ፈልግ

12ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት ስብሰባ በጄኔቫ በተካሄደበት ወቅት 12ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት ስብሰባ በጄኔቫ በተካሄደበት ወቅት   (AFP or licensors)

ቅድስት መንበር ለዓለም ንግድ ድርጅት፡ ዓለም የባለብዙ ወገን ውይይትና ትብብር ያስፈልገዋል ማለቷ ተገለጸ

በጄኔቫ በተካሄደው 12ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ (M12) ስብሰባ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት እና ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የቫቲካን ቋሚ ታዛቢ ባደረጉት ንግግር ዛሬ አለም የተጋረጠውን አለም አቀፍ ቀውሶች ለመቅረፍ አዲስ ትብብር እና ውይይት እንደ ሚያስፈልግ መናገራቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቅድስት መንበር የብዙ ወገን ውይይት በንግድ ጉዳዮች ላይ ያለውን ጠቀሜታ እና ኮቪድ ቀጣይነት ያለው ተጽእኖን ጨምሮ ዛሬ አለማችን እያጋጠሟት ያሉትን በርካታ ቀውሶች ለመቅረፍ በጋራ ቤት የጋራ ጥቅምን በማስተዋወቅ ላይ የተመሰረተ ሁለንተናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ ቅድስት መነበር በቋሚ ተወካዩዋ አማካይነት ገልጻለች። የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ በዩክሬን ውስጥ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት እና የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትኩረት አድርጋ መናገሯ ተገልጿል።

በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት እና ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች የቫቲካን ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ፎርቱናቱስ ንዋቹቹ በአለም ንግድ ድርጅት (WTO) 12ኛው የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ  ስብሰባ ላይ በእነዚህ ነጥቦች ላይ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በጉባዔው ላይ የተወያዩባቸው ጉዳዮች

ኮንፈረንሱ በቦነስ አይረስ፣ አርጀንቲና ከተካሄደ አምስት ዓመታት በኋላ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት እ.አ.አ ከሰኔ 12-16/2022 ዓ.ም በድጋሚ ተሰብስቧል። መጀመሪያ ላይ እ.አ.አ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2021 መካሄድ የነበረበት ቢሆንም የኦሚክሮን አዲሱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመከሰቱ ምክንያት በስዊዘርላንድ እና በሌሎች በርካታ የአውሮፓ ሀገራት የጉዞ ገደቦችን እና የለይቶ ማቆያ መስፈርቶችን በማስከተሉ የተነሳ ተሰርዞ ነበር።

የንግድ ሚኒስትሮች እና ከድርጅቱ 164 አባላት የተውጣጡ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የተሳተፉበት የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ የዓለም ንግድ ድርጅት ከፍተኛው ውሳኔ ሰጪ አካል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በየሁለት ዓመቱ የሚሰበሰበው በማንኛውም የባለብዙ ወገን የንግድ ስምምነቶች ላይ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል።

ለኮቪድ-19 ክትባቶች የባለቤትነት መብት መስጠትን፣ የምግብ ደኅንነት እና ግብርናን፣ የአሳ ሀብት ድጎማዎችን እና የዓለም የንግድ ድርጅት ላይ መከናውን ስለሚገባው ማሻሻያዎች ጨምሮ በዓለም የንግድ ድርጅት ወቅታዊ ድንገተኛ ምላሽ ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እንደ ተካሄዱ ተገልጿል።

የዓለም ንግድ ድርጅትን እና የባለብዙ ወገን አቀራረቡን ማደስ

ሊቀ ጳጳስ ንዋቹቹ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር አሁን በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ክፉኛ ያባባሰውን የ COVID-19 ቀውስ ተከትሎ የዓለም ንግድ ድርጅትን እና የባለብዙ ወገን አቀራረቡን ለማነቃቃት አፋጣኝ እርምጃ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው ትናግረዋል። ወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ ያገረሸው “የጋራ ጥቅምን ከመፈለግ ይልቅ የገበያ ቦታን ፍፁም ራስን በራስ የማስተዳደር እና የፋይናንስ ግምቶችን የሚከላከሉ ወደ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች እና ርዕዮተ ዓለሞች የተተረጎመ ግለሰባዊ አቀራረብን መከተሉን” ጥቅም የሌለው መሆኑን ተናግረዋል።

