ፈልግ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በባሕሬን በተካሄደው የውይይት መድረክ መዝጊያ ላይ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በባሕሬን በተካሄደው የውይይት መድረክ መዝጊያ ላይ  (Vatican Media) ርዕሰ አንቀጽ

“ሃይማኖቶች አመጽን የሚቀሰቅስ ማንኛውንም ተግባር መቃወም ይገባል!”

ርዕሠ አንቀጽ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በባሕሬን በተካሄደው “የምሥራቁ እና የምዕራቡ ዓለም የሰው ልጆች አብሮ መኖር” በሚል ርዕሥ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ መዝጊያ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ “የሁሉም ሃይማኖቶች ተከታዮች፣ እግዚአብሔርን በመናቅ አመጽን እና ጦርነትን የሚቀሰቅሱ ተግባራትን መቃወም እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።  

በባሕሬን ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት የሚገኝባት አዋሊ ከተማ፣ በጦርነት ውስጥ ከምትገኝ የክርስቲያን አህጉር አውሮፓ በጣም ርቃ የምትገኝ ብትሆንም፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዩክሬን ጦርነት እንዲያቆም ጥሪ አቅርበዋል። ከባሕረ ሰላጤው አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ባሕሬን በመልክአ ምድር አቀማመጥ ከምስራቅ አውሮፓ ርቃ የምትገኝ ቢሆንም ነግር ግን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያደረባቸውን ስጋት በመግለጽ ሦስተኛው ዓለም ጦርነት የሚካሄድባቸው አገራት በማለት የጊዜው ከሚጠሯቸው አገራት መካከል አንዷ ለሆነች የመን ቅርብ እንደሆነች ይታወቃል።

ካለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች እና ቀጥሎም ከታዩት ቀዝቃዛው ጦርነቶች በኋላም ቢሆን ዓለማችን ለአስርተ ዓመታት በጥርጣሬ ውስጥ እንዲቆይ፣ በሁሉም የዓለም ክፍሎች አስከፊ ግጭቶች እየተከሰቱ፣ በዛቻዎች እና ኩነኔዎች መካከል እንገኛለን” የሚለው አስተያየት አንድን ሰው ሊያስገርም ይችላል። የሰው ልጅ በሙሉ ዛሬ የኑክሌር ጦርነት ሊያስከትል በሚችለው እና ሊመዘኑ በማይችሉ መዘዞች ስጋት ውስጥ እንደሚኖር መረጃዎች ያመላክታሉ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህን እርስ በራሱ የሚጋጭ ሁኔታን በንፅፅር ተመልክተዋል። በአንድ በኩል አብዛኛው የዓለም ሕዝብ በረሃብ፣ በፍትህ እጦት፣ በሥነ-ምህዳር ቀውሶች እና በተለያዩ ወረርሽኞች የተጠቃ ነው። በሌላ በኩል በጣት የሚቆጠሩ ‘ኃያላን’ የሚባሉ ሰዎች የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚደረግ ትግል ላይ በማትኮር ተፅዕኖን የሚፈጥሩ ተቃዋሚ ክፍሎችን በአዲስ መልክ በማዋቀር ላይ ይገኛሉ። ለአሥርት ዓመታት የተካሄደው ግልጽ ውይይት፣ ከዚህ በፊት ለተደረጉት ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ጠንካራ መሪ በነበረው የቀድሞ ወታደራዊ ኅብረት ሕግ መመራቱ ቀርቶ አሁን ፀሐይ ላይ እንደተሰጠ በረዶ እየቀለጠ እና እየጠፋ የመጣ ይመስላል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህን እየሆነ ያለውን ነገር “የህጻን ጨዋታ” በማለት ገልጸው፣ “ስለ ሰው ልጅ የወደፊት እጣ ፈንታ ከማሰብ ይልቅ "ሐዘንና ሞትን በሚያስከትሉ የእሳት፣ የሚሳይል እና የቦምብ መሳሪያዎች ላይ እየተጫወተ ይገኛል” በማለት ተናግረዋል። ልቅሶና ሞት ግጭቶች ሊያስከትሉ የሚችሏቸው አሳዛኝ መዘዞች ናቸው። ከውይይት እና ከመግባባት ይልቅ ተቃዋሚዎች ጎልተው በመውጣት አንድ ሰው “የራሱን የጨካኝ፣ የኢምፔሪያሊስት ሥርዓት፣ የብሔርተኝነት እና የሕዝባዊነት ርዕዮተ ዓለምን” በሌሎች ላይ መጫንን ቀጥሏል። የምጣኔ ሃብት እና የርዕዮተ ዓለም ቅኝ ግዛት ወይም የኢምፔሪያሊስት ሥርዓት የበላይነት ምኞት ሰላምን፣ የሁላችን ደኅንነት እና የዓለምን የወደፊት እጣ ፈንታን አሳንሷል ወይም አበላሽቷል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በባሕሬን ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅት በድጋሚ ያቀረቡት ጥሪ በግዴለሽነት ለመቆየት አይደለም። “የሕዝቡን ጩኸት እና የድሆችን ድምፅ በመስማት” ፣ “መልካሙን እና ክፉውን ለመለየት” ሳይሆን “እርስ በርስ ተግባብተን በበጎ ነገር ላይ ለመተባበር" ጥረት እንድናደርግ የቀረበ ጥሪ ነው። ዓለማችን ከምን ጊዜውም በላይ የተቀራረበ መሆኑን በመገንዘብ፣ የወንድማማችነት እና የሃይማኖቶች መለያ ባህሪያቸው ወይም ቀዳሚ ሚናቸው የሰላምን መንገድ ማመላከት መሆን አለበት።

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ በክርስቲያን ወንድሞች እና እህቶች እንዲሁም በሙስሊም እና ሌሎች ሃይማኖቶች መሪዎች ፊት ቆመው ባስተላለፉት መልዕክት፣ በፈጣሪ የሚያምን ሁሉ ጦርነትን፣ ፈጣሪን የሚያናንቁ ንግግሮችን፣ ጽሑፎችን እና ድርጊቶችን ለአመጽ ተግባር የሚያውሉትን በኃይል መቃወም እንደሚገባ ተናግረው፣ ዓመፅን እና የጦር መሣሪያ ትጥቅን ለማደራጀት የሚደረገው ሩጫ እንዲቆም፣ የጦር መሣሪያ ንግድን እና ከንቱ የሕይወት መጥፋን መቃወም እንደሚገባ በጥብቅ ማሳሰባቸውን በመግለጽ ርዕሠ አንቀጹ መልዕክቱን ደምድሟል።

08 November 2022, 16:52