ፈልግ

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክትባት እራስን እና ሌሎችን በጋራ ለመከላከል የሚደረግ የፍቅር ተግባር ነው!

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት አገልግሎት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት እና በቫቲካን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ኮሚሺን፣ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በማስመልከት ያስተላለፉትን ሐዋርያዊ አስተምህሮን መሠረት በማድረግ በጋራ ባዘጋጁት ሦስተኛ ዙር የቪዲዮ ቅንብራቸው፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክትባት ሰዎችን ከወረርሽኙ ለመከላከል የሚደረግ የፍቅር ተግባር መሆኑን አስታውቀዋል። ጽ/ቤቶቹ የር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስን ዓለም አቀፍ የጤና ቀውስ አስተምህሮን በመዳሰስ ባዘጋጁት የቪዲዮ ቅንብር፣ አንድ ሰው ወረርሽኙ ካስከተለው ቀውስ ሲተርፍ ሕይወቱ ቀድሞ ከነበረበት ጋር ተመሳሳይ እንደማሆን ገልጸው፣ ነገር ግን የተሻለ ወይም የከፋ እንደሚሆን ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው በአስተምህሮአቸው “አንድ ሰው ራሱን ብቻ ከወረርሽኙ ማዳን አይችልም” ማለታቸውን እና “ከአደጋው መዳን የሚቻለው ሌሎችንም ከወረርሽኙ መከላከል ሲቻል ነው” ማለታቸውን አስታውሰዋል።

13 August 2022, 16:34