ፍትሃዊ የባለብዙ ወገን የንግድ ስርዓት

ስለዚህም የዓለም ንግድ ድርጅት ፍትሃዊ የባለብዙ ወገን የግብይት ሥርዓትን ከማረጋገጥ አኳያ ያለውን ወሳኝ ሚና በተለይም ለበለፀጉ አገሮች ያለውን ወሳኝ ሚና አበክረው ሲገልጹ “ነፃ ንግድ፣ ክፍትና ደንብን መሠረት ባደረገ የባለብዙ ወገን የንግድ ሥርዓት መፍጠር ለዕድገትና ለልማት በጣም ኃይለኛ ሞተር” ብለዋል።

“የባለብዙ ወገን የንግድ ሥርዓት ብቻ ክልሎች በህዝቦች መካከል የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖር እና ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት በተለይም በጣም ድሃ አገሮች የሕግ-ኢኮኖሚያዊ ስርዓትን በማዳበር የመሳተፍ እድል ይሰጣል ያሉ ሲሆን ጤናማ የዓለም ኢኮኖሚ መገንባት ከፈለግን በዚህ የታሪክ ወቅት የሚያስፈልገው የጋራ አስተሳሰብ ባለው የጋራ ቤት ውስጥ የጋራ ጥቅምን በማስተዋወቅ ላይ የተመሰረተ ሁለንተናዊ አካሄድ ነው ብለዋል።

ንግድ እና አካባቢ

በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት እና ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች የቫቲካን ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ፎርቱናቱስ በመቀጠል ስለ ንግድ እና ስለ አካባቢው ሲናገሩ በተለይ ከበለጸጉ አገሮች የተለየ ታዳጊ አገሮች ፍላጎቶችን በመጥቀስ የተናገሩ ሲሆን የንግድ ፖሊሲ ለዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት አጀንዳ አስተዋፅዖ ለማድረግ እና ለማስተዳደር የራሱ የሆነ ውጤት አለው፣ ነገር ግን ውስን ወሰን እንዳለው በመጥቀስ ሊቀ ጳጳስ ንዋቹኩ የዓለም የንግድ እና የአካባቢ ጥበቃ ደንቦችን ከ«የሰላም አንቀፅ» ጋር በማጣመር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ያስችላል ብለዋል። በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ከንግድ ጋር የተያያዙ የአካባቢ ጥበቃ እርምጃዎች ማካሄድ ይችሉ ዘንድ ማገዝ ያስፈልጋል ብለዋል።

ትኩረታችን ጠንካራ ሆኖ መቀጠል አለበት እና ማንንም ላለመተው እና በ 2030 የበለጠ ቀጣይነት ያለው ዓለም ለመገንባት በገባነው ቁርጠኝነት የማይናወጥ መሆን አለብን።

የአዕምሮ ንብረት መብቶች

የወቅቱን የኮቪድ-19 ቀውስ በመጥቀስ፣ ሊቀ ጳጳስ ንዋቹቹ የቅድስት መንበር አቋም የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሀገራት የአእምሯዊ ንብረት መብቶች “ክትባቶችን እና መድሃኒቶችን ጨምሮ ተመጣጣኝ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ የህክምና ምርቶችን በወቅቱ ለማግኘት ምንም ዓይነት እንቅፋት እንዳይፈጥሩ ለማድረግ እንደ ምትሰራ የቅድስት መንበር አቋም ደግመው አረጋግጠዋል። ኮቪድ-19ን ለመዋጋት አስፈላጊ የሆኑትን የምርምር፣ ልማት፣ ማምረት እና የህክምና ምርቶች አቅርቦትን ለማሳደግ እንቅፋት የሚሆኑትን ጉዳዮች ሁሉ ቅድስት መንበር በተቻላት አቅም እንደ ምትዋጋ አክለው ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ የዓለም ንግድ ድርጅት ወረርሽኙን በተመለከተ ምላሽን በተመለከቱ የአእምሮአዊ ንብረት ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለፉት ወራት የተካሄዱትን መደበኛ እና መደበኛ ያልሆነ ድርድር ቅድስት መንበር በደስታ እንደምትቀበል ገልጿል። ማንኛውም ስምምነት ውጤታማ፣ ሁሉን አቀፍ እና ሊተገበር የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

20 June 2022, 13:29