ፈልግ

የቅድስት መንባር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የቅድስት መንባር ዋና ጸሐፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን  

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ማልታን የሚጎበኟት የወንጌልን ሰላማዊነትን በማንገብ ነው ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ ሳምንት ማብቂያ አከባቢ ማለትም ከመጋቢት 24-25/2014 ዓ.ም  ድረስ 36ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ ወደ ማልታ ደሴት እንደ ሚያቀኑ ይታወቃል። ይህንን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማልታ የሚያደርጉትን 36ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት ዋዜማ ላይ የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ከሬዲዮ ቫቲካን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደ ገለጹት ሕይወትን ለማዳን የጋራ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የገለጹ ሲሆን ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማልታ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የስደት ክስተት እና ሁሉም ጦርነቶች እንደሚቆሙ ተስፋ የሚሰጥ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሆነ ገልጸዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

መቀበል፣ መንከባከብ፣ ማቋቋም/ማደረጀት እና ማዋሃድ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማልታ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ በተመለከተ የቫቲካን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ ከሆነው ማሲሚሊያኖ ማኒኬቲ ጋር ቃለ ምልልስ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በመሳደዳቸው፣ ከአመጽ ወይም የተሻለ የወደፊት ሕይወት ፍለጋ የገዛ አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ እና የሚሹትን ሰዎች ሁሉ ለማቀፍ ይቻል ዘንድ ከላይ የተጠቀሱትን በቅዱስ አባታችን የተገለጹትን እነዚህን አራት ግሦች በማስታወስ መላው የአውሮፓ ማሕበርሰብ ስደተኞችን ተቀብሎ በማስተናገድ የጋራ መጋራት እና ኃላፊነታቸውን ይወጡ ዘንድ ጋብዘዋል።

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት ማዕከል ላይ "ለሕይወት ምክንያቶችን ለመስጠት እና ዛሬ ባለው ዓለም ውስጥ በጣም እንደሚያስፈልገንን ተስፋን መልሶ ለማጎናጸፍ ይቻል ዘንድ ቅዱስ ወንጌልን ማወጅ ነው” በማለት መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን እ.አ.አ በ 2020 ዓ.ም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተራዘመው የስደተኞች ጉዞ እና በአሁን ወቅት በዩክሬይን በተከሰተው ጦርነት የተነሳ የሚሰደዱ ሰዎች ብዛት እየጨመረ በአንድ ጊዜ እነዚህ ሁለቱ አብይት ክንውኖች የስደተኞችን ፍልሰት እንዲ ጨምር ያደርጉ ምክንያቶች እንደ ሆኑ ገልጸዋል። በዩክሬን ጦርነት እንደተለመደው ከጳጳሱ ጎን የሚቆሙት ካርዲናሉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት ማዘናቸውንና የጦር መሣሪያዎቹ ጸጥ እንዲሉ ያላቸውን ተስፋ በድጋሚ ገልጸዋል።

ጥያቄ፤ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በምን ዓይነት መንፈስ ነው ሐዋርያዊ ጉዞዋቸውን ለማድረግ እየተዘጋጁት?

መልስ፤ በእርግጠኝነት ይህ በጉጉት የሚጠበቀው ጉዞ በኮቪድ 19 ምክንያት አንድ ጊዜ ስለተራዘመ እና በተመሳሳይ ጊዜም በዚህ የጦርነት አውድ ውስጥ እየተካሄደ ስለሆነ ቅዱስ አባታችንን በእጅጉ እያስጨነቀ ያለው ጉዞ ነው። ስለዚህ ባለፉት ወራት እና በቅርብ ሳምንታት በዩክሬን እየሆነ ላለው ነገር ከዚህ ቀደም በተለያዩ አጋጣሚዎች በተገለጠው በዚህ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ሆነው ይህንን ጉዞ ያደርጋሉ ብዬ አስባለሁ። እናም ምንም እንኳን ተጨባጭ ውጤት ያላመጣ ቢመስልም ድርድር እየተካሄደ ስለሆነ ጦርነቱ እንዲቆም፣ ውዝግቡ በሰላም እንዲፈታ እና ውይይቱ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን በድጋሚ ያሰማሉ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ የዚያ ህዝብ ስቃይ ስቃያቸው እንደሆነ አድርገው በመውሰድ በዚህ የስቃይ መንፈስ ውስጥ በመሳተፍ እና ጦርነቱ እንዲቆም ግብዣ ያቀርባሉ ብዬ አስባለሁ።

ጥያቄ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማልታን በተመለከተ ከዚህ በፊት እንደ ገለጹት በሜዲትራኒያንን ባሕር መካከል የምትገኝ "ሰማያዊ በረሃ" በማለት ገልጸው ነበር። የስደትን አሳዛኝ ሁኔታ የሚያስታውስ ቦታ ነው። አውሮፓ ለዩክሬን ስደተኞች ብዙ እየሰራች ነው፣ አዲስ ተስፋ ፍለጋ አገሮቻቸውን ጥለው ባሕር አቋርጠው እየመጡ ላሉ ስደተኞች ከዚህ በላይ አውሮፓ ምን ማድረግ ትችላለች?

