋፅዖ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

አስፈላጊ የማስተዋል ዓይነት

ሲኖዶሳዊ ሂደቱ ከቃላት ባሻገር በጥልቅ የማዳመጥ እና የማስተዋል ጥበብን እንደሚጠይቅ የተናገሩት ክቡር አባ ጃኮሞ ኮስታ ቀጥለውም፣ በሲኖዶሱ ሂደት ውስጥ ሁለት አስፈላጊ የማስተዋል ዓይነቶች መኖራቸውን ገልጸው፣ ብጹዓን ጳጳሳት በሥነ መለኮት በመታገዝ የሚያደርጉት የማስተዋል ሂደት እንደሆነ ተናግረው፣ ይህም ተጨማሪ ሌሎች ጥያቄዎችን ለመጠየቅ የሚረዳቸው መሆኑን አስረድተዋል።

29 November 2022, 16:29