መልስ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ጌታን እናመስግን፣ ምክንያቱም ከዩክሬን ለመጡ ስደተኞች እውነተኛ አብሮነት የሚገልጹ ተግባራትን ለማከናወን ያለውን ውድድር እያየን ነው። የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እያደረጉላቸው ያለው ነገር በእውነት የሚደነቅ ነው። ይህ አሳዛኝ አጋጣሚ ከደቡብ አህጉራት ለሚመጡት ሌሎች ስደተኞች ለመርዳት ይችላ ዘንድ ስሜታችንን የበለጠ እንዲጨምር እንደሚረዳ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እናም በዚህ ረገድ ከመተባበር እና  "ጫናዎችን" በኃላፊነት ከመጋራት ሌላ አማራጭ እንደሌለ ይሰማኛል - በዚህ መልኩ መናገር እንችላለን - በሁሉም የአውሮፓ ሀገሮች፣ በተለይም በመዳረሻው ላይ በመጀመሪያ መዳረሻ እና ከዚያም በጉዞዋቸው የመጨረሻ መዳረሻቸውን ከሚያደርጉባቸው አገራት ጋር መተባበር ያስፈልጋል።

ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ ቅድሚያ የሚሰጠው - ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ብዙ ጊዜ እንደሚደጋግሙት - ህይወትን ማዳን፣ በባህር ላይ ህይወትን ማዳን ነው። ይህ ደግሞ በመደበኛ መንገድ የሚደረጉትን ለፍልሰት የሚሆኑ መንገዶችን በመጨመር ሊከናወን ይችላል። እናም ከዚያ በይበልጥ ደግሞ ማንም ሰው በግጭት ሁኔታዎች፣ በአስተማማኝ ሁኔታዎች ወይም በልማት እጦት የተነሳ ማንም ሰው ከትውልድ አገሩ እንዳይወጣ መስራት ያስፈልጋል። ስለዚህ በትውልድ አገሮቻቸው በተለይም በኢኮኖሚ ልማት፣ በፖለቲካዊ መረጋጋት፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብዓዊ መብት መከበር ረገድ ተግብራት ሊከናወኑ ይገባል፣ ይህንን ተግባር የሚያጠናክር መዋለ ነዋይ ፈሰስ ማድርግ ይገባል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የገለጹልንን አራቱን ግሦች በማጣመር ስደተኞችን መቀበል፣ መንከባከብ፣ ማቋቋም/ማደረጀት እና ማዋሃድ እነዚህን ሁሉንም በአንድ ላይ በማጣመር መሥራት ያስፈልጋል። የትኛውም ሀገር ብቻውን ሃላፊነት ሊወስድ አይችልም። ከሲቪል ማህበረሰብ ጋር በተለይም የሃይማኖት ተቋማት እና የካቶሊክ ቤተክርስትያንን ጨምሮ የጋራ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል።

ጥያቄ፤ ከቆጵሮስ እና ከግሪክ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቅዱስ ጳውሎስ መርከብ የሰመጠችበት ደሴት ለመሄድ ተቃርበዋል - ይህ ደግሞ ለአሕዛብ ወገን ቅዱስ ወንጌልን የሰበከውን ታላቁን ሐዋርያ ፈለግ መከተልን ያሳያል።  የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የጵጵስና ማዕረግ አስረኛው ዓመት ላይ ደርሰናል፣ በተለይ ቅዱስ አባታችን የሚፈልጓትን ቤተ ክርስቲያን በማሰብ ምን ዓይነት ግምገማ ማድረግ እንችላለን?

መልስ፡ በዚህ አሥረኛው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የጵጵስና ዘመን፣ ወደ ማልታ ጉዞ መደረጉ ለእኔ ጠቃሚ ይመስላል፣ ምክንያቱም ማልታ ከወንጌላዊው የቅዱስ ጳውሎስ መልክ ጋር የተቆራኘ ስለሆነ እና አንድ ማስታወሻ በእዛ ስፍራ ስላለ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዘመነ ጵጵስናቸው  በጽናት ያሳወቁት፣ ቤተክርስቲያን ሚስዮናዊ እንድትሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሚስዮናዊ መሆኗን በብቃት እያስመስከረች እንድትሄድ፣ የወንጌልን አዋጅ ለሁሉም የማድረስ ጥሪ፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የወንጌል ስብከት የማድረስ ጥሪ ነው። ይህ የሚስዮናውያን አገልግሎት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተለምዶ አጽንዖት ተሰጥቶታል ብዬ የማስበው ሁለት ባህሪያት አሉት፣ ማለትም፣ ወደ እውነተኛ ሰዎች መሄድ፣ እራሳቸውን በሚያገኟቸው ሁኔታዎች ውስጥ እነርሱን ማግኘት፣ ይህም አዎንታዊ፣ አሉታዊ ወይም እንዲያውም ወሳኝ ሊሆን ይችላል። በእርግጠኝነት ግብዣው በትክክል የሚስዮናዊ ለውጥ ነው፣ እናም ለመለወጥ ጊዜ እና በጎ ፈቃድ ይጠይቃል። ነገር ግን ይህ ጥሪ በቤተክርስቲያኒቱ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ አምናለሁ፤ እናም አብዛኛው ሰው ወደዚህ አቅጣጫ በመንቀሳቀስ ለዛሬው ሕዝብ ወንጌልን ለመስበክ እና ከምንም ነገር በላይ በወንጌል ስብከት በኩል ምክንያት ለመስጠት ፈቃደኛ ነው ብዬ አምናለሁ። ለሕይወት ምክንያቶች እና ዛሬ ባለው ዓለም ውስጥ በጣም እንደሚያስፈልገን ተስፋ እናደርጋለን።

ጥያቄ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማልታን የጎበኙ ሦስተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚሆኑ ሲሆን ይህም  የምዕራባውያን ማኅበረሰቦች ዓይነተኛ ተግዳሮቶች የተጋፈጡ ቤተ ክርስቲያን ያለባት አገር ትሆናለች ማለት ነው። ይህን የማንነት እና የውይይት ጥምረት በምን መልኩ ነው መኖር የሚችለው?

መልስ፡ በማልታ ያለችው ቤተክርስትያን እንደ ማንኛውም በሁሉም ምዕራባውያን ሀገራት የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በተወሰነ ደረጃ ችግር ገጥሟታል። ትልቅ ለሰዎች ቅርብ የመሆን ሀይማኖት ባሕል አለ፣ ለሰዎች እና ለፍላጎታቸው ቅርብ መሆን፣ በጎ አድራጎትን በተመለከተ በማልታ ውስጥ ስላሉት ብዙ ስራዎች፣ አቅመ ደካማ ለሆኑ ሰዎች ትኩረት መስጠት፣ ለታመሙ ሰዎች ትኩረት መስጠት፣ ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት መስጠት እና በትምህርት ዘርፉ እያካሄዱት የሚገኘው ተግባራትን ብቻ መጥቀስ በቂ ሲሆን በተጨማሪም ቀደም ሲል የጠቀስነው በስደተኞች ዙሪያ ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ አስተዋጾ በማድረግ ላይ የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ናት።

በሌላ በኩል በሃይማኖታዊ ልምምዶች ላይ የተወሰነ ማሽቆልቆል እና ህብረተሰቡ የተመሰረተባቸው የክርስቲያናዊ እሴቶች መፈራረስ ታይቷል። መልሱ ቀደም ብለን የጠቀስነው ነው ብዬ አምናለሁ፣ ይህም ሊሆን ይችላል - እናም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከልባቸው የወጣ በሚመስል መልኩ ሀሳብ ያቀረቡት - በሁለትዮሽ የደቀ መዝሙርና የሚስዮናዊነት ፅንሰ-ሀሳብ የተቀየሰ ነው። በእኔ እምነት ደቀ መዝሙሩ ማንነትን የሚያመለክተው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ካለው ግላዊ ግንኙነት፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ከመከተል የመነጨ ጠንካራ ክርስቲያናዊ ማንነት ነው፣ ክርስቲያኑ ራሱን ያሳየ ሲሆን ማንነቱም የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ነው። በተመሳሳይ ጊዜ ደቀ መዝሙር - ሚስዮናዊ - ይህ ግልጽነት ከዛሬው ዓለም ጋር በሚደረግ ውይይት ከሁሉም በላይ መተርጎም አለበት። ውይይት በተመሳሳይ ጊዜ እንግዳ ተቀባይ እና መተቸት ማለት ሲሆን እውነታ እና የህብረተሰባችን አወንታዊ ገጽታዎች እንኳን ሳይቀር ለማሻሻል ጠቃሚ ነው።

ጥያቄ፡ ሰማንያ አምስት በመቶው የማልታ ህዝብ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ምዕመኑ በእምነት እንዲጸኑ ለማድረግ በማሰብ ወደ እዚያ የሚሄዱ ሲሆን የዚህ ተስፋ ምንድን ነው?

መልስ፡ ማልታ በእምነቱ እንዲጸና እና ይህ እምነት ወደ ምስክርነት እንዲተረጎም ተስፋ አደርጋለሁ ፣ የማልታ ክርስቲያኖች እምነታቸውን በአዋጅ መልኩ መመስከር እንዳለባቸው ያስችላቸው ዘንድ ጠንካራ ግንዛቤ እንዲፈጠር ያግዛሉ ብዬ አምናለሁ። “አጋጣሚ እና አስፈላጊ” በማለት ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረውን ማስታወስ እንችላለን፣ በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ፣ አንድ ሰው ወደደም ጠላም፣ ኢየሱስ ክርስቶስን አውጃለሁ፣ ወንጌሉን እሰብካለሁ ማለት ይኖርበታል። ስለዚህ በዚያ መልኩ የሚሄድ ምስክርነት  የአንድን ሰው እምነት በበጎ አድራጎት እና ሌሎችን በመቀበል ላይ ያለውን እምነት ወደ ሰውነት በመለወጥ ስሜት ውስጥ የሚሄድ ምስክርነት ነው።

01 April 2022, 15:30